ከኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ የተፈናወሉ አማራዎች ዛሬም ድረስ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡                አሻራ ሚዲያ…

ከኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ የተፈናወሉ አማራዎች ዛሬም ድረስ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

ከኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ የተፈናወሉ አማራዎች ዛሬም ድረስ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-17/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር ከኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ከአራት ሽ በላይ የሚሆኑ አማራዎች ተፈናቅለው ባህር ዳር መግባታቸውን መግለጻችን ይታወቃል ፡፡ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ አማራዎች ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ መግባታቸውን ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸውልናል፡፡ እንደ ምንጫችን ገለጻ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ አሁንም 15 አባ ወራዎች መንገድ ተዘግቶባቸው ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ተፈናቅለው የመጡ የአማራ ተፈናቃዮች አሻራ ሚዲያ ባነጋገረበት ወቅት ብዙ ግፍና በደል እንደደረሰባቸው ለአሻራ ሚዲያ ገልጸው ነበር፡፡ የቤተሰብ አባላቶቻቸውም በኦነግ ሸኔ አባላትና በክልሉ መንግስት የስራ ሀላፊዎች ተባባሪነት በጥይትና በስለት እንደተገደሉባቸው መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በኦነግ አባላት በታቸው እንደተቃጠለባቸውና ንብረታቸውም እንደተዘረፈ ተፈናቃዮች ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም አስመልክቶ ምንም አይነት እርዳታ እንዳላደረገላቸውና በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ስዓት እነዚህ ተፈናቃዮች በሰቆጣና ወልድያ ከተማ የቀን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ተፈናቃዮች እንደገለጹት ባህር ዳር ገብተን ለሚመለከተው አካል ብናመለክትም ወደ ወረዳችሁ ተመለሱ ብሎን በተለያየ ከተማ ገብተን ችግር ውስጥ እንገኛለን ብለዋል፡፡ በመጨረሻም አሁንም ችግር ውስጥ ስላለን የክልላችን መንግስት አስፈላጊውን ትብብር ያድርግልን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply