አዲስ አበባ ፣መቐለ፣ ባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ህብረ ብሄር ከተሞች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የከተማው ህዝብ ብዛት ከመቶ 20 እጅ ነው፣ የገጠሩ ህዝብ ብዛት ደግሞ 80 በመቶ ነው፡፡
በአንድ አገር ሦስት መንግሥት!!! የህወሓት/ኢህአዴግ፣ የኦህዴድ/ ኢህአዴግ፣ የብአዴን /ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት አንድም ሁለትም ሦስትም ኛቸው፡፡ በአንድ አገር ስንት መንግሥት!!!
የኢትዮጵያ ህዝብ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ኢህአዴግ ከዶክተር አብይ አህመድና ለአቶ ለማ መገርሳ አዲስ የለውጥ ኃይል አመራር በፍፁም እምነትና ሃቀኝነት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር ሃገራችንን መምራት የሚችሉ ከእግዚያብሄር የተላኩ ‹መሲሃዎች› መጡልን፣ እንባችንን ሊያብሱ፣ ቁስላችንን ሊያክሙ፣ ሞራላችንን ሊገነቡ፣ ከስደታችን ሊሰበስቡን፣ ከእጃችን ካቴና ከእግራችን እግረሙቅ ሊፈቱ፣ ከኢሰብዓዊ ግርፋት ሊታደጉን፣ የጅምላ መቃብር ስፍራዎችን መቼም የትም እንዳይደገም ሊያደርጉ፣ እስር ቤቶችን ወደ ሙዚየምነት ሊቀይሩ፣ መልካም አስተዳደር ሊያሰፍኑ፣ ሙስናና ሌብነት ላንዴም ለሁሌም ሊያጠፉ፣ በህዝባዊ እንቢተኛነትና ተጋድሎ የወደቀውን የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በመጣል፣ ህዝባዊውን በትረ ሥልጣን አበረከትንላቸው፡፡ ከዛም አልፎ ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በህብረት ምርጫው ተራዝሞ በእነሱ አመራር ለውጡን እንዲያሸጋግሩ ሁሉም ከልቡ ፈቀደ፡፡ እግሩ የሸበተ፣ ፀጉሩ የሸበተና ልቡ የሸበተ የቲም ለማ ቡድን በቅቤ አንደበታቸው የሽምቅ ተዋጊውን እንደ ዝናር በቅፌ በአንደበታቸው ደባለቁት፣ ደመሩት፣ በአንደበታቸው ውሃውን ፀበል፣ እባብን ዱላ፣ እሳቱን ውኃ፣ አረጉት፡፡ አበው ‹‹ጉድና ጅራት ከበስተኃላ ነው!!!›› እንዳሉት ከህወሓት/ኦህዴድ ኢህአዴግ ሆድ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!!›› ፈጣሪ እንዲመረምርለት የዋሁ ህዝብ ላከው፡፡ ኦህዴድ ‹‹በየክልሎቹ ያለ ልዩ ፖሊስ፣ የሚሊሽያ ኃይል፣ የደህንነት መረጃ፣ የክልል ማስ ሚዲያ ሰጣ ገባ፣ ህገ ወጦችን አሳልፎ አለመስጠት፣ ለፌዴራል መንግሥት አለመታዘዝ፣ ህገወጥ የመሥሪያና የገንዘብ ዝውውር፣ የ3.2 ሚሊዮኝ ህዝብ መፈናቀልና ርሃብ፣ የህግ ሉዓላዊነት አለመከበር!!!›› እንቆቅልሹ ምን ይሆን፡፡ ህወሓት/ ኦህዴድ ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ‹‹ እንቁላል ዶሮ፣ወይስ ዶሮ እንቁላል!›› ዓይነት ሆነብን፡፡ ህወሓት አንዴ ወልቃይት አንዴ ራያ ጦር ያዘምታል፣ የጦርነት ነጋሪት ይጎስማል!!! በአንድ አገር ሦስት መንግሥት ሆነብንና፡፡ የአማራም ክልል የጦርነት ቀረርቶ ያሰማል፣ በወልቃይታ በራያ ቀልድ የለም! የክልሎቻቸው ማስ ሚዲያ የጥላቻ ሚሳዔል፣ ላውንቸር፣ያወናጭፋሉ፡፡ የፌዴራል መንግስት አልቢትሮ ይመስላል፡፡ የኦሮሚያ መንግሥትም አዳዲስ ቅራኔዎችን እንደ አሸን ይፈለፍላል፣ ኦህዴድ ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም!!!›› ‹‹በህገ-መንግሥቱ ድርድር የለም!!!›› ‹‹የኮንዶሚኒየም ቤቶች መውረስ!!!›› ‹‹የመከላከያ ሠራዊት ሪፎርም በፈረቃ መጠናቀቅ!!!››፣ ‹‹የኦሮሞ ተፈናቃይ ህዝብን አዲስ አበባ የማስፈር መርሃ ግብር!!!››፣ ‹‹ የህገ ወጥ ቤቶች የማፍረስ ፕሮግራም!!!››፣ ‹‹የመንግሥት ሚዲያ ኢቢሲ በኦህዴድ በፈረቃ መያዝ››፣ቤተ-መንግሥት ለመፈንቅለ መንግሥት የገቡት የአጋዚ ልዩ ኮማንዶ ጦር በፑሻፕ ልቡ ጠፍቶ በተማረከ ምሽት ‹‹ከሠንዳፋ፣ ሱሉልታ፣ ሰበታ፣ ለቡ፣ ገላን፣ ገፈርሳ፣ ዓለም ገና፣ ጫንጮ፣ ዱኮም፣ ፈረሰኞች ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነበር!!!›› ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባ ህዝብ ልቡ አዘነ፡፡ የማይታመን ህዝብ!!! ሁለተኛ ዜጋ መሆናችን የገባን፡፡ ህወኃት ለኦህዴድ አዳዲስ ትወና እንዲካንና ኦህዴድ ህወሓትን የህግ ጥስት፣ የስብዓዊ መብት ጥስት፣ የሙስና ዘረፋ ወንጀል፣ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር ሤራ፣ የወልቃይትና የራያ ቬቶ ፓወር ቅቡልነት ከህወሓት/ኦህዴድ ኢህአዴግ ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! ውስጥ ይገኝ ይሆን፡፡ ከህወሓት/ኦህዴድ ኢህአዴግ ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! የህወሓት/ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ለኦህዴድ/ኢህአዴግ የጦር አበጋዝ መንግሥት፣ ቀጥሎ ለብአዴን፣ ቀጥሎ ለሱማሌ፣ ለጥቆ ለሲዳማ እያለ ይዘልቅ ይሆን!!! ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ ይሆን ይሆን!!! ህወሓት/ኢህአዴግ ገምቶ በስብሶ፣ በኦህዴድ፣ ብአዴንና፣ ደህኢዴን ትግል ያብብ ይሆናል!!! ህብለ ሠረሰር የሌላቸው ተፎካካሪ 107 ፓርቲዎች ህዝቡን ለስንት ጊዜ ይሆን የሚሸጡት!!! ለ107 ፓርተዎች መሪዎች የመወዳደሪያ የምርጫ መግቢያ ፈተና (የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ፣ የህግ፣ የጆግራፊ፣ የቴክኖሎጂ፣ የውጪ ጉዳይ ወዘተ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ብቻ እንዲወዳደሩ ቢደረግ 107 ወደ 7 ፓርቲዎች ይቀየራሉ 100 መራጮች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ፈተናውን ገለልተኛ ማህበር ቪዝን ኢትዮጵያ ቢያዘጋጀው ይመረጣል፡፡) የከተማ ኑዋሪዎች በክፍለ ከተማ፣ወረዳና ቀበሌ ተደራጅቶ በምርጫ ከንቲባውን መምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት አላቸው፡፡ በተመሳሳይ መምህራን ማህበር፣ የሠራተኛ ማህበራት፣ የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የገበሬዎች፣ ሲቪክ ሶስይቲ መደራጀት ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ኢህአዴግ 7 ሚሊዮን ካድሬዎችና የፓርቲ ንግድ በሞኖፖል የያዘ ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ያስቀጠለ መንግሥት ነው፣ ህገመንግሥቱ አይነኬ እንደሆነ ተነግሮናል!!! ኢትዮጵያ የማናት የቻይና!!! የቻይና ስውር ቅኝ ግዛት፣ አርፈን 17.5 ቢሊየን ዶላር የቻይና ብድርን ለመክፈል ተግተን ብንሠራ ይሻለናል እንላለን፡፡ ቴሌ፣ የምድር ባቡር ፣ አየር መንገድ፣ የንግድ መርከብ ወዘተ ያለባቸው የቻይና እዳ የትየለሌ ነው፡፡ በእዳ የተተበተበ ፓርቲ ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ ነውና!!!
የኢትዮጵያዊያ ከተማ ነዋሪዎች በምርጫ ራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት አላቸው
ከህወሓት ወደ ኦህዴድ የጦር አበጋዞች ዘመነ መንግስት
በ1994 እኤአ በማዕከላዊ እስታትስቲክስ ባለሥልጣን መስሪያ ቤት ይፋ የተደረገው በኢትዩጵያ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ መሠረት በአዲስ አበባ፣ድሬ ዳዋና በሃራሪ ከተሞች ውስጥ ያለውን የንዋሪዎች የህዝብ ስብጥር ከሠንጠረዡ ውስጥ ቀንጭበን ለማሳየት እንሞክራለን፡፡ የዛሬ 21 አመት የወጣው እስታትስቲክስ ሪፖርት ዛሬ በምን መልክ የከተማዎቹ ንዋሪዎች የህዝብ ስብጥር እንደደረሰ መረጃ የለም፡፡ እንዲህ ዓይነት ሪፖርትም ከዛ በኃላ በማዕከላዊ እስታትስቲክስ ባለሥልጣን ለህዝብ ቀርቦ አያውቅም፡፡ ዋናው አላማው ግን አማራውን፣ኦሮሞውንና ጉራጌውን ቁጥር በነዚህ ከተሞች መቀነስ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ወያኔ ምርጫ በደረሰ ግዜ በእነዚህ ከተሞች ህዝቦች ባለመመረጡና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋፊዎች ናቸው የሚል መረጃ ስላለው ነው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋና በሃራሪ ከተሞች ውስጥ የህዝቡን ስብጥር በጉልበት መቀየር ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ነው በመልሶ ማልማት ፕሮግራም ስም በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቀጥሎም በድሬ ዳዋና በሃራሪ ከተሞች ውስጥ ለማድረግ እቅድ ነበረው፡፡ በዚህም መሠረት በነዚህ ከተሞች ውስጥ ለዘመናት የኖረውን ህዝብ በእድር፣ በእቁብ፣ በፅዋ ማህበራት፤ በሰርግና በሃዘን አብሮ የሚኖረውን ህዝብ መፐወዝ ያስፈለገው፡፡ የከተማውን ህብረተስብ ድርና ማግ የሆነበትን (Social fabric) በመበጣጠስ ወደ ልዩ ልዩ ቦታዎች ህዝቡን በማስፈር ከ50 እስከ 70 አመታት የኖሩበትን መንደርተኛች በስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ የከተተው፡፡ ወያኔ በምትካቸው ከሃገሪቱ ልዩ ልዩ ቦታዎች ታመኝ የሆኑ ሰዎችን ማስፈሩ ለመጭው ምርጫ በአሸናፊነት ለመወጣት የጠነሰሰው ዘዴ ነበር፡፡
Table 2.15 Percentage Distribution of Majour Ethnic Groups with 500,000 or more Persons by Region, Ethiopia: 1994
Ethnic group Affar
Amara Gedo Guragie Hadiya Keffa Oromo Sidama Somalie Tigraway Welaita Gamo Other Eth.Nationa
l groups Foreigners Not stated Total
Addis Ababa 0.0 48.3 0.0 17.5 0.4 0.1 19.2 0.1 0.2 7.6 0.5 0.9 3.0 2.0 0.1 100
Dire Dawa 0.0 27.7 0.0 4.5 0.5 0.0 48.0 0.0 13.9 1.8 0.2 0.0 2.2 0.9 0.1 100
hararai 0.0 32.6 0.0 3.2 0.0 0.0 52.3 0.0 1.7 1.7 0.1 0.0 8.2 0.1 0.1 100
Source:-the 1994 population and housing census of Ethiopia, volume II analytical report, page 44
• አማራ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 48.3 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 27.7 በመቶና በሃራሪ ከተማ 32.6 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ኦሮሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 19.2 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 48.0 በመቶና በሃራሪ ከተማ 52.3 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ጉራጌ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 17.5 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 4.5 በመቶና በሃራሪ ከተማ 3.2 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ትግራይ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 7.6 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 1.8 በመቶና በሃራሪ ከተማ 1.7 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ሱማሌ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.2 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 13.9 በመቶና በሃራሪ ከተማ 1.7 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ወላይታ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.5 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.2 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.1 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ጋሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.9 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.0 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.0 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ሃዲያ ህዝብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 0.4 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.5 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.0 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
• ሌሎች ኢትዩጵያዊ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 3.0 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 2.2 በመቶና በሃራሪ ከተማ 8.2 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አላቸው፡፡
• የውጭ ዜጎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 2.0 በመቶ፣ ድሬ ዳዋ ከተማ ውስጥ 0.9 በመቶና በሃራሪ ከተማ 0.1 በመቶ ከነዋሪዎቹ ድርሻ አለው፡፡
ከኦህዴድ/ኦዴፓ ኢህአዴግ ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!! ከተሞች፣ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምርጫ ራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ መብት አላቸው ወይስ የላቸውም፡፡
በኢትጵያ የከተማ ህዝብ ብዛት ከመቶ ሃያ እጅ ሲሆን የገጠር ህዝብ ባዛት 80 በመቶ እጅ ይይዛል፡፡ ቀጥሎ በሚገኑት ከተሞች ውስጥ ህብረ ብሄር ህዝብ እንደሚኖሩባቸው ከላይ ካለው የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋና ሃረር ከተሞች የህዝብ ሥርጭት ሠንጠረዥ ማየት ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ፣ (3,273,000 እስከ 3,352,000 ሲገመት ከዚህም በላይ ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን የሚገምቱ ሰዎች አሉ፡፡ በተመሳሳይ በሃገሪቱ ውስጥ ከመቶ ሽህ በላይ ህዝብ ያላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ጎንደር (323,900 እስከ 341,991)፣ መቀሌ (323,700 እስከ 340,859)፣ (187,900-198,428)፣ ጂማ (177,900-186,148)፣ ጂግጂጋ (159,300-164,321)፣ ሻሸመኔ (147,800- 154,587፣ ሶዶ (153,322)፣ ብሸፍቱ/ ደብረዘይት (147,100- 153,847)፣ አርባ ምንጭ (142,900-151,013)፣ ሶዶ (145,100)፣ ሆሳዕና (133,800-141,352)፣ ሀረር/ሀረሪ (129,000-133,000)፣ ዲላ (112,900-119,276)፣ ነቀምት (110,640-115,741)፣ ደብረ ብርሃን (102,100-107,827)፣ ደብረ ማርቆስ (103,263)፣ አሰላ (103,522)፣ ከተሞች፣ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምርጫ ራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት አላቸው እንላለን፡፡
ከኦህዴድ/ኦዴፓ ኢህአዴግ ሆድቃ የተገኘ ጥቁር ሰንዱቅ!!!
{1} የአዲስ አበባ ወጣቶች ዴሞክራሲያዊ ትግል በተካሄደ ሠላማዊ ሠልፍ በግፍ 5 ወጣቶች ሞተዋል፣ በሽህ በላይ ወጣቶች ላይ ክስ ሳይመሰረተ በጦላይ እንዲታሰሩ መደረጉ ህዝባዊውን ትግል በፍርሃት ከቶታል፣ ወያኔ የገዳዬች በሪሞት የሚቆጣጠረው የገዳይ ኃይል እንዳለ ተረድተናል፡፡
{2} በሃረሪና የድሬዳዋ ከተሞች፡- የሃረሪ ክልላዊ መንግሥት በሀብሊና ኦህዴድ 40/40/20 አስተዳደራዊ የግፍ አገዛዝ ሃረርና የድሬዳዋ ህዝብ የአዲሱ የዴሞክራሲያዊ ለውጥ ተቆዳሽ መሆን አልቻለም፡፡
{3} በሃዋሳ ከተማ በደቡብ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ የክልላዊ መንግሥት ጥያቄ የህዝቡን አብሮ የመኖር ህልውና ዘለቄታዊ ጥቅም በምን መልኩ ያስተናግዳል ሃዋሳ ከተማ ህብረ ብሄራዊ ዜጎች ህልውና ቀጣይነት ምን ይሆናል መልስ ያሻዋል፡፡
{4} በአዳማ ከተማ የህዝቡን አብሮ የመኖር ህልውና ዘለቄታዊ ጥቅም በምን መልኩ ያስተናግዳል አዳማ ከተማ ህብረ ብሄራዊ ዜጎች ህልውና ቀጣይነት ምን ይሆናል መልስ ያሻዋል፡፡
{5} በባህር ዳር ከተማ የህዝቡን አብሮ የመኖር ህልውና ዘለቄታዊ ጥቅም በምን መልኩ ያስተናግዳል የባህር ዳር ከተማ ህብረ ብሄራዊ ዜጎች ህልውና ቀጣይነት ምን ይሆናል መልስ ያሻዋል፡፡
{6} በአጠቃላይ ከመቶ ሽህ ህዝብ በላይ ያላቸው ህብረ ብሄራዊ ዜጎች የሚኖሩባቸው የከተሞች እጣ ፈንታ በኢትዮጵያ እንዴት ይቀጥላል፡- የአዲስ አበባ፣ ጎንደር ፣ መቀሌ ፣ ጂማ ፣ ጂግጂጋ ፣ ሻሸመኔ፣ ሶዶ፣ ብሸፍቱ፣ አርባ ምንጭ፣ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ሀረር፣ ዲላ፣ ነቀምት፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ አሰላ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ከተሞች፣ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምርጫ ራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት አላቸው እንላለን፡፡
source:-
• World population Review, Population of cities in Ethiopia (2019) latest official projections.
• Ethiopia: Regions, Major Cities & Towns- Population statistics in Maps and charts. WWW.citypopulation.de>Ethiopia/ Federal Democratic republic of Ethiopia
• (1984) Central Statistical Agency of Ethiopia (provided by Clive Thornton))
• (1994)(2007)(2015 ) Central Statistical Agency of Ethiopia(web)
• (2016) List of cities and towns in Ethiopia (WikipediA)