ከውጭ ሀገር በበየነ መረብ የሚተላለፉ መገናኛ ብዙሀንን እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ ተገለፀ፡፡አሁንም ድረስ በበይነ መረብ አማካኝነት ከውጭ ሀገር የሚተላላፉ መገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠ…

ከውጭ ሀገር በበየነ መረብ የሚተላለፉ መገናኛ ብዙሀንን እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ ተገለፀ፡፡

አሁንም ድረስ በበይነ መረብ አማካኝነት ከውጭ ሀገር የሚተላላፉ መገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠርበት ቴክኒካል አሰራር እንደሌለው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን በሀገር ውስጥ የሚሰሩ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን፤ ከዚህ ቀደም መስሪያ ቤቱ ቀርበው ምዝገባ እንዲያካሄዱ ማሳሳቡ ይታወሳል፡፡

የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ወንደሰን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፤ እስካሁን ድረስ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን አሰራርን ህጋዊ ለማድረግ በተጀመረው ስራ፤ 35 በግለሰብና በተቋም ደረጃ ያሉ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን ተመዝግበዋል፡፡

ለመዝገባ በርካታ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን የመጡ ሲሆን ነገር ነገር ግን ማሟላት ያለባቸውን ዶክመንት ባለማሟላታቸው እንዲመለሱና እንዲያሟሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የእነዚህ የመገናኛ ብዙሃን አይነቶች ምዝገባ አስፈላጊነት ስርአት አልበኝነትን ከመቆጣጠር ባለፈ ለመገናኛ ብዙሀኑ የአቅም ማጎልበቻ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ያልተመዘገቡ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣኑ የማያውቃቸው እንደሆኑ የገለፁት አቶ አበራ ተጠያቂነት በሚመጣባቸው ወቅትም ሆነ በማንኛውም መንገድ ምንም ድጋፍ አይሰጣቸውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በበይነ መረብ አማካኝነት ከውጭ ሀገር የሚተላለፉ መገናኛ ብዙሀንን ግን የምንቆጣጠርበት አሰራር ይፈጠራል ያሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን በዚያ አቋም ላይ አንገኝም ብለዋል አቶ አበራ፡፡

በውጭ ሀገር አካውንት የተከፈቱና የሀገር ቤት ቋንቋዎች በመጠቀም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ማስተላለፍን የመሰሉ የህግ ጥሰት የሚፈፅሙ የበየነመረብ መገናናኛ ብዙሃን፤ ክትትል በማድረግ በፍትህ ተቋማት ግለሰቦቹ ሊከሰሱ የሚችሉበት አማራጭ ይኖራል ብለዋል፡፡

እነዚህን በውጪ ሀገር አካውንታቸውን ያወጡ የመገናኛ ብዙሃንን መቆጣጣር ያልተቻለው አሰራራቸውን ህጋዊ ለማድረግ አካውንቱን ካወጡበት ሀገር ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ጨምር ሌሎች ከፖሊሲ ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ስራዎችን መስራት ስለሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

በጂብሪል መሀመድ

ነሃሴ 07 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply