You are currently viewing ከወሎ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ                    መግቢያ የተከበርከዉ የኢትዮጲያ ህዝብ፤የተከበርከዉ የአማራ ሕዝብ ሆይ እንደሚታወቀዉ አማራ በአብሮነት አምኖ ብቻ ሳይሆን ለአብ…

ከወሎ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ መግቢያ የተከበርከዉ የኢትዮጲያ ህዝብ፤የተከበርከዉ የአማራ ሕዝብ ሆይ እንደሚታወቀዉ አማራ በአብሮነት አምኖ ብቻ ሳይሆን ለአብ…

ከወሎ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ መግቢያ የተከበርከዉ የኢትዮጲያ ህዝብ፤የተከበርከዉ የአማራ ሕዝብ ሆይ እንደሚታወቀዉ አማራ በአብሮነት አምኖ ብቻ ሳይሆን ለአብሮነት የሚከፈለውን መሥዋእትነት ከፍሎ ለዘመናት የዘለቀ፤ በኢትዮጵያ ሀገረ ምንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ያለውና ታላቅ ማንነት ያለዉ ሕዝብ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን በዘመናት መካከል ከየአቅጣጫዉ የሚመጡ እና ከራሱ ውስጥ የሚነሱ ቡድኖች አማራውን በጠላትነት ፈርጀዉ ማለትም የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ፈልስፈው ዘርፈ ብዙ ጥቃት ሲያደርሱበት ኖረዋል እያደረሱበትም ይገኛሉ።… የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሠረት እና መሰሶ ጥላቻ ነው፡፡ የዚህ የጥላቻ ፖለቲካ መሲሁ ትህነግ ሲሆን ደቀ መዝሙሮቹ መሥራችና አጋር ድርጅቶች ነበሩ፤ የጥላቻው የስበት ማዕከል ደግሞ እንደብሔር አማራ ነው፡፡ የብሔሮች የውስጥ ባህላዊ ድክመት (ጎጂ ባህሎች)፣ በፖለቲካል ኢኮኖሚ አለማደግ እና አለመሰልጠን በአንድ ብሔር ጨቋኝነት ምክንያት የመጣ ችግር ተደርጎ በፖለቲካ ልሂቃኑ መስማማት ተደርሶበት የርዕዮተ ዓለም መፍለቂያ ቤት ሆኖ ጣራ ለብሶ አምስት አስርት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ትሕነግ የጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎቻችን ላይ ሳይሆን በልዩነቶቻችን ላይ ያተኮረ ፖለቲካ ያራምድ ስለነበር የዜጎችን በጋራ የመልማት ፍላጎትን፣ ሀገራዊ ተቋማት እና ሀገራዊ የጋራ እሴቶቻችንን ከማሳደግ ይልቅ ለእያንዳንዱ ብሔር የእኔ የሚለው ቁስል በመፍጠር እና በማሳመን በፈጠራ ቁስሎች ላይ የተመሰረተ ብሔራዊ ትርክት እና ትርክቱን የትግሉ መሥመር ያደረገ ፖለቲካል ማሕበረሰብ በእያንዳንዱ ብሔር ዉስጥ በመፍጠር በልዩነት ላይ መሠረቱን ያደረገ ፖለቲካን መስርቷል፡፡ የክልሎችን ወያኔያዊ አወቃቀር ብንመለከት እንኳ ዋና ትክክለኛ ዜጎች ያሉበት ክልል፣ ትምክህተኛ እና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ ዜጎች ክልል፣ ጠባብ አሰተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ክልል እና አጋር አካላት ያሉባቸው ክልሎች ነበሩ፡፡ በዚህ ጽንፈኝነት እና ዘረኝነት የተነሳ በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ማህበረሰቡ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ መካረር ውስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡ በሠላማዊ ትግል የሚታገሉ የብሔራዊና ኅብረ ብሔራዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በፖለቲካ አቋማቸው እየታፈኑ ሲታሰሩ እና ሲገደሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ በመቁረጥ ነፍጥ አንገበው ወደበረሀ ወረዱ፡፡ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚኖሩ ልዩ ልዩ ብሔሮች በተለይ አማራው ዘውጌ በሆኑ ጥሙቃነ ትህነግ አመራሮችና አክራሪዎች መፈናቀል፣ መዘረፍ፣ መገደል እና የጅምላ ፍጅት ሲደርስበት ቆይቷል፡፡ የትግራይ ክልል የተለያዩ የአማራ ግዛቶችን በህገ ወጥ መንገድ ወደትግራይ አካሏቸው ነበር፡፡ ስለሆነም ይኽ የጥላቻ ፖለቲካ በሀገራችን የተለያዩ ፍላጎቶችን ማስተናገድ ስላቃተው የለውጥ ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡ እንደሚታወቀው የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያዉያን ጋር በመተባበር ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመዉረር ብሎም ለማፈራረስ ከዉጭም ይሁን ከዉስጥ ከሚሰነዘር ኃይል ሲመክት ኖሯል፡፡ ይሀንን ኢትዮጵያን ወዳድ አቋሙን መሠረት በማድረግ (በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ አንድነት የማይደራደር በመሆኑ) በአንዳንድ የኢትዮጵያን አንድነት ጠል የሆኑ አካላት ተስፋፊ፣ ጨቋኝ፤ በዝባዥ፣ ፊዉዳ ቅኝ ገዢ እና የመሳሰሉት ስሞች ሲሰጡት ኖረዋል፡፡ እንደትህነግ አይነቶቹ ደግሞ ሙሉ በሙሉ አማራ ጠል የሆነ የፖሊቲካ አመለካከት ከመቅረፅ ባለፈ ሌሎች ወንድም ኢትዮጵያዉያን ጭምር ተመሳሳይ አቋም እንዲኖራቸዉ ለረጅም ዘመን ሲወተዉቱ ኖረዋል፡፡ ትህነግ በአንድ ወቅት ጫካ ገብቶ የቀረፀዉ “ትግላችን የአማራ ኢምፔሪያሊዝምን ማስወገድ ነዉ” የሚል የማታገያ ስልት ነድፎ ሲንቀሳቀስ የነበረና በኋላም በኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ድጋፍ ሥልጣን ላይ ሲወጣ ይኽንኑ አማራ-ጠል ትርክት በተግባር በቀረፀዉ ህገ መንግሥት ጭምር በመላ ሀገሪቱ ሲተገብረዉ ኖሯል፡፡ የትህነግ የጭቆና ቀንበር የመረራቸዉ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ህዝባዊና ነዉጥ አልባ (popular nonviolent struggle) ትህነግ ያልለመደዉ አይነት ዘመናዊ ትግል በማድረግ ትህነግን ከሥልጣን ለማባረር በቅተዋል፡፡ ትህነግ በዚህ ህዝባዊ ትግል ሲሸነፍ ወደ መቀሌ በመመለስ ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ትርክቱን በመደስኮር የትጥቅ ትግል ለሁለተኛ ጊዜ አዉጇል፡፡ ስለሆነም በሀገራችን የተስፋፋው ቁስል ሳይሽር ትሕነግ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን (ሰሜን ዕዝን) በመውጓት የአማራና የአፋር ክልሎችን ወሯል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው የህልውና ትግል ጋር ተያይዞ የአማራ ሕዝብ ልጅ የሆነው የአማራ ፋኖ ከተለያዩ የአማራ ግዛቶች በመትመም አሸባሪውን ኃይል በእልህና በቁጭት ተዋግቶታል፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳ ፋኖ የአማራ ሕዝብ ጥንተ ውርስ ቢሆንም በየአካባቢዊ በሚያመች መልኩ የተደራጀ ስለነበርና የተቀናጀ አስተዳደራዊ መዋቅር ስሌለው በሁሉም ወሎ አካባቢ የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች ዉህደት በመፈፀም ይኽን የአማራ ፋኖ አንድነት በወሎ መሥርተናል፡፡ በመሆኑም የአማራ ፋኖ በወሎ የሚከተሉትን ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥተናል። 1. የአገራችን በተለይም የአማራ ህዝብ ከወትሮዉ በተለየ መልኩ የህልዉና ፈተና ላይ መሆኑን በመረዳት ዉስጣዊ አንድነቱን በመጠበቅ በትብብር የሚቃጣበትን የትኛዉም ጥቃት ለመመከት አንድነቱን እንዲያፀና እናሣስባለን። 2. በወሎ ጠቅላይ ግዛት በተለያየ መንገድ በፋኖ አደረጃጀት ፈጥረን ስንቀሣቀስ የነበርን የአማራ ፋኖ በአንድነትና በትብብረ ከሌሎች የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ጋር ለመሥራት እንዲያሥችለንና የትኛዉንም ጥቃት ለመመከት በአንድ ጥላ ስር መሠባሠቡ አስፈላጊ ሁኖ ስለአገኘነዉ “የአማራ ፋኖ አንድነት በወሎ” የሚል የፋኖ አንድነት አደረጃጀት የመሠረትን መሆኑን እያሣወቅን መላዉ ህዝባችን በአባልነት እንዲቀላቀልና አስፈላጊዉን ድጋፍ እንዲያደርግ ስንል እንጠይቃለን። 3. የአማራ ህዝብ ጥንተ ጠላት የሆነዉ ትህነግና ግብረ አበሮቹ በወረራ የያዟቸዉ የአማራ ግዛቶች በአፋጣኝ ነፃ እንዲወጡ እና የማንነት ጥያቄዎች እንዲመለሡ አስቸኳይ ዉሣኔ እንዲሰጣቸዉ እናሳስባለን። 4. የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄያቸዉ የሚመለሡበት፤ የሥነ ልቦና ስብራታቸዉ የሚታከምበት፤ የወደሙባቸዉ ንብረቶች የሚሟሉበትና በአጠቃላይ ወደ ቀደመ ኑሯቸዉ በተረጋጋ መንገድ እንዲመለሡ አስፈላጊ የሆነ የትኛዉንም ህጋዊ ዉሣኔ እንዲሠጠዉ እንጠይቃለን። 5. የአማራ ፋኖ በወሎ የአማራን ህዝብ ደህንነትና ጥቅም ለመጠበቅ ከሚሰሩ ከሌሎች የአገራችንና የአማራ የመንግስትና የፀጥታ ተቋማት ጋር በጋራና በትብብር የምንሰራ መሆናችንን እናሣዉቃለን። 6. ደጀናችንና ጉልበታችን ህዝባችን፤ መሣሪያችን አንድነታችን መሆኑን ተረድተን ፋኖ ለአማራ ህዝብ ቀድሞ የሚገኝና የትኛዉንም በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚቃጣን ጥቃት በግንባር ቀደምትነት የሚመክት በመሆኑ በየትኛዉም ቀጠና ለመዝመት ዝግጁ መሆናችንን እናሣዉቃለን። 7. የተከበርከዉ የአማራ ህዝብ በተለይም በጀግንነትህና በነፃነት ትግልህ የምትታወቀዉ የወሎ ህዝብ ሆይ በየትኛዉም የወሎ አካባቢዎች የአማራ ፋኖ በወሎ ከሚለዉ ዉጭ በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ የትኛዉም ሀይል ፋኖን የማይወክል፤ ለህዝብ አንድነትና ደህንነት ፈተና የሆነ፤ ለመንግስት ስራም እንቅፋት የሚሆን በመሆኑ በእኛም ሆነ በየትኛዉም አካል እዉቅና የሌለዉ መሆኑን እናሣዉቃለን። 8. የአማራ ፋኖን በመምሰልና በተከበረዉ የአማራ ፋኖ ጭምብል ነገር ግን በአላማና በተግባር ከፋኖ የወጣ ከአማራ ፋኖ አባል ያልሆኑ በተናጥልም ይሁን በቡድን የአማራ ህዝብ ኢ- ሞራል የሆኑ እኩይ ተግባር የሚፈፅሙትን የአማራ ፋኖ በወሎ አጥብቆ ያወግዛል።የትኛዉንም በአማራ ፋኖ ስም ከአማራ ፋኖ በወሎ ዕዉቅና ዉጭ ህዝባችን የማይፈልጋቸዉና በህዝባችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ የትኛዉንም ተግባር ከህዝባችን፣ከመንግስትና ከመደበኛ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የምንታገለዉ መሆናችንን እያሣወቅን በቅድሚያ ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ እናሣሥባለን። 9. እኛ የአማራ ፋኖዎች አገራችን ኢትዮጲያ ችግር በሚያጋጥማት ጊዜ ጦረኛና ተዋጊ፤ በሰላሙ ጊዜ የልማት አርበኛ መሆናችን የሚታወቅ በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል ዳር ድንበርንና ህዝባችንን እየጠበቅን ወደ ልማት የምንገባበትን የልማት አማራጮች እንዳዘጋጅልን እንጠይቃለን። 10. መላዉ የፋኖ አባልና የአማራ ህዝብ ሰፊዉ መሬታችንና የተከበረዉ ብዙሀኑ ህዝባችን በጠላት ቁጥጥር ስር መሆኑን በመረዳትና በቀጣይም ተመሣሣይ ወረራና ጥቃት የሚሠነዘር መሆኑን ተረድተን ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እንዲናደርግ ጥሪ እናቀርባለን። 11. የአማራ ፋኖ ለአገር አንድነትና ለህዝብ ክብር ሲል የከፈለዉን ዋጋ በመካድ በአማራ ፋኖ ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች መዋቅራዊ በሚመሥል መልኩ የሚደርሡ ወከባዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ እያሣሠብን በቀጣይ የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ እንዲካሄድ ከሁሉም የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በጋር የምንሰራ መሆናችንን እናሣዉቃለን። ፋኖነት ለኢትዮጲያዊነት ህያዉ ምስክር ነዉ! ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት! ሚያዚያ 10/2014 ዓ.ም ወሎ -ደሴ አማራ ኢትዮጲያ የአማራ ፋኖ በወሎ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply