ከወገኖቻችን ጋር አንዋጋም ያሉ የትግራይ ሚሊሻዎች ለአማራ ክልል ጸጥታ ሀይል እጅ ሠጡ።   አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ…

ከወገኖቻችን ጋር አንዋጋም ያሉ የትግራይ ሚሊሻዎች ለአማራ ክልል ጸጥታ ሀይል እጅ ሠጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ከወገኖቻችን ጋር አንዋጋም ያሉ የትግራይ ሚሊሻዎች ለአማራ ክልል ጸጥታ ሀይል እጅ ሠጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ከምሸቱ በግምት 2 ሠዓት አካባቢ ከወገኖቻችን ጋር አንዋጋም በማለት 29 የሚሆኑ የታጠቁና 8 ጀሌዎች ያሉበት በድምሩ 37 የሚሆኑ የትግራይ ሚሊሻዎች እጅ የሰጡ መሆኑ ተገልጧል። ከዚህ በተጨማሪም የትግራይ ክልል ፓትሮል 3F መኪና እንደያዙ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ አብርጅሀጅራ ከተማ የፀጥታ ሀይሉ ይዟቸው መጥቷል። በዚህም የዞናችን ሁሉም የፀጥታ አካሎች እንዲሁም ተሽከርካሪ የሰጣችሁ ባለኃብቶች፣ ወጣቶች፣ ማህበረሰቦች ለነበራቹህ ተሳትፎ እያመሰገን በቀጣይ ከዚህ የበለጠ አካባቢያችን በንቃት እና በትጋት እየጠበቅን ከፀጥታ አካሉ ጎን በመሰለፍ የተለመደዉን አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እናሳስባለን የሚል መልዕክት የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ተላልፏል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ስለ አንድ ቡድን ፍላጎት ሲባል ወንድም ከወንድሙ ጋር መገዳደል የለበትም በማለት በሰላም ፈቅደውና ወደም እጅ ስለመስጠታቸው በምዕራብ ጎንደር ዞን የሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ እሸቱ ስመኘው ለማረጋገጥ ችሏል። በህወሀት ተደጋጋሚ አፈና ሲደርስባቸው የነበሩ በርካታ የወልቃይት ጠገዴ አማራዎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል። በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሀ ጅራ ነዋሪዎች ትናንት ምሽት ላይ የሚሊሻዎችን ውሳኔ በማድነቅ በተኩስ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የህወሀት የእብሪት አካሄድ በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ ሲፈፅም ከነበረው በደል አልፎ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው ጥቃት የነውረኝነትና የሀገር ክህደት ጥግ ማሳያ በሚል በተለያዩ አካላት መወቀሱ ብሎም በፌደራል መንግስት የአስቸኳይ አዋጅ ታውጆ ወደ አፀፋ ጦርነት የተገባ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ዘገባውን ለማጠናቀር የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ ኮሚዩንኬሽንን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply