ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ የሚፈልሱ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ደቡብ ወሎ መግባታቸው ተነገረ፡፡

ከ2011ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዞኑ እየተሰደዱ ያሉ ሰዎች ከ11 ሺ በላይ ሆነዋል ነው የተባለው፡፡ተፈናቃዮች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ጥቃትን ሸሽተው ወደ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መግባታቸውን የዞኑ ምክትል አስተዳደሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ ለአሀዱ ገልጸዋል፡፡

ከተፈናቃዮቹ መካከል አብዛኛዎቹ ሕፃናትና ሴቶች መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡በዞኑም ለተፈናቃዮቹ አስፈላጊዉ አቅርቦት እየተደረገ ቢሆንም በሁለት ካምፖች ከ1 ሺ በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸዉን  እና አስፈላጊዉን ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ የክልሉን እና የፌደራል መንግስትን መጠየቃቸዉን ተናግረዋል፡፡

ከመጠለያ ጣቢያዉ ዉጪ ያሉት ተፈናቃዮች በተለያዩ ወረዳዎች የሚያውቋቸው ነዋሪዎች ዘንድ ተጠልለዋል ብለዋል፡፡በአሁን ሰአት ብርድ ልብስ፤ የህጻነት አልሚ ምግብ፤ ለነብሰ ጡሮችም የህክምና አገልገሎት እጥረት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ቀን 30/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ የሚፈልሱ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ደቡብ ወሎ መግባታቸው ተነገረ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply