ከክፍለ ሃገር የመጣ በማስመሰል ሀሰተኛ መሸኛ እያዘጋጁ ተገልጋዩን ሲያጭበረብሩ ቆይተዋል የተባሉ በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ አምስት ተቋማት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ።እርምጃውን የወ…

ከክፍለ ሃገር የመጣ በማስመሰል ሀሰተኛ መሸኛ እያዘጋጁ ተገልጋዩን ሲያጭበረብሩ ቆይተዋል የተባሉ በህትመት ስራ ላይ የተሰማሩ አምስት ተቋማት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ።

እርምጃውን የወሰደው የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ነው።
ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኝት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ይህ ችግር እየተፈጠረ ያለው ብሏል መስሪያ ቤቱ።

እርምጃው የተወሰደባቸውም ከክፍለ ሀገር የተሰራ በማስመሰል ከአንድ ክልል ወይም ቀበሌ የተሰጠ አስመስለው ህገወጥ መሸኛ ሲሰሩ የተገኙ ህትመት ቤቶች ናቸው ተብሏል።
እነዚህ ቤቶች የማይሰሩት ህገወጥ የህትመት ስራ የለም ያሉት፣ የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የነዋሪነት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ናቸው።

ዳሬክተሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የስራ ፍቃድ የወሰደ ሁሉ በህግ አግባብ ስራውን ይሰራል ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡
ቤቶቹ ከህገወጥ መሸኛ በተጨማሪ ህገወጥ የልደት ሰርተፍኬት እና የተለያዩ ሰነዶችን እንደሚያዘጋጁም ተደርሶበታል ብለዋል፡፡

እነዚህ ህገወጥ የህትመት ቤቶች በሚሰሩት ህገወጥ ስራ ምክንያት፣ ዜጎች በህጋዊ መንገድ መታወቂያ እንዳያገኙ ምክንያት መሆናቸውን ነው አቶ ዮሴፍ የተናገሩት።

ከነዋሪነት መታወቂያ እና ከሌሎችም አገልግሎቶች ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ሌብነቶችን ለማስቀረት ተቋሙ አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ እያደረገ እንደሚገኝም ዳሬክተሩ ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና

በአዲስ አበባ የወረቀት የነዋሪነት መታወቂያ ሙሉ በሙሉ መቆሙ ይፋ ሊደረግ ነው።
ከተማዋ በነዋሪነት ለመዘገበቻቸው ነዋሪዎች ለዘመናት በወረቀት ስትሰጥ የነበረውን የነዋሪነት መታወቂያ /City Residency ID/ ካርድ ሙሉ ለሙሉ ማቆሟን ይፋ ታደርጋለች።
አ/አ በዘመናዊ የከተማ አስተዳደር የከተማ የነዋሪነት መታወቂያን በተደራጀ መልኩ በመስጠት ከ75 ዓመት በላይ እድሜን አስቆጥራለች።
የወረቀት መታወቂያን ለመጨረሻ ግዜ ተሰናብታ ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል መሻገሯን በነገው እለት ሰኔ 25/2016ዓ.ም ይፋ እንደምታደርግ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሳውቋል።

በሔኖክ ወገብርኤል

ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply