#ከወለጋው ጭፍጨፋ የተረፉ ነፍሶች አሁንም የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ መሆኑ ተገለፀ! ታሕሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትንን ጨምሮ በተለያዩ የወለ…

#ከወለጋው ጭፍጨፋ የተረፉ ነፍሶች አሁንም የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ መሆኑ ተገለፀ! ታሕሳስ 7 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትንን ጨምሮ በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች ከጭፍጨፍ አምልጠው ጫካ የገቡ አማሮች በርሃብ እየሞቱ መሆኑን የጥቃቱ ሰለባዎች ለአሻራ ተናግረዋል። በክልሉ መንግስት በሚመራው የኦሮሚያ ልዩሃይል እና ኦነግ ሸኔ በወለጋ በተለያዩ አካቢዎች የሚኖሩ በርካታ የአማራ ተወላጆችን ያለእርህራሄ ጨፍጭፏል። በመሆኑም ከጭፍጨፋ አምልጠው በየጫካ የገቡ አማሮች በርሃብ ምክንያት በየጫካው እንደቅጠል እረግፈዋል ሲሉ ምንጮች ለአሻራ ሚድያ ተናግረዋል። በክልሉ ያሉ ከዞን እስከ ወረዳ ያሉ የመንግሰት አመራሮች በተሳተፉበት የአማራን የዘር ማፅዳት ዘመቻ በርካታ አማራዎች ተገድለዋል ያሉ ሲሆን ጠቃሚ የሚሏቸውን ሃብት ንብረቶች በአመራሮች መኪና ሳይቀር እየጫኑ ወስደዋቸዋል። ቀሪዎችን ደግሞ በእሳትእና በከባድ መሳሪያ በመተኮስ አውድመዋቸዋል ብለዋል። አክለውም ሃብት ንብረታችን ወድሟል። ቤተሰቦቻችን ታርደው ለአውሬ ተሰጥተዋል። እባካችሁ ነፍሳችንን አድኑልን። መንገድ ይከፈትልን እንውጣ በማለት በተደጋጋሚ ብንጠይቅም በየቦታው ኬላ በማቆም አንድም አማራ ከወለጋ ምድር በህይወት መውጣት የለበትም የሚል መልስ ሰጥተውናል። ይህን መልስ የሚሰጡን ደግሞ የመንግስት አመራሮች ናቸው ሲሉ ገልፀዋል። በመጨረሻም መረጃ ሰጭዎቹ በምስራቅ ወለጋ አሁንም ሞት እንደቀጠለ ነው። የኦሮሚያ ልዩ ሃይል እና ኦነግ ሸኔ በየቀኑ ከሚጨፈጭፈን በተጨማሪ በርሃብ እና በውኃ ጥም እንደቅጠል እየረገፍነ ነው። እባካችሁ ድምፅ ሁኑን ሲሉ በድጋሜ በሰቆቃ ለአሻራ ተናግረዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24 ፎቶ:- ከፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply