ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮ የበልግ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ተባለ

እስከ ግንቦት መጨረሻ ባሉት ወራት ውስጥ ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ እንስቲትዩት አስታውቋል።

የዝናብ ስርጭቱ ከመጀመሩ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ በጥር ወር 2016 ዓ.ም በተከናወነ ትንብያ ፤ ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን ስርጭት እደሚኖር በኢትዮጲያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሜትሮሎጂ ትንበያ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሸመ ተናግረዋል፡፡

በሶማሌ፣ ጉጂ፣ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከዓመታዊ የዝናብ መጠን 55 በመቶ የዝናብ ስርጭት የሚኖረው በበልግ ወቅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከየካቲት ጀምሮ በሶማሌ ክልል፣ በጉጂ፣ ቦረና፣ ሲዳማ ፣ደቡብ ኢትዮጲያ እና ደቡብ ምዕራብ እንዲሁም አፋር ክልል ከቀላል እስከ ከባድ የዝናብ መጠን መስተዋሉን አንስተዋል፡፡

በምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች በልግ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው መሆኑን አንስተው፤ በእነዚህ አከባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የዝናብ ስርጭት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

በቀሪዎቹ ወራት በልግ ዋነኛ እና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አከባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ የሆነ ፤ ከቀላል እስከ ከባድ የዝናብ ስርጭ እንደሚኖር ጠቁመው፤ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ ከቀላል እስከ ከባድ ያለው ዝናብ የሚቀጥል እንደሚሆን ተመላክቷል።

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply