You are currently viewing #ከወለጋ ሰሚ ያጡት ድምፆች! #በወለጋ ሆሮጉድሩ ታግተው የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች በግፍ መረሸናቸው ተነገረ! ታሕሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ  ምስራቅ ወለጋ በሆሩ…

#ከወለጋ ሰሚ ያጡት ድምፆች! #በወለጋ ሆሮጉድሩ ታግተው የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች በግፍ መረሸናቸው ተነገረ! ታሕሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ምስራቅ ወለጋ በሆሩ…

#ከወለጋ ሰሚ ያጡት ድምፆች! #በወለጋ ሆሮጉድሩ ታግተው የቆዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማሮች በግፍ መረሸናቸው ተነገረ! ታሕሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ምስራቅ ወለጋ በሆሩጉድሩ ህዳር 29/2015 ዓ/ም በዘር ተለይተው በኦነግ ሸኔ፣ በኦሮሚያ ልዩ ሃይል እና አጋሮቻቸው ታግተው የቆዩ አማሮች ታህሳስ 11/2015 ዓ/ም በገዳዩ ሃይል መረሸናቸው ታውቋል። ይህ ገዳይ ሃይል ካለምንም ምክንያት አማራ በመሆናቸው ብቻ ማጎሪያ ውስጥ አስገብቶ ብዙ ግፍ እና በደል ሲያደርስባቸው ከቆየ በኃላ ታህሳስ 11/2015 ዓ/ም በግፍ የረሸኗቸው መሆኑን የአሻራ ምንጮች በስልክ ተናግረዋል። በመንግስት ትዕዛዝ እየተንቀሳቀሰ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል እና አጋሮቹ በየቀኑ ዘግናኝ ጨፍጨፋ እያካሄደ ይገኛል ያሉ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በአደባባይ አማሮችን በግፍ ከገደሉ በኋላ ፍፁም ከኢትዮጵያዊነት ሰብዕና ውጭ አስከሬናቸውን ሰብስበው እያደዷቸው ይገኛሉ ሲሉ ምንጮቻችን ብሶታቸውን በእንባ ታጂበው ገልፀዋል። በተጨማሪም በምስራቅ ወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ከጭፍጨፋ የተረፉ አማሮች በኦሮሚያ ልዩሃይል እና ኦነግሸኔ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑ ተገልጿ። በርካቶች በየእስር ቤቱ ተረሽነዋል ብለዋል። በመጨረሻም ሌሎች እገታ ላይ ያሉት አማሮችም ከመረሸናቸው በፊት እባካችሁ ድረሱን ሲሉ ተማፅነዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply