
ከእነ ኮሚሽነር ዋኘው የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሯል የተባለ አንድ የልዩ ኃይል አባል ባህር ዳር ላይ ታሰረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከእነ ኮማንደር ዋኘው የግድያ ሙከራ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቀድሞ የርዕሰ መስተዳደሩ የህግ አማካሪ የነበሩት የመርሃ ፅድቅ አጃቢ እና የልዩ ኃይል አባል የሆነው አለባቸው አንተነህ ባ/ዳር ላይ መታሰሩ ታውቋል። የአማራ ክልል የልዩ ኃይል የብርጌድ አዛዥ ኮሚሽነር ዋኘው አዘዘው እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ ዳኛቸው በለጠ በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል። አንተነህ ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ከሆኑት የልዩ ኃይል አባላት መካከል አንዱ ስለመሆኑ በቅርብ የሚያውቁት ጓደኞቹ ያጋሩት መረጃ ያመለክታል።
Source: Link to the Post