You are currently viewing “ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ለመዝጋት እና ሁከት ለመፍጠር ሙከራዎች ተደርገዋል” በሚል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አማራ ሚዲያ…

“ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ለመዝጋት እና ሁከት ለመፍጠር ሙከራዎች ተደርገዋል” በሚል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አማራ ሚዲያ…

“ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ለመዝጋት እና ሁከት ለመፍጠር ሙከራዎች ተደርገዋል” በሚል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ “ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ለመዝጋት እና ሁከት ለመፍጠር ሙከራዎች ተደርገዋል” በሚል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጧል። በተጨማሪም ከ10 በማያነሱት ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን በስልክ ያነጋገርናቸው የአይሻ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎም በዞኑ አብዛኛው አካባቢዎች ውጥረትና አለመረጋጋት በመፈጠሩ ከድሬዳዋ ወደ ጅቡቲ የሚወስደው አስፓልት መንገድ መዘጋቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ የተገኘ መረጃ ያመላክታል። “ተወልደን ካደግንበትና በቋሚነት ከምንኖርበት መፈናቀላችን አግብባ አይደለም” ሲሉ አስተያየታቸውን የገለፁት አቶ ጣሂር ዲረኔ የተባሉ ነዋሪ “የአፋር ክልል ከተሞች ከሆኑት ከገርበኢሴ፣ ኡንድፎ እና አደይቱ ከተሞች በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ሲቲ ዞን መሰደዳቸውን” ይገልፃሉ። ዘገባው የአዲስ ዘይቤ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply