ኢንዱስትሪ በአጠቃላይ የኢንዱስትሪዎች ፓርክ ሼድ ስራ 10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አስከትሎል፡፡ ለባህር ማዶ ሃገራት አምስት ኢንቨስተሮች ከ1992 እስከ 2015 እኤአ ቀጥተኛ የባህር ማዶ ኢንቨስትመንት (FDI) አንደና ቱርክ በ22.3 ቢሊዮን ብር 163 ፕሮጀክቶች፣ ሁለተኛ ቻይና በ14.5 ቢሊዮን ብር 814 ፕሮጀክቶች፣ ሦስተኛ ህንድ በ7.1 ቢሊዮን ብር 322 ፕሮጀክቶች፣ አራተኛ አሜሪካ 1.1 ቢሊዮን ብር 235 ፕሮጀክቶች፣ አምስተኛ ሱዳን በ805 ሚሊዮን ብር 373 ፕሮጀክቶች፣ በአጠቃላይ በ46 ቢሊዮን ብር መዋለ-ንዋይ በማፍሰስ 1,907 ፕሮጀክቶች ገንብተዋል፡፡ ኢንቨስተሮቹ ለፋብሪካና ለመኖሪያ ግንባታ ከ60 እስከ 80 አመታት የሚቆይ የመሬት ሊዝ ስምምነት ተሰጦቸዋል፡፡ ( Land lease term: 60-80 years at nominal rate for factories & residential quarters) የኢንቨስትመንቱ ወጪ በ46 ቢሊዮን ብር ሲሆን አንድ ዶላር በ27 ብር ብናሰላው 1 ቢሊዮን 700 ሚሊየን ዶላር መዋለ-ንዋይ የፈሰሰበት ሲሆን አጠቃላይ የኢንዱስትሪዎች ፓርክ ሼድ የግንባታ ስራ 10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ መውጣቱ የሚያሳየው በጥናት ላይ ያልተመሠረተ ኢንቨስትመንትና በሙስና የተዘረፈ ገንዘብ ምንተፋ እንዳለበት ወደፊት ይፋ ይሆናል፡፡ የኢንዱስትሪዎች ፓርኮች በሃገር በቀል ኢንቨስተሮች በግሉ ዘርፍ ሊሰራ ይችል የነበሩ፣ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች፣የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ(ጫማና ጎንት)፣ የታሸጉ ልዩ ልዩ ምግቦችና መጠጦች፣ ለሱፐር ማርኬቶች፣ መድሃኒቶች፣ ሳሙናና ቅባት ነክ ምርቶች እንዲሁም ኬሚካል፣ ፋርማሲዩቲካልና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ የመሳሰሉት በግሉ ዘርፍ በሃገር ውስጥ ባለሃብት ሊሰሩ ይችሉ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ የ2010 ዓ/ም በጀት እቅድ መሠረት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እቅድ 997 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን የእቅዱ አፈፃፀም ግን 487.5 ሚሊዮን ዶላር ማለትም 57.8 በመቶ ሆኖል ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪ ዞኖች ድርሻ አናሳ በመሆኑ አልተገለፀም፡፡ ከኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ግን ኢምንት ነው፡፡ የኢንዱስትሪ ዞኖች ሼዶች ግንባታ ወጪ ቆሞ የገቢ ንግድ የሚተኩ ኢንዱስትሪዎች (Import Substitution Industrialization (ISI) መተካት ይኖርባቸዋል እንላለን፡፡ ከውጪ የሚገቡ የፍጆታ እቃዎችን በማቆምና በሃገር ውስጥ አምርቶ በመተካት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በሰሊጥ ምርታችን የዘይት ፋብሪካ በማቆቆም ምርቱን በሃገር ውስጥ በማከፋፈል የውጭ ምንዛሪ ማዳንና ለብዙ ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር ይቻላል፡፡ በአዲሱ ለውጥ የኢንዱስትሪዎች ፓርኮች ቱሩፋትና ግድፈት ተጠንቶ ይቅረብ፡፡
FDI to date- illustrates the top 5 countries investing in Ethiopia (since August 22, 1992-April 02, 2015) summary of licensed foreign direct investment projects by country of origin: no of projects and tot capital in 000br
No | Country of Origin | Tot No of Projects | Tot Capital in ‘000’ Br |
1 | Turkey | 163 | 22,325,174 |
2 | China | 814 | 14,531,756 |
3 | India | 322 | 7,177,924 |
4 | USA | 235 | 1,192,791 |
5 | Sudan | 373 | 805,083 |
Total | 1,907 | 46,032,728 |
የኢትዩጵያ መንግስት ኢንደስትሪያል ዞኖች ልማት ኢንቨስተሮች የሚሠጣቸው ልዩ ልዩ ማበረታቻና የሚያሞላላቸው የመሠረተ-ልማት በተመለከተ፡–
{1} የኢትዩጵያ ኢንደስትሪያል ዞኖች ኢንቨስተሮች ከ8 እስከ 10 አመታት የገቢ ግብር አይከፍሉም፡፡ {2} ኢንቨስተሮቹ ከባህር ማዶ ሃገራት የሚያስገቦቸው የታክስ ቀረጥና ሌሎች ታክሶች እንዳይከፍሉ በማበረታታት ከገቢ ንግድ ከሚያስገቡት ካፒታል ጉድስ (የፋብሪካ ማሽኖች)፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ መለዋወጫ እቃዎች 15 በመቶ ከካፒታል ጉድስ ምህረት የንግድ ፍቃድ ካወጡ በኃላ፣ የውጪ ንግድ ምርት ለመላክ የሚያገለግሉ የጥሬ ዕቃዎች ግብዓቶችና መገልገያ መኪናዎች ከቀረጥ ነፃ የማስገባት መብት አላቸው፡፡ {3} በአንድ መስኮት ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎቶች ኢንደስትሪያል ዞኖች ግቢ ውስጥ ሰርቪስ ያገኛሉ፡፡ {4} ኢንደስትሪያል ዞኖች ኢንቨስተሮች፣ የውጪ ዜጎች የሰው ኃይል የሥራ ፍቃድና የመኖሪያ ፍቃድ ሠርተፊኬት ይሞላላቸዋል፡፡ {5} ኢንደስትሪያል ዞኖች ኢንቨስተሮች የካስተም አገልግሎት የገቢ ንግድ ጥሬ እቃዎች የትራንስፖርት አገልግሎት
{6} ኢንቨስተሮቹ ኤክስፖርት የሚያደርጉት ምርቶች የግብር ታክስ ያለመክፈል ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ {7} ኢንደስትሪያል ዞኖች ልማት ኮርፖሬሽን ለኢንቨስተሮች ብዙ ሄክታር መሬት ለኢንድስትሪ ዞኖችን ከሊዝ ኪራይ ነፃ ቦታ ይሰጣል፡፡ {8} በኢንዱስትሪል ፓርኮች ኮንትራት ስምምነት መሠረት ሼድ ሬንት (ኪራይ)፣ ፓርክ ኦፕሬሽን ኤንድ ማኔጅመነንት ኮንትራት (የፓርክ ኦፕሬሽንና የአስተዳደር ኮንትራት ውል)፣ ዜሮ ሊኪውድ ዲስቻርጅ (ዜሮ የፈሳሽ ፍሰት አስተዳደር) እና ሲወሬጅ ስርቪስ (የፍሳሽ አገልግሎትን) ጭምር ያካትታል፡፡ {9} የባንክ ብድር ይመቻቻል፡፡ {10} የታክስና ቀረጥ የማንሳት ማበረታቻ በ769/2012 እኤአ በወጣው አዋጅ ተደንግጎል፡፡ {11} የኢትዩጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት 20 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ለኢንደስትሪያል ዞን ያቀርባል፡፡ {12} የኢትዩጵያ ውሃና ፍሳሽ ልማት አገልግሎት 10,000 ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በቀን ለኢንደስትሪያል ዞን ያቀርባል፡፡
{2} Incentives applicable to industrial parks
{2.1} Manufacturers: Exempted from income tax up to 8 – 10 years / Exempted from duties & other taxes on imports of capital goods, construction materials, spare parts with a value of 15% of capital goods after business license, raw materials for the production of export commodities & vehicles / One-stop government services within the Parks premises / Loss carry forward (for half on income tax exemption of period granted) / Land lease term: 60-80 years at nominal rate for factories & residential quarters / Expedited procedure of securing entry, work permit and certificate of residency for expatriate personnel working in industrial Parks and their dependents / Customs facilitation – transport of imported raw materials straight from customs post to factory through bonded export factory scheme / Investors also benefit from no taxes on exports
{2.2} Developers: Exempted from income tax up to 15 years (outside Addis Ababa) / Exempted from duties & other taxes on imports of capital goods, construction materials, spare parts, 15% of capital goods after business licence, raw materials & vehicles / Provision of essential infrastructure, including dedicated power substations / One-stop government services within the Parks premises / Land lease term: 60-80 years at nominal rate for factories & residential quarters
{2.3} Services available in industrial Parks/ One –stop-shop (on site and in EIC’s HQ in Addis abeba) / One site dedicated fire prevention and protection / Waste treatment / Facilitation and after care / Park security / Cafeteria banking & other common services / Custom clearance service for imported raw materials & exported products
በዓለማችን የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ታሪካዊ አመጣጥ፣ፍችና ዓይነቶች
በኢምሊ ሮሃን በቀረበ ጥናት መሠረት የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ፍች፣ዓይነቶችና ታሪካዊ አመጣጥ በአጭሩ ለመቃኘት እንሞክራለን፡፡የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አጠቃቀም ከኢኮኖሚ ምክንያቶች ጋር በተነሳ የረዥም ግዜ ማለትም በ1704 እኤአ በጅብራልተር ውስጥ፣ በ1819 እኤአ በሲንጋፖር ውስጥ በንግድ ትስስር ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ በ1920 እኤአ በስቴን ውስጥ የመጀመሪያው ማን-ፋክቸሪንግ ዞን ማን-ፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ መሠረቱን ያደረገ ተመስርቶ ነበር፡፡ ምንም እንኮን፤የዛሬዎቹን ዞኖች ንድፍና አላማዎች በመዳሰስ የሻኖን ኤክስፖርት ፕሮሰሲንግ ዞን በአየርላንድ በ1958 እኤአ ውስጥ ተቆቆመ ‹የዞኖች እናት› በመባል ይታወቅ ነበር፣ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተስፋፋው ከዛን ዘመን ጀምሮ ነበር፡፡ የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እድገት እየጨመረ ሄደ፣ ዛሬ የተለያዩ የዞኖች ዓይነቶች ከትንሽ የንድፍ ልዩነትና አላማ በአለማችን ላይ ተግባራዊ ሆነዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለመጥቀስ {1} ነፃ የገበያ ዞኖች፣ {2} ኤክስፖርት ፕሮሰሲንግ ዞኖች፣ {3} ኢንተርፕራይዝ ዞኖች፣ {4} ፍሪ ፖርትስ፣ {5} ሲንግል ፋክተሪ ኤክስፖርት ፕሮሰሲንግ ዞኖችና {6} ልዩ ዞኖች በመባል ይታወቃሉ፡፡ በአንድ አገር ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ሲመሰረቱ ዋነኛ አላማዎችና ጠቀሚታዎች ውስጥ የሚጠቀሱት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ውስጥ መግባት፣ ለሃገሬው ሰው የስራ እድል መፍጠር፣ የሙያ ክህሎትና የቴክኖሎጅ ሽግግር፣ የገቢ ምንጭና ልዩ ልዩ ጥቅሞች፣ የተሸሻለ ምርትና ሸቀጣ ሸቀጥ ለውጭ ንግድ ማቅረብ፣ውጭ ምንዛሪ ማስገኘት ይኖርበታል፣
Special Economic Zones: A tool for development or for a “race to the bottom”
Before exploring the debate of SEZs as tools for development, a short note on the history, definition and types of Zones is provided. The usage of special Zones for economic reasons has a long tradition, starting as early as 1704 in Gibraltar and 1819 in Singapore. These early Zones were geared towards facilitating trade, while the first manufacturing-based zone was established in Spain in the 1920’s. However, considering the design and aims of Zones of today, the Shannon EPZ (Export Processing Zone) in Ireland, established in 1958, can be considered the “mother of Zones”, as it became instrumental in spreading the knowledge about SEZs globally (FIAS 2008, Aggarwal 2010 and Bolin 2004). The practice of SEZs have developed over time, and today a variety of different zone types with slightly different design and aims are implemented globally. These include Free Trade Zones, Export Processing Zones, Enterprise Zones, Free Ports, Single Factory Export Processing Zones and Specialized Zones (see FIAS 2008 for a discussion of the features of the different Zones types).
The area usually employ liberal and flexible policies in order to attract FDI, to promote non-traditional exports and to generate foreign exchange earnings, employment, income, and spillover benefits, including learning by locally owned firms (see e.g. World Bank 1992, UNCTC/ ILO 1988 and FIAS 2008). Within the general definitions of SEZs, a further distinction of three different types of Zones can be identified: 1) Export focused enclave Zones with little integration with the host economy 2) Zones as a testing-ground for liberal policies and 3) Zones as a policy tool within a broader economic reform.
የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ጥቅሞች፣ Defining Zone Benefits and Costs;-The economic benefits from zone development are both static and dynamic. The static benefits are quite straightforward and include: {I} የስራ እድል መፍጠርና የገቢ ማስገኛ (Direct employment creation and income generation){2} የውጪ ንግድን ማሳደግና የውጪ ንግድ ዘርፎችን ማስፋፋት Export growth and export diversification) {3} የውጪ ምንዛሪ ገቢ ማሳደግ (Foreign exchange earnings) {4} ቀጥተኛ የውጪ መዋለ-ንዋይ መሳብ (Foreign direct investment) {5} የመንግስት ገቢን ማሳደግ (Government revenues) የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ተግባራዊ ጠቀሜታ በደሃ አገሮች ለዜጎች የሥራ እድል መፍጠር፣የውጪ ምንዛሪ ገቢዎችን መጨመርና የመንግስትን ገቢ ከፍ ማድረግ ዋናዎቹ ጥቅሞች ናቸው፡፡ ይሄም የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ከተቆቆሙ ጀምሮ ያስገኙት ጥቅም በየአመቱ በማስረጃ ተደግፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች በሰው ኃይል ልማት ላይ ያስገኘው ጠቀሜታ ለመለካት ቢያዳግትም በረጅም ግዚያት ውስጥ አስተዋፅኦውን መገምገም ይቻላል፡፡
በሰው ኃይል ልማት የሚካተቱት ጠቄሜታዎች መኃል፤-{1} ቀጥተኛ ያልሆነ የስራ እድል ፈጠራን ከፍ ማድረግ (Indirect employment creation) {2} የሙያ ክህሎትና ሥልጠና ማሳደግ (Skills upgrading){3} የሴቶች የስራ ዕድል መጨመር (Female employment) {4} የቴክኖሎጅ እውቀት ሽግግር መኖር (Technology transfer) {5} የልምድ ልውውጥና ልዩ የስራ ልምድን ማዳበር(“Demonstration effect” arising from application of “best practices”) {6} የክልሎች ኢኮኖሚያዊ የተስተካከለ እድገት መፍጠር (Regional development) በኢትዩጵያ የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ጠቀሜታን በየአመቱ ምን ጥቅምና ጉዳት አስገኙ ብሎ መረጃ ማቅረብ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ለዜጎች ብልፅግና ተጨባጭ ትርጉም ይኖረዋል፡፡ከለበለዛ ምንም ፋይዳ አይኖረውም፡፡
{I} የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስም የመሬት ወረራ፣ለኢንድስትሪ ዞኖችን 5130 ሄክታር መሬት ቦታውን ተረክበው 50 ፋብሪካዎች ለመገንባትና አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ለማስፋፋት ታቅዶል፡፡ከቦታው ላይ፤ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪያል ዞን 157 ሄክታር ሲዘጋጅ ከቦታው ላይ 180 አባ ወራዎችና እማ ወራዎች እስካሁን ተፈናቅለዋል፡፡ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ሁሉን አቀፍ የልማት እቅድ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስአበባ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ሁሉን አቀፍ የልማት እቅድ ለኢትዩጵያ ህዳሴ በሚል የሚታወቀው መንግስታዊ አካል፤ 234 ፋብሪካዎች ከመዲናዋ ክልል ውጭ አዲስ የማኑፋክቸሪንግ ኢንድስትሪ ዞን እንዲገነቡ ለማድረግ በዝግጁት ላይ መሆኑ አስታውቆ ነበር፡፡ በአዲስአበባ የሚገኙ ኢንድስትሪዎች በቁጥር 18 የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ፣132 የብረትና አልሙኒየም ፋብሪካዎች፣44 የምግብና የመጠጥ ፋብሪካዎች፣27 የኬሚካልና የትንባሆ ፋብሪካዎች እንዲሁም 13 የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካዎች እንደሚገኙ ታውቆል፡፡ የከተማው ማስተር ፕላን መሠረት እነዚህን ፋብሪካዎች ከአዲስ አበባ ከተማ በማስወጣት የከተማዋን ዓየር ንብረት ለመጠበቅ ታልሞል፡፡ በድራፍት ረቂቁ መሠረት ሁሉን አቀፍ የኢንዱስት ፓርኮችና፣ልዩ ዞኖች በሞጆ ደረቅ ወደብ አቅጣጫ ለመገንባት ታቅዶል፣ ወደ ጠጂ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ፣ ወደ አዲሱ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ እንዲሁም ዘመናዊ አዲስ አበባ አዳማ የተገነባው የመኪና መንገድ አቅጣጫ ፋብሪካዎቹን ለመትከል አቅደው ነበር፡፡ የነዋሪውን ህዝቡ ይሁንታ ግን አላገኘም፡፡
{II} ለኢንድስትሪ ዞኖችን የፈጠረው የሥራ ዕድል የተጠበቀውን ያህል አይደለም፣ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መረጃ መሠረት፡-
- በኢትዮጵያ የሰው ኃይል ልማት በመካከለኛና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በ2007/8 ዓ/ም 380,000 ሽህ የነበረ ሲሆን ከአጠቃላዮ የሃገሪቱ የሰው ኃይል 0.9 በመቶ ይሸፍን ነበር ፡፡ በ2012/13 ዓ/ም 757,600 ሽህ የሚሆን ሲሆን ከአጠቃላዮ የሃገሪቱ የሰው ኃይል 2 በመቶ ይሸፍናል ተብሎ ይገመታል፡፡
- በኢትዮጵያ የሰው ኃይል ልማት በግብርናው ዘርፍ በ2007/8 ዓ/ም 31,752,000 ሚሊዩን የነበረ ሲሆን ከአጠቃላዮ የሃገሪቱ የሰው ኃይል 74 በመቶ ይሸፍን ነበር ፡፡ በ2012/13 ዓ/ም 33,371,573 ሚሊዩን የሚሆን ሲሆን ከአጠቃላዮ የሃገሪቱ የሰው ኃይል 68 በመቶ ይሸፍናል ተብሎ ይገመታል፡፡
{III} ኢንደስትሪያል ዞኖች ከጁቡቲ ወደብ 800 እስከ 1200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ ተጨማሪ የትራነስፖርት ውጪ ስላለው በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ በርካሽ ሽጦ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለውም፡፡ ከሠንጠረዡ ላይ የኢንደስትሪያል ዞኖች ከጁቡቲ ወደብ ያላቸውን ርቀት አስተውሉት፡፡
{IV} ለኢንድስትሪ ዞኖች ለጥሬ እቃዎች ግብዓት የሚያስፈልጉ የውጭ ምንዛሪ ጥያቄዎች በርካታ ስለሆነ፣ በውጭ ንግድ ያስገኛሉ የተባለው የውጭ ምንዛሪ የተጠበቀውን ያህል አለመሆኑ በጥናት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በቻይና፣በህንድ፣ በቱርክ ወዘተ ኢትዩጵያ ውስጥ የሚቆቆሙ ኢንደስትሪያል ዞኖች ግብአቶች/ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎች፣ መለዋወጫ፣ ወዘተ ከውጪ ሃገራት ተገዝተው የሚመጡ በመሆናቸው የውጪ ምንዛሪ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የፋብሪካዎቹ ምርቶችም አነስተኛ ተጨማሪ እሴት ብቻ ነው የሚፈጥሩት በአጠቃላይ እንኮን የውጪ ምንዛሪ ገቢ ማሳደግ ይቅርና ለራሳቸውም የውጪ ምንዛሪ ጠያቂና ጥገኞች ናቸው፡፡ 1)የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የሰው ኃይል ልማት በተመለከተ፣ የኢንደስትሪና የስልጠና ክህሎት አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ 2) የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የፖሊሲ ለውጦች አገር አቀፍ ለውጥ አማጭ አለመሆን፣ 3)ኢንደስትሪያል ዞኖች የተሳሳተ ቀጥተኛ የውጪ መዋለ-ንዋይ በመሳብ ዝቅተኛ ቴክኖሎጅ፣አነስተኛ የሙያ ክህሎትና ምንም ተቆጣጣሪ የሌለው እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡4) የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ለሴት ሰራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ክፍያ ያደርጋሉና ልዩነት ያደርጋሉ፡፡ 5) ኢንደስትሪያል ዞኖች መሰረታዊ የሠራተኞች መብት ይጥሳሉ፣የሠራተኛ ማህበራትን መደራጀት ያግዳሉ፣ዝቅተኛ ደሞዝ ይከፍላሉ፣የህክምና አገልግሎት አይሰጡም ወዘተ 6) የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ካንፓኒዎች ለሠራተኞቻቸው ተስማሚ ያልሆነ የሥራ ቦታ፣የጤንነት አጠባበቅ፣የደህንነት ሁኔታ አጠባበቅ አመቻቹም፡፡ 7) የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የከባቢ አየር ሁኔታና የአካባቢ ብክለትን የመከላከል ስልት የላቸውም፡ 8) የኢንደስትሪ ፓርኮች ግንባታ ለሃገሪቱ ዜጎች የሚያበረክተው የቴክኖሎጂ ሽግግር ምን ድረስ እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ከህንድ፣ ከቻይና ፣ከቱርክ፣ወዘተ ሃገሮች ተነቅለው የመጡ አገልግሎታቸውን የጨረሱ ፋብሪካዎች ምን ያህል ዘለቄታዊ ጥቅም ብዙ ሠራተኛ በመቅጠር፣ በውጭ ንግድ አስተዋፅኦ፤ በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ ወዘተ አገራችንን ይጠቅማሉ፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሚ የሆኑ ደሃ አገራት ያገኙት ጥቅም በጥናት ተደግፎ ቢገለፅ የኢንደስትሪ ፓርኮች ግንባታ በኢትዩጵያ አሳማኝ በሆነ ነበር፡፡ የኢንደስትሪ ፓርኮች ግንባታ ነዋሪዎችን ያፈናቅላል፣ መንግስት ለሃገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ዌም በአክሲዮን ህዝብ የሚገዛቸው የማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪዎች ባለቤትነት ቅድሚያ አልተሰተም!!!
የኢትዩጵያ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ(2008-2012ዓ/ም)፣ ( Growth and Transformation Plan (GTP)2015/16-2019/20)
በሚያዝያ ወር 2007 እኢአ የቻይና ግዙፉ ኩባንያ ሁጃአን( Huajian) የቻይና የቆዳ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ134 ሄክታር መሬት ላይ የኢንድስትሪ ዞን ለመገንባት የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡ ሁጃአን የቆዳ ፋብሪካ ምርቶች ውስጥ ጫማ፣ጎንት፣ቦርሳና የቆዳ ውጤቶች ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኩባንያው ከራሱና ከቻይና ልማት ባንክ የግንባታ ወጭውን ተበድሮ እንደሚሰራ ገላፆል፡፡
በሌላ በኩልም የታይዋኑ ግዙፍ ኩባንያ የሆነው ጆርጅ ሹ ቦሌ ለሚ አካባቢ በገነባው ፋብሪካ በቀን 3000 ጥንድ ጫማዎች በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ጆርጅ ሹ በሞጆ ከተማ 50 ሄክታር መሬት ተረክቦ አዲስ የኢንደስትሪ ዞን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ኩባንያው ጫማ፣ ያለቀለት ቆዳ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የግንባታው ወጭ 600 ሚሊዩን ዶላር ሲገመት ከአራት አመት በኃላ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡መንግስት ከቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፍ በ2007 እኢአ መጨረሻ የሚጠብቀው የውጭ ንግድ ገቢ 500 ሚሊዩን ዶላር ቢሆንም በስድስት ወራት የተገኘው ገቢ 65 ሚሊዩን ዶላር በታች መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ሲጠናቀቅ ከቆዳኢንደስትሪ ዘርፍ 800 ሚሊዩን ዶላር የማግኘት ዕቅድ ነድፎል፡፡ የኮሪያ ልማት ኢንስቲትዩት አማራሪዎች የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የኢንደስትሪ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ላይ የኢትዩጵያ መንግስት ዝቅተኛ ትኩረት እንደሰጠው በጥናታቸው በማስረጃ አጋልጠዋል፡፡ በኢንደስትሪው ዘርፍ በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዝቅተኛ የኤክስፖርት (የውጭ ንግድ) አፈፃፀም በ2007 ዓ/ም መጨረሻ መንግስት ለማግኘት ያቀደው የገቢ መጠን አንድ ቢሊዩን ዶላር ነበር፡፡ ሆኖም ከዕቅዱ እጅግ በመራቅ ከ200 ሚሊዩን ዶላር በታች ገቢ ተመዝግቦል፡፡ በዚህ ዘርፍ ላይ የተደረገው ኢንቨስትመንት ዝቅተኛ መሆኑም ለኢንደስትሪው ዝቅተኛ ዉጤት ምክንያት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
- በቆዳና ቆዳ ዉጤቶች መስክም ዝቅተኛ ዉጤት መመዝገቡን ኮርያውያኑ በጥናታቸው አረጋግጠዎል፡፡ መንግስት ለማግኘት ያቀደው የገቢ መጠን ግማሽ ቢሊዩን ዶላር ነበር፡፡ ሆኖም ከእቅዱ በታች150 ሚሊዩን ዶላር ብቻ ገቢ ተገኝቶል፡፡
- የብረታ ብረት ኢንደስትሪም ዘርፍ አገሪቱን ጫና ውስጥ መክተቱ በጥናታቸው አረጋግጠዎል፡፡ በሃገሪቱ በርካታ የብረታ ብረት ውጤቶችከውች በገፍ እየገቡ መሆናቸው የአገሪቱ የንግድ ሚዛን ጉድለት እንዲባባስ አድርጎል በማለት ተችተዋል፡፡
- በኢትዮጵያ የ2010 ዓ/ም በጀት እቅድ መሠረት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እቅድ 997 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን የእቅዱ አፈፃፀም ግን 487.5 ሚሊዮን ዶላር ማለትም 57.8 በመቶ ሆኖል ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪ ዞኖች ድርሻ አናሳ በመሆኑ አልተገለፀም፡፡
የኢንዱስትሪ ዓይነቶች፤
የፍጆታ እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎች፣ Consumer Goods Producing Industries በኢንደስትሪያል ዞኖች የሚቆቆሙት ፋብሪካዎች በሙሉ የፍጆታ እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎች ናቸው፡፡ ልብስና አልባሳት ነክ ምርቶች፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ምግብ የታሸጉ ልዩ ልዩ ምግቦችና መጠጦች፣ ለሱፐር ማርኬቶች፣ እህል፣ መድሃኒቶች፣ ሳሙናና ቅባት ነክ ምርቶች እንዲሁም ትንባሆ/ሲጋራ፣ ሲሚንቶ፣ ሜታልና ኢንጅነሪንግ፣ ኬሚካል፣ ፋርማሲዩቲካልና አግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ የመሳሰሉት የእለት ተዕለት አላቂ እቃዎች የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ናቸው፡፡ በኢንደስትሪያል ዞኖች የሚቆቆሙት ፋብሪካዎች በሙሉ የፍጆታ እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎች በመሆናቸው በሃገሪቱ መሠረታዊ ለውጥ አያመጡም፡፡
የካፒታል እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎች፣ Capital Goods Producing Industries የፍጆታ እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎችን፣ የሚሠሩት የካፒታል እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎች ፋብሪካዎች ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለምሳሌ፣የሲሚንቶ ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ የቢራ ፋብሪካ፣ የስካÿር ፋብሪካ፣ የመኪና ፋብሪካ፣ የትራክተር ፋብሪካ፣ የጀነሬተር ፋብሪካ፣ የኤሌትሪክ ቆት፣ ኮንፒውተር፣ ሞባይል፣ የባቡር ፋብሪካ፣ የአይሮፕላን ፋብሪካ፣ የመርከብ ፋብሪካ፣ የታንክ ፋብሪካ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ግዙፍ የኢንደስትሪ ፋብሪካዎች መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጡ የአንድ ሃገርን ኢንደስትሪ እድገትን ከስር መሰረቱ መቀየር የሚችሉ ኢንደስትሪዎች ሲሆኑ ብዙ ሽህ ሠራተኞች፣ ካፒታል፣ ልዩ ልዩ ግብአቶችን በመጠቀም በዓለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪ የሆኑ የፍጆታ እቃዎች አምራቶች ፋብሪካዎችን ለዓለማችን በመሸጥ ከፍተኛ ትርፍ ያገኛሉ፡፡፡ ይህ ዓይነት አንድ የካፒታል እቃዎች አምራች ኢንደስትሪ ፋብሪካ ኢትዩጵያ ውስጥ የለም፡፡ በኢንደስትሪያል ዞኖች የሚቆቆሙት ፋብሪካዎች በሙሉ የፍጆታ እቃዎች አምራቶች ኢንደስትሪዎች በመሆናቸው በሃገሪቱ መሠረታዊ ለውጥ አያመጡም፡፡
የኢንደስትሪ ፓርኮች ግንባታ ለሃገሪቱ ዜጎች የሚያበረክተው የቴክኖሎጂ ሽግግር ምን ድረስ እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ከህንድ፣ ከቻይና ፣ከቱርክ፣ወዘተ ሃገሮች ተነቅለው የመጡ አገልግሎታቸውን የጨረሱ ፋብሪካዎች ምን ያህል ዘለቄታዊ ጥቅም ብዙ ሠራተኛ በመቅጠር፣በውጭ ንግድ አስተዋፅኦ፤ በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ወዘተ አገራችንን ይጠቅማሉ፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሚ የሆኑ ደሃ አገራት ያገኙት ጥቅም በጥናት ተደግፎ ቢገለፅ የኢንደስትሪ ፓርኮች ግንባታ በኢትዩጵያ አሳማኝ በሆነ ነበር፡፡ የኢንደስትሪ ፓርኮች ግንባታ ነዋሪዎችን ያፈናቅላል፣ መንግስት ለሃገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ቅድሚያ ለምን አይሰጥም!!!
የገቢ ንግድ የሚተኩ የኢንዱስትሪዎች (Import Substitution Industrialization (ISI)
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ግንባታ ቆሞ ቀሪው ገንዘብ የገቢ ንግድ የሚተኩ የኢንዱስትሪዎች (Import Substitution Industrialization (ISI) ላይ ቢውል የተሸለ ይሆናል የሚል እምነት አለን ይሄንንም የምጣኔ ኃብት ጠበብት በአጭር ጊዜት ውስጥ አጥንተው እንዲተገብሩ ዶክተር አብይ አህመድ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ወደ ተሸለ ውጤት ማምጣት ይቻላል እንላለን፡፡Import Substitution Industrialization (ISI) is a trade and economic policy which advocates replacing foreign imports with domestic production. ISI based on the premise that a country should attempt to reduce its foreign dependency through the local production of industrialized products.
የባህር ማዶ ምርቶች፣ ከዚህ ውስጥ ልዮ ልዮ መጠጦች፣ ልብስና አልባሳት ነክ ምርቶች፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ምግብ የታሸጉ ልዩ ልዩ ምግቦች ለሱፐር ማርኬቶች፣ እህል፣ መድሃኒቶች፣ ሳሙናና ቅባት ነክ ምርቶች እንዲሁም ትንባሆ/ሲጋራ፣ ሲሚንቶ፣ ሜታልና ኢንጅነሪንግ፣ ኬሚካል፣ ፋርማሲዩቲካልና አግሮ ፕሮሰሲንግ ላይ ወዘተ ከአጠቃላይ የገቢ ንግድ ድርሻ ከአንድ እስከ ሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደሚሸፍን ይታወቃል ስለዚህ የገቢ ንግድ የሚተኩ የኢንዱስትሪዎች (Import Substitution Industrialization (ISI) ይህን የውጭ ምንዛሪ በማዳን እነዚህን ምርቶች በሃገርቤት ማምረት ይችላሉ እንላለን፡፡ በግብርናው ዘርፍ ከሚገኝ የሠሊጥ ምርት፣ የዘይት ነክ እህል ምርቶች የዘይት ፋብሪክ ከነዚህ ምርቶች ጭማቂ ዘይት በማምረት ከባህር ማዶ የሚመጣ የዘይት ምርትን መተካት ይችላሉ እንላለን፡፡ በተመሳሳይ የስኮር አገዳ ምርቶች የስኮር ፋብሪካ በመገንባት የስኮርና የስካር ውጤቶች በማምረት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ይቻላል፡፡ በኢንደስትሪያል ዞኖች የሚቆቆሙት ፋብሪካዎችን የገቢ ንግድ የሚተኩ የኢንዱስትሪዎች በመተካት ከውጭ የሚገቡ የፍጆታ እቃዎችና ሸቀጣ ሸቀጦች በመተካት የውጭ ምንዛሪ በማዳን በሃገሪቱ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ፡፡
የኢንደስትሪ ፓርኮች ኪሳራ፣ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የኢንደስትሪ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ላይ የኢትዩጵያ መንግስት ዝቅተኛ ትኩረት እንደሰጠው አማካሪዎች በጥናታቸው በማስረጃ አጋልጠዋል፡፡ የኢትዩጵያ መንግስት ልምድ ከወሰደባቸው አስራ አምስት መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች፤ የኢንደስትሪ ልማት ፍኖተ ካርታ የወሰዳቸው የአሠራር ስልቶች፣የኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ሆኖ ሳለ ከመካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ጋር ማወዳደር ተገቢ አልነበረም በማለት አጥኝዎቹ ተችተዋል፡፡ ከአስር በላይ አዳዲስ የኢንደስትሪ ፓርኮች እንደሚገነቡ፣ ፓርኮቹ ለቀጣይ አስር ዓመታት ለሁለት ሚሊዩን ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልፆል፡፡(ሰኞ ጥር 2 ቀን 2008 አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ገጽ 1-2) በጊዜው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለባለሃብቶች በጨረታ እንዲሳተፉ የሚያስችል ጥሪ ቀርቦ የጨረታ ሰነድ የገዙ ዘጠኝ ብቻ ቢሆኑም እነዚህም ባለኃብቶች አልመጡም ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት መንግስት በተለየ ሁኔታ የባንክ ማስያዥያን ሳይጨምር እስከ 85 በመቶ የብድር አቅርቦት ጨምሮ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ለማቅረብ ተገዶል ነበር፡፡ መንግስት የረዥም ግዜ ብድር ያለምንም ማስያዣ እስከ 75 በመቶ የፕሮጀክቱን የገንዘብ መጠን የሚሸፍን ሲሆን፣ ቀሪውን 25 በመቶ ባለሃብቶች ከራሳቸው መዋጮ በጥሬ ገንዘብ እንዲሸፍኑ አድርጎ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለስራ ማስኬጃ የሚቀርብ የፋይናንስ ጥያቄ እስከ 85 በመቶ በመንግስት እንደሚመለስና ቀሪው 15 በመቶ ግን የኢንቨስተሮች ድርሻ መሆኑ ተገልፆ ነበር፡፡ ይህም ከሌሎች ማበረታቻዎች እስከ 90 በመቶ እንደሚደርስ ታውቆል፡፡ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማበረታቻዎች ውስጥ የባንክ አገልግሎት፣ የጉምሩክ አገልግሎት፣ የውሃ፣ የኤሌትሪክ ኃይል፣ የቴሌኮም አገልግሎቶች መንግስት እንደሚያቀርብ ተገልጾል፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም የባንክ መተማመኛ ሰነድ (ሌተር ኦፍ ክሬዲት)ለመክፈት ይከፈል የነበረው የ3.5 በመቶ ኮሚሽን፣ አሁን ወደ 0.5 ከመቶ ዝቅ መደረጉን ተገልጾ ነበር፡፡ መንግስት የ10 አመት የግብር እፎይታ፣ ከቀረጥ ነጻነን ጨምሮ ወደ ውጪ ከተላከ ምርት የተገኘው የውጭ ምንዛሪ እስከ 28 ቀናት ባለሃብቶቹ እጅ እንዲቆይና ለሚያስፈልገው ተግባር እያገላበጡ እንዲጠቀሙበት ለማገዝ ማበረታቻ ተሰጥቶል፡፡ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአሜሪካዎቹ ፒቪኤች ኩባንያ (ካልቪን ክሌን፣ ቶሚ ሂልፈንገርና ሄሪቴጅ ብራንድስ)ና ቫኒቲ ፌር (ራንግለር፣ ባንስ፣ ቲምበርላንድ፣ ሊ) የህንዶቹ አርቪን፣ ሬንሞንት ኩባንያዎች አካቶ ከቻይና፣ ከሆንግ ኮንግ፣ ከስሪላንካ .ከማሌዥያና ከኢንዶኔዥያ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረቻ ቦታ በመያዝ ለመስራት እቅድ እንዳላቸው ዶክተር አርከበ ዕቁባይ አስታውቀው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የ2010 ዓ/ም በጀት እቅድ መሠረት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እቅድ 997 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን የእቅዱ አፈፃፀም ግን 487.5 ሚሊዮን ዶላር ማለትም 57.8 በመቶ ሆኖል ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪ ዞኖች ድርሻ አናሳ በመሆኑ አልተገለፀም፡፡ ከኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ግን ኢምንት ነው፡፡
ምንጭ
- Email: [email protected]
- Web: investethiopia.gov.et
- Industrial Parks Development Corporation Web: ipdc.gov.et
- Ministry of Industry Web: moin.gov.et
Unfortunately I made a research on Industrial Parks Development of Ethiopia, but I have never seen this kind of false and biased data, that say industrial parks developed with 10 billion USD, I think the country itself have not have this much amount or it missed written and the compression with the great renascence dam is not appropriate, first the budget of one renascence dam can built 10 to 15 modernized parks, second the dam yet not be finalized according to its timetable but still a remarkable project, third with out the industrial parks what will be the option for industrialization?
In general the data is used misleads the writer and its conclusion and for future before publishing any document it needs to verify the data and the source also need to cross check otherwise it lower down the creditability of the site or the institute who published it,