ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት ቆሟል፡፡የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፥ ” ለህዝቡን ድህንነት ሲባል በተለያዩ መንገዶች ወደ ከተማው የሚገቡ ጸጉረ ልውጦ…

https://cdn4.telesco.pe/file/pGMjX36KLXyl6wiyO8mZHfwNbvdSQY4enp9SMdsX6H8-KKIiJxygrEiJVWH57gHrw_DzoMs-cPO-ES5QkCsK2yGLSU7_sMxqsSpfZQCC83cvi4LUr7V79raClxv1dim6TaS04B-f-Pns9twgC2Izxenj9HvnujA9hENNkFA2kKr5fvmN-lXId5guqNTMEHgXKlL4Wa_bFxJ4A9sWOvGfOaCT5NBoH5D_iP6JmOW6q0xoXbmwiW0H3q3FTE-PvZMvZw1aXkXqUnNEWPF8vO4_eW9N8JWYJIvzfr_39Ny_wiHpPW005OxcS7gVkbzQWNyb0gRh4oZRFvmcRZH6OWPDqw.jpg

ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት ቆሟል፡፡

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፥ ” ለህዝቡን ድህንነት ሲባል በተለያዩ መንገዶች ወደ ከተማው የሚገቡ ጸጉረ ልውጦችን እና ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል ሲባል የከተማ አስተዳደሩ ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም ወረዳ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት መስጠት ቆሟል ” ብሏል።

የሀገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ከከትላንት ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል::

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጅ መሰረትም የከተማው የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፡፡

ሆኖም የከተማችን ነዋሪዎች ሆነው በተለያዩ ምክኒያቶች መታወቂያ ያልወሰዱ ነዋሪዎች ካሉ በልዩ ሁኔታ በሚመለከተው አካል ተጣርቶ እና ተረጋግጦ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚዘጋጅላቸው ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply