ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸው ተገለፀ።ከቤት እንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ የተለያዩ በሽተዎች ቢኖሩም በማህበረሰቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ ለችግ…

ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸው ተገለፀ።

ከቤት እንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ የተለያዩ በሽተዎች ቢኖሩም በማህበረሰቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ ለችግሩ መስፋፋት መንስኤ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፣ ሰዎች እና የቤት እንስሳት አንድ ላይ የሚኖሩ በመሆናቸው ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች እንዳሉ ህብረተሰቡ ማወቅ አለበት ብለዋል።

ማህበረሰቡ ይህን በመገንዘብ በቤታቸው የሚገኙትን የቤት እንስሳት ጤንነት መጠበቅ እና ማስከተብ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ለአብነትም በብዙዎች ዘንድ የእብድ ውሻ በሽታ በመባል የሚታወቀዉን ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉውን በሽታ አንስተዋል።

በጤና ባለሙያዎች ዙሪያም በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ያልተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን የግንዛቤ እጥረትም ለመቀነስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ዶ/ር አለማየሁ መኮንን ተናግረዋል።

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply