ከዚህ በኃላ በላሊጋ የመቆየት ፍላጎት የለኝም… ቪኒሽየስ!ትላንት በስፔን ላሊጋ ለ7ኛ ጊዜ የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ቪኒሽየስ ጁኒየር ላሊጋው በዘረኝነት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Owl1f-TUeI45dcY1nuVNrpioRIuSNTt5oXKv-3Oma0BV73uIsGue8m4EaCwtfsWNREjfb7qIxAabEEfACcqsOnw-wDIxOdzjl-zRNJv4nd_KOpPw2Wr-qXTEe6SEfGdI8v8WWtc1ZeSCtpGqnmr9YAR_S9EyY8O7G3b2Cx-6oXY8aFCed2kqxfN92wsaswZGAM9FW8ruSZTqj_fpnTPZZKbADy-Z8QZnwxKxPiDX5quY8yfhGk0yLcVa2_BM0wJ_qy4wSd0SmC0HEpXHqSgLCLR9Lsa8La8H_FN6lrf_R_bLEPVaQIrzQCglgMbFdNYHmoNwBQT5f4OsKAeZxLsCkw.jpg

ከዚህ በኃላ በላሊጋ የመቆየት ፍላጎት የለኝም… ቪኒሽየስ!

ትላንት በስፔን ላሊጋ ለ7ኛ ጊዜ የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ቪኒሽየስ ጁኒየር ላሊጋው በዘረኝነት የተጨማለቀ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

በአንድ ወቅት የሮናልዶ እና የሚሲ ሊግ ይመስል የነበረው ላሊጋ አሁን የዘረኞች ሊግ ሆኗል ብሏል፡፡
ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሲያ ጋር በነበረው የላሊጋ ጨዋታ ቪኒሽየስ ጁኒየር እስቴዲዬሙ በነበሩ ተመልካቾች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶበታል፡፡

በጨዋታው መሃል በቀይ ካርድ የወጣው እንዲሁም የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ይህ ተጫዋች በላሊጋው አመራሮች ላይም ቅሬታውን ገልጿል፤ሙሉ በሙሉ ላሊጋው ወደ ዘረኝነት ተቀይሯል ሲለም ተናሯል፡፡

በቪኒሽየስ የደረሰውን የዘረኝነት ተቃውሞ ተከትሎ ስመጥር ተጫዋቾች በድርጊቱ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም መካከል የቀድሞ የማድሪድ አስለጣኝ እና ተጫዋች ዚነዲን ዚዳን ድርጊቱን እጅግ አሳዛኝ ሲል ገልጾታል፡፡

የፊፋው ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኒዮ ከቪኒሽየስ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረው ደርጊቱን የፈጸሙት ደጋፊዎች እና ክለቡ ከፍተኛ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ብለዋል፡፡
የሪያል ማድሪዱ አስለጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ላሊጋው የዘረኞች መፈንጫ ሆኖ ዝም ማለቱ አሳዛኝ ነው ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply