You are currently viewing #ከዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የተላከ አስቸኳይ መልዕክት:- ለመላው አማራ ህዝብ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የሽብር ወንጀል ስፈፅም ከግብረአበሮቼ ጋር ተይዤ ዘብጥያ መውረዴን…

#ከዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የተላከ አስቸኳይ መልዕክት:- ለመላው አማራ ህዝብ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የሽብር ወንጀል ስፈፅም ከግብረአበሮቼ ጋር ተይዤ ዘብጥያ መውረዴን…

#ከዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የተላከ አስቸኳይ መልዕክት:- ለመላው አማራ ህዝብ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የሽብር ወንጀል ስፈፅም ከግብረአበሮቼ ጋር ተይዤ ዘብጥያ መውረዴን እንደማንኛውም ሰው ከመገናኛ ብዙሀን ዛሬ ሰማሁ፡፡ የኦሮሞ ብልፅግና መንግስት እና ግብረአበሮቹ ክስ እየፈበረኩ ማሰር መግደል ልማዳቸው መሆኑ የታወቀ በመሆኑ እኔም ከዚህ ቀደም በሀሰት ክስ የታሰርኩ እና የተንገላታሁ በመሆኑ እንዲሁም ስርዐቱ ሲጀመር ጀምሮ በሀሰት ልብ አማላይ ንግግሮች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ አልገረመኝም ፡፡ ነገር ግን ፈፅሞ የማይተዋወቁ ሰዎችን፣እንዲሁ በአቦሰጡኝ ሊቃወሙኝ ይችላሉ ያላቸውን ሰዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ ሰብስቦ ማሰሩ ሳያንስ ልክ እንደኔ በእጁ ያልገቡትንም ጨምሮ በቁጥጥር ስር አውያለሁ ማለቱ ብልፅግና እና ሀሠት እንዴት እንደተዋሀዱ ማሳያ ነው፡፡ ይህ አማራ ጠል ስርዐት ፡ አማራ ጠል የሆኑትን ዘረኛ የፌደራል እና የክልል ህገመንግስቶችን ተቀብሎ ቀጥሎዋል ከ52 በላይ ፀረ አማራ እና የዘር ፍጅትን የሚሰብኩ መፃህፈትን ሰፖንሰር በማድረግ አሳትሞ አሰራጭቱዋል በመንግሰት መገናኛ ብዙሀን በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅትን የሚሰብኩ ፕሮግሞች አሰራጭቱዋል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የዘር ፍጅትን የሚያነሳሱ ንግግሮች ተደርገዋል ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማሮች ከኦሮሚያ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሉዋል ከሠላሳ ሺ በላይ አማሮች ላይ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ፈፅሙዋል በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ንብረት እንዲወድም አድርጉዋል ቤተክርስትያንን ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ እጅ ከፍንጅ ተይዝዋል ከነባሩ እስልምና መጅሊሱን ነጥቆ ወገኖቼ ላላቸው አስረክቡዋል አገሪቱን ለማፍረስ አሲሩዋል፣የገደል አፋፍ ላይ አድርሱዋታል በኑሮ ውድነት ህዝቡን መድረሻ አሳጥቱዋል፣በተረኝነት የአገሪቱን ንብረት ዘርፉዋል ተጨማሪ ብዙ ሚሊዮን ዜጎች ላይ የዘር ፍጅት ለመፈፀም እና ለማስፈፀም በዝግጅት ላይ ነው የአማራ ህዝብ በደሙ ያስመለሳቸውን ርስቶቹን ለጠላት ለማስረከብ ተስማምቱዋል የአማራን ህዝብ ልጅ የሆነውን ፋኖን ለመደምሰስ አቅዶ ተንቀሳቅሱዋል የአማራ ልዩ ሀይልን ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን አቅዶ ወደ ስራ ገብቱዋል የአማራ ህዝብ ወደ ዋና ከተማው አዲስአበባ እንዳይገባ ማገዱን በይፋ አሳውቁዋል ይሄን ለማስፈፀም ስርዐቱ የእጅ ጥራጊ መብላት፣የዋንጫ ልቅላቂ መጠጣት ያስለመዳቸውን ግብረበላ አክቲቪስቶች፣ፖለቲከኛ ነን ባዮችን እና ባለስልጣናትን አሰልፎ ይንቀሳቀሳል ይሄንን አስከፊ ስርዐት ለመታገል እና ለማስወገድ ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉን ፡፡የአማራ ህዝብ ትግል ለበላይነት የሚደረግ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት ግቡ ያደረገ ለሰላም፣ለፍትህ ፣ለእኩልነት እና ለዲሞክራሲ የሚደረግ እንዲሁም ፣ከሁሉም በላይ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ትግል መሆኑን በመረዳት መላው ህዝባቸን በሙሉ ሃይሉ ይሄንን አስከፊ ሰውበላ ስርዐት ለማስወገድ እንዲንቀሳቀስ አደራ እላለሁ፡፡ የአማራ ፋኖ እና ልዩ ሀይል አባላት እና አዛዦች በዚህ ወሳኝ ወቅት ለአማራ ህዝብ በታማኝነት ዘብ እንድትቆሙ እየጠየቅኩ፣የመከላከያ ሠራዊት አባላትም የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ የአምባገነኖች ዘብ ባለመሆናችሁ፣የንፁሀንን ደም በማፍሰስ፣በመግደል እና በሀሰት በመወንጀል በሚደረገው በሰብዐዊነት ላይ እየተፈፀመ ላለው ወንጀል ተባባሪ ባለመሆን ለአንድነት እና ለፍትህ በመቆም ህዝባዊ ወገንተኝነታችሁን እንድታሳዩ እጠይቃለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ያለው ወንድማችን የቱለማ ነገድ፣የመከራ ፅዋ እየተጎነጩ ያሉት እና በግፈኞች ማንነታቸውን የተቀሙት የአንፊሎ እና የጨቦ ህዝቦች፡፡ በኦሮሞ ተስፋፊ ሀይሎች ርስታቸውን እየተቀሙ ሰላም ያጡት የሶማሌ፣የሲዳማ ፣የጋሞ እና የጉራጌ ወንድሞቻችን ትግላችሁን ከአማራ ህዝብ ትግል ጋር እንድታስተሳስሩ እጠይቃለሁ፡፡ የአማራ ህዝብ ለሺ አመታት አባቶችህ እና እናቶችህ በከፈሉት መስዋዕትነት እንደ አገር የቆመችው ጥንታዊቱዋ አገርህ ኢትዮጵያ ከአንተ እንደተወሰደችብህ በመረዳት ለትግሉ በፅናት እንድትቆም አደራ እያልኩ በዚሁ አጋጣሚ የአማራ ህዝብ የታጋይ ልጆቹ ን መዝሙር እንዲያደምጥ እና አብሮ እንዲዘምር አላፈገፍግም የሚለውን መዝሙር እጋብዛለሁ፡፡ ወንድወሠን አሰፋ (ዶ/ር) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply