You are currently viewing ከዱርቤቴ በሊበንእስከ ደልጊ እና መተማ የሚወስደው መንገድ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብታዊ እና የጤና አገልግሎት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።  ( አሻራ ታህሳስ 28፣ 20…

ከዱርቤቴ በሊበንእስከ ደልጊ እና መተማ የሚወስደው መንገድ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብታዊ እና የጤና አገልግሎት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። ( አሻራ ታህሳስ 28፣ 20…

ከዱርቤቴ በሊበንእስከ ደልጊ እና መተማ የሚወስደው መንገድ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብታዊ እና የጤና አገልግሎት ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። ( አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም ) በ1997 ዓ.ም አራት ወረዳዎችን ማለትም ዱርቤቴን፤ ሊበንን፤ደልጊንና መተማን የሚያገናኘው መንገድ ይሰራል የሚለው የመንግስት ዕቅድ ባለመፈፀሙ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ሲሉ የመንገዱን ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ ሰብሳቢ ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል፡፡ ከአሁን በፊት የመንገድ ግንባታው በመዘግየቱ ምክንያት ኮሚቴው የፌደራል መንገዶች ባለስልጣንን በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢጠይቅም ከፌደራል መንገዶች ባለ ስልጣን በኩል አንድ ጊዜ ጨረታ አውጥተናል ተቋራጮች ሊሰሩት ዝግጅት ላይ ናቸው ፤ሌላ ጊዜ ደግሞ ባልታወቀ ምክንያት ተጓቷል የሚል ምላሽ እየሰጡ መንገዱ ሳይሰራ በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና እና የዓሳ ምርቶች በብዛት ለገበያ ባላማቅረባቸው በብልሽት ኪሳራ እየገጠማቸው ይገኛል ብለዋል፡፡ ጥያቄያችንን ለአማራ ክልል መንገዶች ቢሮ ያቀረብን ቢሆንም ጨረታ አውጥተናል ያሉበትን ወረቀት ከመደበቅ ጀምሮ በተደጋጋሚ የማድበስበስ ስራ ሰርተውብናል ሲሉ ገልጸውልናል፡፡ መንገዱ ለመጀመሪያ ጊዜ በደርግ ዘመነ መንግስት ጥርጊያ ተደርጎለት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ለተከታታይ ከ20 ዓመት ወዲህ ግን ምንም አይነት ጥገና ተደርጎለት እንደማያውቅ ገልጸውልናል፡፡ ክቡራን ተመልካቾቻችን ከኮሚቴው ሰብሳቢ ጋር የስልክ ቃለ ምልልስ አድርገናል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply