ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ሀይቅ የሚገኙ አማራዎች በቂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/…

ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ሀይቅ የሚገኙ አማራዎች በቂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በጅምላ እየተጨፈጨፉ፣ እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ እና እየተሳደዱ ያሉ አማራዎችን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ሲመጣ እንጅ ሲቀንስ እየተስተዋለ አይደለም። ከምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ፣ ከቄለም ወለጋ ዞን ሮብ ገቢያ/ሀዋገላን ወረዳ ለምለም ቀበሌ መንደር 20 እና 21፣ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ እና አሙሩ፣ ከምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉትን፣ ኪረሞ እንዲሁም ከከማሽ ዞን ሚዥጋ/በለው ጅጋንፎይ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት በአሸባሪ ኦነጋዊያን በጅምላ የተጨፈጨፉ ብዙ ናቸው፤ ለዘመናት ከሚኖሩበት ቀዬ የተፈናቀሉትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ናቸው። በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ወሎ ሀይቅ አቅንተው “በቱርክ ካምፕ” ተጠልለው የሚገኙ በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች በቂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ነው። ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ተጠልለው የሚገኙ አማራዎችም እዚህ እርዳታ አታገኙም በመባላቸው ወደ ሀይቅ እና ጃራ እየተጓዙ መሆናቸው ተገልጧል። በአጠቃላይ አስቸኳይ እና በቂ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጹት ተጎጅዎች መንግስት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ማናቸውም የሰው ልጅ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች ሁሉ እንዲደርሱላቸው ጠይቀዋል። በቅርቡ ከመንግስት በኩል የተወሰነ እርዳታ የቀረበ ቢሆንም ለሁሉም ሊደርስ አለመቻሉ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply