“ከወለጋ ደብረብርሃን በመግባታችን በጣም እድለኛ ነን” ደብረ ብርሃን የገቡ የወለጋ ተፈናቃዮች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ…

“ከወለጋ ደብረብርሃን በመግባታችን በጣም እድለኛ ነን” ደብረ ብርሃን የገቡ የወለጋ ተፈናቃዮች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከ2 ቀን በፊት ደብረብርሃን ነበርኩ አሁን ባለው ከወለጋ ማቆሚያ ካጣው ግድያ ከሞት ተርፈው ሸዋ ደብረብርሃን ከተማ መጠለያ ካምፕ የገቡ ወገኖቻችን ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ተገኝቼ ነበር። ሰው ሁኖ መፈጠር እስከሚያስጠላ ድረስ ዘግናኝ ግፍ የተፈፀመባቸው ወገኖቻችን ከግድያ ከመታረድ ተርፈው ከብዙ እንግልት እና መከራ በማለፍ ደብረብርሃን ከተማ መዳረሻቸውን የሚያደርጉ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የገፈቱ ቀማሾች አሁንም ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። ደብረብርሃን ከተማ ብቻ 6 መጠለያ ካምፕ ያለ ሲሆን ወደ 30,000 /ሰላሳ ሺህ ተፈናቃዮች / የሚገኙ ሲሆን በሰሜን ሸዋ ብቻ 85,000 /ሰማንያ አምስት ሺ ተፈናቃዮች / ይገኛሉ። ቁጥራቸው የሚበዛው ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካማ የሆኑ በእድሜ የገፉ እናት እና አባቶቻችን ናቸው። ሁሉም በሚቻል መልኩ አማራ በመሆናቸው ምክንያት እየተለዩ ጥቃት እንደደረሰባቸው በእንባ ጭምር ይናገራሉ። ለመስማት የሚከብዱ በደል እና ግፍ ተፈፅሞባቸዋል። ይሁን እና ደብረብርሃን መግባታቸው እራሳቸውን እንደ እድለኛ የሚቆጥሩ በርካታ ናቸው። እዛ ያሉት ወገኖቻችን በሞት በመከራ ውስጥ ናቸው፤ ድረሱላቸው ይላሉ። ያሳለፉት መከራ ዘግናኝ ነው፤ ደብረብርሃን እስከሚደርሱ ድረስ በብዙ ፈተና አልፈዋል። በደብረብርሃን እጅግ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ፕላስቲክ ምንጣፍ ላይ መተኛት ከባድ ቢሆንባቸውም “የአይምሮ ሰላም አለን፤ የሚገድለን የለም፤ በሰላም እንተኛለን” ይላሉ። ለእለት ምግብ ቁጥራቸው እጂግ ከፍተኛ ቢሆንም “ጾማችንን አላደርንም፤ የሸዋን የደብረብርሃን ወገኖቻችን ሲኖራቸው አብልተው ሳይኖራቸው አዝነው ይሄዳሉ የከተማውን ህዝብ ከልብ አመስግንልን” ብለዋል። ይሄንን ስቃያቸውን በማየት የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ ወገኖች ቀጥታ ወደ ቦታው በራሳችሁ አማራጭ በመሄድም ሆነ እናንተ በፈለጋችሁት የበጎ አድራጎት አደረጃጀት በኩል የገንዘብም ሆነ የዓይነት/ ምግብ ፍራሽ ብርድልብስ / አስተዋጽኦ ማድረግ እንደምትችሉ አደራ እላለሁ፤ አመሠግናለሁ። ምንጭ:_Yergalem Tadesse ላኮመልዛው

Source: Link to the Post

Leave a Reply