#ከጃርዴጋ ጃርቲ የጣር ድምፆች! በጃርዴጋ ጃርቲ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በገዳዩ ሃይል ተከበናል የሚመለከተው አካል ይድረስልን ሲሉ ለአሻራ በስልክ ተናገሩ። ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም…..

#ከጃርዴጋ ጃርቲ የጣር ድምፆች! በጃርዴጋ ጃርቲ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በገዳዩ ሃይል ተከበናል የሚመለከተው አካል ይድረስልን ሲሉ ለአሻራ በስልክ ተናገሩ። ሕዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከዚህ በፊት ከጭፍጨፋ የተረፉ በጃርዴጋ ጃርቲ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ከ25/2015 ዓ/ም ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩሃይል እና ኦነግ ሸኔ አካቢያችንን ከቦ ይገኛል ብለዋል። ከአሁን አሁን ጥቃት ተከፈተብን በሚል ጭንቀት ውስጥ ነን ሲሉ ስጋታቸውን ለአሻራ ሚድያ በስልክ ተናግረዋል። እንደምንጮች ገለፃ ከቀን 25/205 ዓ/ም ጀምሮ በወለጋ በተለያዩ አማራዎች ይኖርባቸዋል የሚባሉ ቦታወች ለጥቃት ይመቻቸው ዘንድ ጥናት ያደረጉአቸውን አካባቢዎች ከበባ እያደረጉ ነው ብለዋል። በመንግስት አመራሮች የሚመራው የኦሮሞ ልዩ ሃይል ከሰሞኑ በአማሮች ላይ የዘር ፍጅት የፈፀመው የኦሮሞ ተወላጆች ቦታውን ለቀው እንዲወጡ በማድረግና በአብዛኛው አማሮች የሚኖሩበትን አካባቢ በማጥናት ነው በማለት ገልፀዋል። በጃርዴጋ ጃርቲ የሚኖሩ አማሮቸን ይህ ገዳይ ጥምር ሃይል አሁን ላይ ጥናቱን ጨርሶ ከበባውስጥ አስገብቶናል ከመጨፍጨፋችን በፊት እባካችሁ መልዕክታችን አድርሱልን በማለት ተማፅነዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply