ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ መናኽሪያ የነበሩ አማራዎች ከግቢ እንዲወጡ መደረጉን ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ መናኽሪያ የነበሩ አማራዎች ከግቢ እንዲወጡ መደረጉን ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡሰዮ፣ ጉዳያ ቢላ፣ስቡስሬ እና ከምዕራብ ሸዋ ባኮቲቤ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በግብረ አበሮቹ ለዘመናት ከሚኖሩበት ቀዬ የተፈናሉ አማራዎች ከተጠለሉበት አስኮ መናኽሪያ እንዲወጡ መደረጉን ለአሚማ ተናግረዋል። ከጥር 16 ቀን 2014 ጀምሮ ተፈናቅለው አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ እየለመኑ ዘመድ ያለው በየዘመዱ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ፣ በየመስጊዱ እና በየበረንዳው እየተጠለሉ ከቆዩ በኋላ ኑሮውአቸው ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ አስኮ መናኽሪያ አቅንተው ለልመና ተዳርገዋል። ወደ አስኮ መስተዳድር እና ጉለሌ ክ/ከተማ ሄደን ትብብር እንዲደረግልን ብንጠይቅም የሚያስተናግደን አላገኘንም ሲሉ አማረዋል። እነዚህ ቁጥራችን ከ300 በላይ እንደሚሆን ለአሚማ የገለጹት ተፈናቃይ አማራዎች ጥር 7 ቀን 2014 ረፋድ ላይ ወደ መናኽሪያው የመጡ አንድ አመራር እና ፖሊሶች ከግቢ እንድንወጣ በማድረጋቸው ሜዳ ላይ ለመውደቅ ተገደናል ብለዋል። አሁንም መንግስትም ሆነ የሰብአዊ ድርጅቶች በአስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ሊሰጡን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የኦሮሚያ፣ የአማራ ክልል መንግስት፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር እና የፌደራል መንግስት ንጹሃን አቅመ ደካሞች፣ አዛውንቶች፣ ህጻናት፣ወላዶችና ህሙማን በአስተሳሰብ ድኩማን አሸባሪዎች ተፈናቅለውና ከሞት ተርፈው አዲስ አበባ የደረሱ ወገኖችን ከማገዝ ይልቅ እየሰሙ እንዳልሰሙ እያለፉ ነው። ማቋቋሙ እንኳ ቢቀር በአሳዳጆች ላይ እርምጃ በመውሰድ፣ ከዘር ቆጠራ ወጥተው እንደ ሰው በማሰብ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ሲያቀርቡ እየተስተዋለ አይደለም የሚሉት ብዙዎች ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply