#ከወለጋ_ተፈናቅለው_ደብረብርሃን_ለሚገኙ_ወገኖች_ድጋፍ_ተደረገ! ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በዛሬው ቀን ከወለጋ ከሞት ተርፈው ደብረብርሃን ከተማ ቻይና ካምፕ ለሚ…

#ከወለጋ_ተፈናቅለው_ደብረብርሃን_ለሚገኙ_ወገኖች_ድጋፍ_ተደረገ! ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በዛሬው ቀን ከወለጋ ከሞት ተርፈው ደብረብርሃን ከተማ ቻይና ካምፕ ለሚገኙ ወገኖቻችን የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደርጓል። ✅-100 እስፖንጂ ፍራሽ ✅-100 ብርድልብስ ✅- 18 ኩንታል መኮረኒ ✅-ሩዝ እና ዘይት ድጋፍ ተደርጓል። ለተደረገው ድጋፍ የሲቪል ማህበረሰቦች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ በቦታው ተገኝተው ከልብ አመስግነዋል በተመሳሳይ የደብረብርሃን ከተማ የምግብ ዋስትና ሀላፊ አቶ ግርማ ለተደረገው ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል። ይሁን እና የተፈናቃዮች ቁጥር በደብረብርሃን ከተማ ብቻ 6 መጠለያ ጣቢያ ያለ ሲሆን እስከ 23,000 /ሀያ ሶስት ሺ / ተፈናቃዮች ያሉ ሱሆን በአጠቃላይ በሰሜን ሸዋ ዞን እስከ 80,000 /ሰማንያ ሺ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ይሄንን ችግር በማየት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ ወገኖች በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ በመደገፍ ወገንተኝነታችሁን ታስመሰክሩ ዘንድ የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ያሳስባል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “1000347415891 ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት” ብሎ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል። ስልክ ☎️ +251116661086 0996856611 “የወሎን መልካም እሴት እናስቀጥላለን” የ ወሎ ቤተ አምሐራ – Wello Bete Amhara የልማት እና በጎ አድራጎት ድርጅት ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply