“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…

“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…

“ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ሀገርን ለማተራመስ የሚሠሩ የውጭ ኃይሎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መታገል ይገባል” ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ እንደተናገሩት የእኔ ብሔር ብቻ ማለት ባለፉት 27 ዓመታት የተወረሰና ያደገ አስተሳሰብ ነው። ይህ ደግሞ ለነጭ ጁንታዎች ተጠቃሚነት ሰፊ ዕድል የሰጠና ኢትዮጵያን የችግር ቋት ውስጥ የከተተ ነው። በመሆኑም ከብሔር አስተሳሰብ ወጥቶ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ቆሞ የነጭ ጁንታዎችን እጅ ማሳጠር ያስፈልጋል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውጭ ኃይሎች ከሚያስተላልፉት መልዕክት ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማቆርቆዝ ያለመ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ኦባንግ፤ የነዚህን ኃይሎች ድርጊት ለማስቆም በቅንጅት መሥራት ካልተቻለ አደጋው የከፋ ይሆናል ነው ያሉት። የትህነግ ጁንታ በ27 ዓመታት የአገዛዝ ዘመኑ ከነጭ ጁንታዎች ጋር በመሆን ሃገሪቱን ለብዙ ችግር ዳርጓታል የሚሉት አቶ ኦባንግ፤ አሁንም ይህንን አሠራር ነጭ ጁንታዎች ይፈልጉታልና የተለያዩ ሪፖርቶችን ለህዝብ በማቅረብ ከትህነግ ጁንታ ጎን መሆናቸውን እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህ ነጭ ጁንታዎች በሃገሪቱ የተፈጠረውን ግጭት መነሻ አድርገው የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ይገኛሉ ብለዋል አቶ ኦባንግ። በተለይም የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ መስለው የሌለና የሀሰት መረጃ ከመስጠት አንጻር ችግር እየፈጠሩ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ እውነታውን ስለሚያውቀው ይህንኑ እውነታ ለዓለም ማኅበረሰብ ማሳወቅ አለበት። ለዚህ ደግሞ በተናጠል ሳይሆን በአንድ ሃሳብ በአንድነት መቆም እንደሚገባ ገልፀዋል። በኢትዮጵያ ያለው ጉዳይ የኢትዮጵያ እንጂ የነጭ ጁንታዎች ጉዳይ እንዳልሆነ ግልጽ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፤ ነጭ ጁንታዎች ግን እኛ እናውቅላችኋለን በሚል እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። እንደ አቶ ኦባንግ ገለጻ፤ አሁን አገር እያተራመሰ ያለው ጁንታ ቀደም ሲል ከእነዚህ ነጭ ጁንታዎች ጋር ወዳጅ ነበር ብለዋል። በዚህ የተነሳ ጁንታው ሀገር በሚመራበት ወቅት ይፈጽም የነበረውን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለማሳየት አይፈልጉም። አሁን ግን የህግ ማስከበር ሥራ ሲሠራ ጩኸታቸው ሁሉ ሰብዓዊ መብት ሆኗል። ‹‹የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የመንግሥታት ድጋፍ ጉዳይ ሳይሆን ሰው የመሆን ጉዳይ ነው›› የሚሉት አቶ ኦባንግ፤ ነጭ ጁንታዎች ግን ይህንን ትተው 27 ዓመት ሙሉ የነበረውን አሰቃቂ ሰብዓዊ ጥሰት ሳያነሱ ዛሬ እየሆነ ያለውን ይኮንናሉ ሲሉ አክለዋል። ይሄን የሚሉ ኃይሎች ደግሞ ማመዛዘን እንኳን የተሳናቸው ለመሆናቸው ብዙ ምክንያት መጥቀስ ይቻላል የሚሉት አቶ ኦባንግ፤ የግጭቱ ጀማሪ የትህነግ ጁንታ ስለመሆኑ ጁንታው ራሱ ምስክርነቱን ሰጥቶ እያለ እነርሱ ግን መንግሥት ዋሽቷል ብለው ሲያቀነቅኑ መታየታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር የእነርሱ ድጋፍ ለጁንታው እንጂ ለሰብዓዊነት አለመሆኑን ነው የገለጹት። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት በተለያየ መንገድ በውጭ አካላት ጫና ለመፍጠር ሙከራዎች እንዳሉ እሙን ነው። ስለሆነም ይህንን መመከት የሚቻለው ጉዳዩ የሃገር መሆኑን አምኖ በተቀናጀ መልኩ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ላይ በመሥራት ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥትን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥልቅ ጥናት አድርገው ሁኔታውን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማስረዳት አለባቸው። የማይወክለንንም ሃሳብ አይወክለንም ማለት ያስፈልጋል ብለዋል። የትህነግ ጁንታ ከሠራው ሥራ አንዱ የመደራጀትና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ተግባራዊ እንዳይሆን ማድረግ ነው ያሉት አቶ ኦባንግ፤ አሁን ግን ይህ ኃይል በመደምሰሱ ትክክለኛ ፍትህና የሰብዓዊ መብት መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ ሁሉም በሚያውቀው ቋንቋ እውነታውን ማስረዳትና የኢትዮጵያን ገጽታ መገንባት ላይ መረባረብ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ያስፈልጋል፤ የነጭ ጁንታዎችን የረዘመ እጅ መቁረጥም እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በቅርቡ ወደ አሜሪካ አቅንተው የሃገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ሲያስረዱ እንደቆዩና አሁንም በዚህ ሥራ ላይ እንደሆኑ የሚያነሱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ፤ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ከኮንግረንስ እስከ ቲንክ ታንክ ግሩፕ ድረስ ወርደው መሥራታቸውን ተናግረዋል። አሁንም ቢሆን ነጭ ጁንታዎች ጠንካራ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲኖር ስለማይፈልጉ እነርሱ እጃቸው እንዲያጥር በመሥራት ላይ እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። ሆኖም በግለሰቦች ደረጃ የሚደረገው እንቅስቃሴ በቂ ስላልሆነ ሁሉም በቻለው ሁሉ መሥራት እንዳለበት መግለፃቸውን ኢትዮ ፕረስ ነው የዘገበው

Source: Link to the Post

Leave a Reply