‹‹ ከኮሮናቫይረስ ተዓቅቦ፣ወደ ምርጫ ተዓቅቦ!!! በስመ ዴሞክራሲ ስንት ግፍ ተሠራ!!! ›› ሚሊዮን ዘአማኑኤል

የአንባገነንነትና የዶሚኖ ውድቀት ውጤት እያሳሳቀ ነው!!! The Dictatorship and Domino Effect
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ባደረገው ውይይት መሠረት የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ 119 (መቶ አስራ ዘጠኝ) ተሰብሳቢዎች ውስጥ 114 በመቶ አስራ አራት ድጋፍ፣ በአራት ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቋል። በአጀንዶዎቹ መሠረት ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቦ ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልፆል።
• የኮሮናቫይረስ ወረርሺኙ ስጋት ሆኖ እስካለበት ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል፤
• እንዲሁም ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ አለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሲያረጋግጥ
• የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካጸደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው ውሳኔ ያሳለፈው።
እንኳን ‹‹ ከኮሮናቫይረስ ተዓቅቦ፣ወደ ምርጫ ተዓቅቦ!!! አደረሳችሁ፣ እዚህ አገር በስመ ዴሞክራሲ ስንት ግፍ ተሠራ!!!›› ፍርኃታችን ልክ አጣ፣ የወያኔ ኢህአዴግና የብልጽግና ኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራና ማጭበርበር ሰለቸን፣ የሃገር ድንበር የማያስከብር መከላከያ ሠራዊት፣ የህዝብ ህይወትና ንብረት የማይጠብቅ የፖሊስ ሰራዊት፣ ፍትህና ርትህ የማያስጠብቅ የፍትህ ሚኒስትር/ ፍርድ ቤት፣ በህዝብ ያልተመረጠ የአንባገነን መንግስት ውድቀቱ እንደ ዶሚኖ ጠጠር ዓይነት ነው፣ አንድ የክብሪት እንጨት ስትለኮስ እሳቱ ጫካ ማቃጠሎን የዘነጉ የተማሩ ልጆቾ መአዛ አሸናፊ፣ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ አዳነች አቤቤ፣ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ሊያ ታደሰ፣ ዶክትር አብይ አህመድን ወደ ኮነሬል አብይ አህመድ አሸጋገራችሁት እንላለን፡፡ የሴት ሚኒስትሮች ምክር ቤት አቆቁማችሁ የአንባገነናዊ ሥርዓትን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመተካት ታገሉ! የአገር መሪነት ሥልጣን ለእናንተም ይገባልና!!! አለዚያማ…..
በፈቃድ ከመጣ ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!! (‘No slavery is more disgraceful than that which is self-imposed’Seneca) ይሄ አባባል ለእኛ ‹‹በፈቃድ ከመጣ የልሂቃን ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ቢባል ያስኬዳል፡፡ የኢትዮጵያ ልሂቃን ከባህር ማዶ የቀሰሙትን ትምህርት ከሃገራቸው ተጨባች ሁኔታ ጋር ባለማዛመድ እንዳለ በመቅዳትና በመተርጎም ከስልጣኔ ማማና ከምሁራን ጎራ ቢደመሩም ለሃገራቸው የፖለቲካ፣ ምጣኔ ኃብትና ምህበራዊ ጉዳዮች የሰጡት መፍትሄ አጠያያቂ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በቀኃሥ፣ በደርግና በኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት፣ኦዴፓ ብልፅግና መንግስት ዘመን ህገ- መንግሥቱ ከተለያዩ ሃገራት የተገለበጠ ህገመንግሥት፣ የፖለቲካ ርዕዮት፣ የኢኮኖሚ እቅድ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ችግር አፈታት በአጠቃላይ የመንግሥታዊ አስተዳደርና ሥርዓተ መንግሥታዊ መዋቅሮች የተኮረጁና በህዝብ ላይ በግድ የተጫኑ ለመሆናቸው ሾተላይ ሰላይ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በወያኔ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘር ፌዴራሊዝም ፖለቲካ ከተጫነብን 29 አመታት ተቆጠረ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ህዝቡን በልሳን ከፋፍሎ ለሞት፣ እስራትና ስደት ዳረገው፡፡ በኦሮሞና ሱማሌ፣ በአማራና ትግራይ፣ በሲዳማና ወላይታ፣ ወዘተ በተከሰተው የዘር ግጭት የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች ቁጥር ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን አሻቅቦ ነበር፡፡
(1) የህወሃት በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተካሄደበት፣በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፀመብን ‹ኢንተር ሃሞይ!› ብለው እንደጮሁት ዛሬም ድራማ እየሰሩ ናቸው ታዲያ እነዚህን ቦዘኔ ሌባ የወያኔ አመራሮች ‹‹በፈቃድ ከመጣ የወያኔ አመራር ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ልንላቸው ይገባል፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን ስለማይችል መቐለ የመሸገው ፀረ-ዴሞክራቲክ ኃይል ለፍርድ መቅረብ ይገባዋል እንላለን፡፡ በዘር ግጭት! የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች፡-የማንነት ጥያቄ ሠለባዎች፣ ባለፉት 29 አመታት ወያኔ ባጸደቀው በዘርና ልሳን በተከለለ ፌዴራላዊ ክልላዊ አስተዳደር የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁም ስቅሉን በማየት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ በወያኔ ከፋፍለህ ግዛው የአባላህኝ ዘመን ከክልላቸችን ውጡ፣ ቅስቀሳ የተነሳ የሃገራችን ዜጎች በሁሉም የሃገሪቱ ጋዛት ውስጥ ተዘዋውሮ የመስራት መብቱንና ክብሩን አጥቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ከአንድ ሚሊዩን 500 ሽህ ህዝብ በላይ የኦሮሞና ሱማሌ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በጉጂ ኦሮሞዎችና በሲዳማ ጊዴኦ የዘር ግጭት የተፈናቀሉ ከ750 ሽህ እስከ አንድ ሚሊዮን ወገኞቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በሲዳማና ወላይታ በተከሰተው የዘር ግጭት ከ20 እስከ 30 ሽህ ህዝብ ሲፈናቀል በተመሳሳይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 8510 የትግራይ ተወላጆች የዘር ግጭትን በመፍራት ወደ ትግራይ ክልል ተመልሰዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የትግራይ ርዕስ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዬን አንዴ የትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተደረገ በማለት አንዴ ህገመንግሥቱ ተናደ፣ አንዴ ፌዴራልዝሙ ፈረሰ ከመቐለ በማለት እያቅራሩ ትግራይ ራሶን ገንጥላ መንግሥት ትሆናለች በማለት ሲያስፈራሩ ሁለት አመታት አለፈ፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአንድ በኩል የተሰለፉ ሕወሓት የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምርጫ ለማካሄድ ወስኖል፡፡ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባርና ኦፌኮ ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጥያቄን ተቃውሞል፡፡ የኦዴፓ/ ብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ክልል በአምስት ክልሎች የመወቀር ጥያቄም ተቀባይነት አጥቶል፡፡ ከኦዴፓ/ ብልፅግና ፓርቲ ጋር የወገኑ ኦዴፓብልፅግና፣ አዴፓብልፅግና ፣ደኢህዴን ብልፅግና፣ የሶማሌ፣ ሃረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቢኒሻንጉል፣ አፋር፣ ብልፅግና ክልላዊ መንግስታት ኢዜማ ሲሆኑ በሦስተኛው ጎራ ያሉ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ አብሮነት፣ መድረክ፣ አብን፣ ወዘተ የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጊዜያዊ የሽግግር / የባለአደራ/ መንግሥት አቆቁመው ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የጣምራ መንግስት ለመመሥረት ካሁኑ በጋራ በጊዜዊ መንግሥታቸ ስም ተሰባስበው የህብረት መግለጫ ካልሰጡ ህዝባዊው ትግል መና ይቀራል፣ የተናጥል ትግል የትም እንደማያደርሳቸው ሊያውቁ ይገባል እንላለን፡፡
(2) በዶክተር አብይ አህመድ ዘመንም ፣ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ መሠረት በኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ
• ‹‹ 707 (ሰባት መቶ ሰባት) ሰዎች መገደላቸው፣
• 1344 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ አርባ አራት) ሰዎች በጥይት ተመተው የአካል ጉዳተኛ መሆናው
• 72 (ሰባ ሁለት) ሰዎች የመታፈናቸውን፣ እንዲሁም
• 23 (ሃያ ሥስት) ባንኮች መዘረፋቸውን የተደበቀ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል፡፡››
በዶክትር አብይ መንግሥት የሁለት አመት በትረ ሥልጣን ዘመን ኦነግ ከኤርትራ ምድር ከነበረው አምስት ሽህ ሽምቅ ተዋጊ ውስጥ አንድ ሽህ ሦስት መቶውን ብቻ ትጥቅ አስፈትቶ፣ ቀሪውን ሦስት ሽህ ሰባት መቶ ሠራዊት ከነትጥቁ አገር ውስጥ በማስገባት የወለጋ ህዝብ በኦነግ ሸኔና አባ ቶርባ ነፍሰ ገዳዬች መከራውን ያያል፡፡ በኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ህዝብ በስብዓዊ ጋሻነት ተይዞል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ምክትል አፈ-ጉባ ዔው አቶ መሃመድ ረሽድ ሃጂ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም….ምናልባትም በራሳቸው በኩል ተጽዕኖ ተደርጎባቸው ካልሆነ በቀር በምክር ቤቱ አባላት የደረሰባቸው ምንም አይነት ጫና እንዳልነበረ ጠቁመዋል። በምክር ቤቱ የሕገ-መንግስትና ማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ አቶ ወርቁ አዳሙ በበኩላቸው ምክር ቤቱ በዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብስባ እንደሚያካሂድ ገልጸው፤ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ይኸው ሊደረግ መወሰኑን ተናግረዋል። ሰኔ 1 እና 2 ቀን 2012ዓ/ም አስተባባሪ ኮሚቴው አምስት አጀንዳዎችን በጋራ ቀርጾ ማጽደቁን፤ አጀንዶዎቹም
(1)ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ፣ ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉም መሠረት የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሺኙ ስጋት ሆኖ እስካለበት ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል፤ እንዲሁም ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ አለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሲያረጋግጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካጸደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው ውሳኔ ያሳለፈው።
መጋቢት 10 ቀን 2010ዓ/ም ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርና የሃገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ኤታማጆር ሹም ሆኖ ሥልጣን ያዘ፡፡ አብይ ያገኘው ህዝባዊው ድጋፍ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ፣ ጠላትና ወዳጅ በአንድነት የጨፈረበት፣ እሳትና ጭድ የታረቀበት፣ ዘይትና ውኃ የተቀላቀለበት፣ የህዝብ ልቦች በአንድነት የጎሰሙበት ቀን ነበር፡፡ የህዝብ ተስፋ ዳግም የለመለመበት፣ ይሄን ለውጥ አይቼ በማገስቱ ብሞት አይቆጨኝም የተባለበት ቀን ነበር፡፡ ህዝቡ ፈጣሪውን በደስታና በሃዘን ያመሰገነበት ያን የተስፋ ቀኑን ማን ይነጥቀዋል፡፡ ወደ ተስፋዋ ምድር ሊያሸጋግረን የሙሴ ብትርን ይዞ ጦርነት፣ርሃብ፣ ስደት፣ አጥፍቶ ብልፅግና ሊያጎናፅፈን ቃል ኪዳን ገባልን፡፡ ታዲያ ሰው በተስፋ መኖርን፣ ተስፋውን እንዴት ይነጠቃል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ቃል የገባህውን ተስፋችንን መልስልን!!! ኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን በሽታ ምክንያት ምርጫ መተላለፉን እና በበሽታውም ምክንያት የአምስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆል፡፡ በዚህም መሠረት ከመስከረም 30 በኃላ የሥልጣን ክፍተት (Power Vacume) ተፈጥሮ ህግ አልባ መንግሥት ይፈጠራል፡፡ በሃገሪቱ ያሉት የፌዴራልና የክልል መንግሥቶች ህገወጥ መንግሥቶች ይሆናሉ፡፡ ሉዓላዊው መንግሥት የህግ ማዕቀፍና ህገ-መንግሥት አይኖረውም፡፡ የህወሓትና ኦነግ ለመቶ ዓመታት ኢትዮጵያን ለመግዛት በርሃ የነደፉት ህገመንግሥት በገዛ እራሱ ተተብትቦ እራሱን ጠልፎ ወደቀ፡፡ አይነኬው!!! ህገመንግሥት…የማይነካውና የማይገሰሰው ህገመንግስት፤ እንደ መለስ ዜናዊ ሞተ፣ እንደ አቡነ ፓውሎስ ሞተ፣ ህገመንግሥቱም ሞተ፣ ተቀበረ፡፡ አዲስ ህገመንግሥት የማርቀቅ እድል ለሁሉም ዜጎች ተፈጠረ፡፡ ለዚህ ነው የህገ መንግሥት ቀውስ በሃገሪቱ አስተዳደር የተከሰተው ስለዚህ መፍትሄው በሕገ መንግሥቱ ማዕቀፍ ሥር ባሉ አማራጮች አይፈታም የፖለቲካ መፍትሔ ብቻ ነው ያለው፣ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የፖለቲካ ውይይት ድርድርና ስምምነት ማድረግ ብቻ ነው መፍትሄው ይላሉ አብዛኛዎቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፡፡ በሌላ በኩል ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 104 እና 105/2 መሠረት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ቀዶ ጥገና በማድረግ ካሉት አማራጮች በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ የማስፈጸሚያ ሥነ ሥርዓት ያለው እና አሁን ለገባንበት አጣብቂኝ ምላሽ የሚሠጥ ሆኖ ተገኝቶል ይላሉ ዶክተሮቹ የብልፅግናና ኢዜማ ፓርቲ መሪዎች፡፡ በሕገ መንግሥቱ ማዕቀፍ ሥር ያሉ አራት አማራጮች፡-(ሀ) በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 60/1 እና 3 መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በትነው በ6 ወር ውስጥ ምርጫ ማድረግ፦(ለ) በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እና ምርጫውን ማራዘም፦(ሐ) በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 83 እና 84 መሠረት የሕገ መንግሥት ትርጉም ከፌደሬሽን ምክር ቤት መጠየቅ፦(መ) በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 104 እና 105/2 መሠረት የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግ፦ የሚሉ አማራጮች በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ የማስፈጸሚያ ሥነ ሥርዓት ያለው እና አሁን ለገባንበት አጣብቂኝ ምላሽ የማይሠጥ ሆኖ ተገኝቶል ይላሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፡፡
(2) በግለሰብና በቡድን ጥያቄዎች ትርጉም፣
(3) በደቡብ ኢትዮጵያ የክልልነት ጥያቄዎች፣ የደቡብ ክልልን በአምስት ክልሎች ስር ለማዋቀር የተደረገው የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ ጥናት በተሳታፊዎቹ ውድቅ ሆኖል፡፡ በህገመንግሥቱ የህዝብ ጥያቄ መሠረት ክልል የመሆን የማንነት ጥያቄ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ ሃምሳ ስድስት ብሄር ብሄረሰብ አካቶ በአንድ ስልቻ ከቶ ለሃያ ሰባት አመታት ይገዛ የነበረው ህወሓት/ ኢህአዴግና፣ ብልፅግና/ኢህአዴግ ለሁለት አመታት በህገመንግሥቱ የተቀመጠውን መብት እንደ ሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የወላይታ፣ ጉራጌ፣ ሆሳዕና፣ ስልጤ ጌዲኦ፣ ሸካ፣ ወዘተ ክልላዊ መንግሥትነት መጠየቃቸው የህገመንግሥቱ ሃገር የመበተን እርግማን ወይም በረከት ሆኖል እንላለን፡፡
(4) ከሕዝብና ቤት ቆጠራ በተያያዘ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መሠረት በኢትዮጵያ ከሕዝብና ቤት ቆጠራ ከምርጫው በኃላ እንዲካሄድ በመወሰን ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጎል፡፡ በዚህም መሰረት ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ውይይት የውሳኔ ሃሳቡን ተቀብሎ በ114 ድጋፍ፣ በአራት ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቋል። ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉም መሠረት የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሺኙ ስጋት ሆኖ እስካለበት ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል፤ እንዲሁም ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ አለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሲያረጋግጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካጸደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው ውሳኔ ያሳለፈው። የዶክተር አብይ መንግሥት ወደ ፍፁም አንባገነንነት መንግሥት እየተሸጋገረ በመሄድ ላይ ለመሆኑ ህዝቡንና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን መናቃቸው ይፋ ወጥቶል፡፡ ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ በፍቃዳቸው ሲያስተላልፉት በሃገረ አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ሁለት ሚሊን ህዝብ የቫይረሱ ተጠቂ ሆኖ ከመቶ አስራምስት ሽህ ህዝብ ሞቶ በኖቨንበር 2020 አጠቃላይ ምርጫ እንደሚካሄድ ዜናውን ማድመጥ ጆሮ ላለው ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች፣ አንደኛ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ተደርጎ፣ ሁለተኛ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት ተበትኖ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር በማድረግ፣ ሦስተኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ብልጽግና ፓርቲ የምርቻውን ጊዜ ሠሌዳ በህብረት እንዲያወጡ፣ አራተኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ፕሮግራማቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ በጋራ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
የዶክተር አብይ መንግሥት በሁለተኛ አመት በትረ ስልጣኑ በሃገራችን ህግና ሥርዓት ባለማስከበር የንፁሃን ደም በግፍ እንዲፈስ አድርጎል፣ ብዙ ህዝብ ተፈናቅሎል፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዘረመል ቤተሙከራ ተገድለዋል፡፡ በሃገሪቱን በወታደራዊ እዝ አገዛዝ (ኮማንድ ፖስት) ስር ትገኛለች:: ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ወዘተ ክልሎች በኮማንድ ፖስት ሥር ወድቀዋል፣ የስብአዊ መብት ጥሰትና የዴሞክራሲ አፋና በህዝብ ላይ ቀጥሎል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና/ ኢህአዴግ መንግስት ለአምኒስቲ ዓለም አቀፍ ድርጅት የኢትዮጵያን የስብዓዊ መብት ጥስት ሪፖርት ዶክተር አብይ አህመድ ድርሰት ነው በማለት ተሳልቆበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ላቀረቡት የስብዓዊ መብቶች ጥሰት ሪፖርት መረዳት የተሳናቸው፣ የፍትህ ሚኒስትሮ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሲያስተባብሉና ሲቃወሙ ተደምጠዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ ሃቁን በይፋ ለህዝብ ገለፀው በዚህም መሠረት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በኦነግ ሸኔ ‹‹ 707 (ሰባት መቶ ሰባት) ሰዎች መገደላቸው፣ 1344 (አንድ ሽህ ሦስት መቶ አርባ አራት) ሰዎች በጥይት ተመተው የአካል ጉዳተኛ መሆናው እንዲሁም 72 (ሰባ ሁለት) ሰዎች የመታፈናቸውን ገለፀ፡፡›› አብይ አህመድ ስለ ሪፖርቱ በፓርላማ በምክር ቤት ላይ ምንም አላሉም፡፡ አዳነች አቤቤም ዝም መፅሃፉም ዝም!!!

ተጨማሪ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 5 ሰዎችም ሕይወት አልፏል
“በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ {1} በዚህም በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2ሺህ 670 ደርሷል። {2} ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 163 ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 1 ሰው የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑ ታውቋል። {3} በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል 117 ወንድና 47 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስክ 92 አመት ነው። {4} ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 104 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 26 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 22 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል እና 1 ሰው ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።{5}በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 5 ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያለፈ ሲሆን 2ቱ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው፣ 3ቱ ደግሞ በሕክምና ማዕከል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል። {6}በዚህም አጠቃላይ በአገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል። {7}የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። {8}በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 33 ሰዎች ( 32ቱ ከአዲስ አበባና 1 ሰው ከአማራ ክልል ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 434 መድረሱን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል። {9}እስካሁን አጠቃላይ 165 ሺህ 151 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።” በየቀኑ ሪፖርት ያቀርባሉ ዶክተር ሊያ ታደሰ፡፡ የካፍያው ጊዜ እንዲህ ያንቀጠቀጠን የዶፉ ጊዜ ብርክ ብርክ እንዳይለን፣ በህብረተሰቡ ህሊና ውስጥ የሞትን ፍርሃት ልናስወግድለት ይገባል እንላለን፡፡ በ1918 እስ 1919እኤአ በስፓኒሽ ፍሉ አምስት መቶ ሚሊዮን ህዝብ በኤችዋንኤንዋን ቫይረስ ተያዘ፣ አንድ ሦስተና የዓለም ህዝብ ቁጥር ነበር፡፡ በበሽታው ህይወታቸው ያለፈው ህዝብ ቁጥር ከ አስራሰባት አስከ ሃምሳ ሚሊዮን ሲገመት እስከ መቶ ሚሊዮን እንደሚደርስና በሰው ልጆች ታሪክ ከፍተኛው ሰው ቸራሽ ተስቦ እንደነበር ታሪክ ያወሳል፡፡ 1918 Flu Pandemic/ Unusually Deadly Influenza Pandemic:-The Spanish flu, also known as the 1918 flu pandemic, was an unusually deadly influenza pandemic caused by the H1N1 influenza A virus. Lasting about 15 months from spring 1918 to early summer 1919, it infected 500 million people – about a third of the world’s population at the time. The death toll is estimated to have been anywhere from 17 million to 50 million, and possibly as high as 100 million, making it one of the deadliest pandemics in human history.
የኦህዴድ/ ኦዴፓ የብልፅግና ፓርቲ ተረኛ አንባገነን መንግሥት በመሆን ይገዛል፡፡ ወደፊት ኢንተርኔት በመዝጋት፣ዴሞክራሲዎ መብቶች በማፈን፣ ብልፅግና የሚያካሂደው ጸረ ዴሞክራሲ ሥራ የጀመረው የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል በማድረግ ሲሆን ‹‹የኮሮናቫይረስ ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ አለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሲያረጋግጥ ይላል የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት (World Health Organization) ኤች አይ ቪ ኤድስ፣ ኢቦላ፣ ሳርስ፣( SARS), ሚርስ (MERS), ዲንጉ ፌቨር (Dengue fever) ኮሮናቫይረስ (COVID-19) ወዘተ በዓለማችን ቫይረስ ይከሰታል ያልፋል፡፡ ኮሮናቫይረስ ለየት የሚያደርገው ቻይና በላብራቶሪ ውስጥ የሰራችው ሰው ሠራሽ ቨይረስ ነው በማለት አሜሪካ ስትከስ በአንፃሩ ቻይና እና የሶብየት ህብረት ደግሞ አሜሪካ የፈበረከችው ሰው ሠራሽ የቤተሙከራ ቫይረስ ነው በመባባል የመካሰሳቸው እንቆቅልሽ ሚስጢሩ ደግሞ ከሰባ በመቶ ጥቁሮችን (ጥቁር አሜሪካኖችን) የጨርስ መሆኑ ትንግርት ነው፡፡ በዓለም የሰው ዘር አዲስ ሥርዓት ተቀይሮል ኮሮናቫይረስ ተከስቶል እሱ ሲያልፍ በሌላ ቫይረስ የመተካቱ ሚስጢር አርቴፊሻል ቫይረስ መቀጠሉ አይቀሬ መሆኑ ተተንብዬል፡፡ የዓለም አቀፍ የጤና ተቋም ሲያረጋግጥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካጸደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ በማለት ነው ውሳኔ ያሳለፈው። ለካ የሥልጣን ጥማት ከውኃ ጥማት የበለጠ ነውና!!!
የእስክንድር ነጋ ‹‹ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ›› ለህዝቡ እርዳታ ለመስጠት የከለከለ መንግሥት፣ ‹‹በአስቸኳይ ምርጫ ይካሄድ ብሎ ህዝብ ሠልፍ ቢወጣ፣ ከመግደል አይመለስም!!!›› ዶክተር አብይ አህመድ ሃቀኛ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ በህዝብ ላይ ጦርነትዎን በማንሳት፣ ለህዝቡ የዴሞክራሲን ጭላንጭል በማሳየት የገቡትን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ‹‹እንከን የለሽ ምርጫ›› ማካሄድ ይጠበቅብዎታል!!! የሰላም ኖቬል ተሸላሚ መሆንዎን አይርሱ፣ ዛሬ ህዝቡ በፖለቲካ ነቅቶል፣ በእርስዎ ዘመን ሌላ ዙር ‹‹ቀይ ሽብር›› እንዳናይ ለፈጣሪ እንፀልያለን!!! ቀይ ሽብር ‹‹መቼም የትም አይደገም!!!›› እንላለን!!!

ምርጫ
(1) የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ምርጫ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ
(2) ‹‹የተጠየቅነው የሕግ ጉዳይ በመሆኑ ሒደቱ ሕግን ብቻ የተከተለ እንዲሆን አድርገናል›› ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ
(3) የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከስራቸው በፍቃዳቸው ለቀዋል
(4) ተጨማሪ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 5 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

Leave a Reply