ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው።በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/L74cpOwJJRs3ffBnz--K_zGpT_G8ukpj3SQ9wbXZR9UuqrSDapS6aD1Xz5v6d4uLy54xaAt45DixTB_x-qXvE1r38b0L2UZzRhT5GWN1BFGc_RdVfnrI4kUVSC7luzxk_o4NCeah70HLv2kkSJ4g7-azJFuQM4nzYhhwNKOJJRfaODv0SCy-YIre5cT63JPj8r_4fhWXgb5SQnqA9Fe8MUXKK2DWmH7faQoT50AWsIXDrVRG6WjqdcmimnU7mswQBZaXrr3N2kF05PIElHAvIt245NVNWxLJOX5gZXjiGy74o2yVlKyBRrIW0uavYD6uG8_ihl7ICtn-0HyJyGRK1w.jpg

ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው።

በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋናው የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የተባለው መሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትን እና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለማሻሻል ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት ለመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየት ዋናውና ትልቁ ማነቆ የልማት ተነሺዎች የሚጠይቁት የተጋነነ የካሳ ክፍያ መሆኑን ገልጸው፤ ንብረት የሚገምቱ እና ካሳ የሚከፍሉ ተቋማት ወደ አንድ ሊመጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በማህበረሰቡም ፕሮጀክቶች ተገንብተው ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ፤ ከካሳ ክፍያ የሚገኘውን ጥቅም አስበልጦ የማየት አስተሳሰብ በመኖሩ፤ ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘበ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም የአዋጁ መሻሻል አስፈላጊነቱ የላቀ እንደሆነም ባለድርሻ አካላት አንስተዋል።

የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው የአዋጁ መሻሻል በካሳ ክፍያ ሂደቱ በታችኛው እርከን የመንግስት አስተዳደር፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋና የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ማሻሻያ አዋጁ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ የንብረት ግመታው እና የካሳ ክፍያው በክልልና በወረዳ መዋቅሮች የሚፈጸም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ቅሬታ ሲያነሱም በአቅራቢያቸው የፍትህ አገልገሎት እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply