ከወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል ሲገቡ የነበሩ 25 አባወራዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ           አሻራ ሚዲያ      ህዳ…

ከወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል ሲገቡ የነበሩ 25 አባወራዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ አሻራ ሚዲያ ህዳ…

ከወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል ሲገቡ የነበሩ 25 አባወራዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ አሻራ ሚዲያ ህዳር 22/2013 ዓም ባህር ዳር በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም የኦነግ ታጣቂዎች አማራዎችን ብቻ ነጥሎ በመግደልና በማፈናቀል በከፈቱት የጥቃት ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከወለጋ ጉሊሶ ወረዳ መገደላቸውና መፈናቀላቸውን አሻራ ሚዲያ እየተከታተለ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ህዳር 22/2013 ዓ.ም ደግሞ አንድ በካምፕ ውስጥ በእስር ላይ እንገኛለን ያለን ግለሰብ ከቦታው እንደገለጸልን ከአሁን በፊት በተፈጠረው ችግር አካባቢውመን ለቀን ለመውጣት በየጊዜው ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አካባቢው ሙሉ በሙሉ በኦነግ የተከበበ በመሆኑ እስካሁን በጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ለ…መኖር ተገደናል ሲሉ ገልጸው ሰሞኑን በሌሊት ለመውጣት ስንቀሳቀስ ነቀምት ውስጥ የመንግስት አካላት ይዘው ካምፕ ውስጥ አፍነውን ያለ ምንም ምግብና መሰረታዊ ፍላጎት እንገኛለን ብለዋል፡፡ ግለሰቡ ጨምረውም ሀያ አምስት አባወራዎች ከነቤተሰቦቻችን በአንድ አውቶቡስ መኪና እየተጓዝን እያለን ነው ከነ ተሸከርካሪው ዚህ ችግር የተዳረግነው ብለዋል፡፡ በጉሊሶ ወረዳ የነበረንን ከ200 በላይ የቁም ከብት እና በርካታ የቤት እንስሳት ሀብት ንብረት ሙሉ በሙሉ ተዘርፈንና የደረሰ ሰብላችን ጥለን ነው አካባቢውን ለቀን የወጣነው ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ግለሰቡ ጨምረውም በቋንቋችን ምክንያት ብዙ ግፍና በደል ስንቀበል ኖረናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከለታታዮች ከተጎጂ ግለሰቡ ጋር ያደረግነውን ሙሉ የስልክ ቃለ ምልልስ ይዘን የምንቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply