ከገዛ እናቷ 50 ሽህ ዶላር ለማግኘት የራስዋን የእገታ ወንጀል ያቀነባበረችዉ ስፔናዊ ወጣት በቁጥጥር ስር ዋለች:: ከሰሞኑ አንድ ስፔናዊት ሴት ከፍቅረኛዋ ቤተሰብ ጋር በማሴር ታግቻለዉ በሚል…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Ar6RnR74MDdRbeV-BWeKsIYi9QgFM5f0_nlYGG9OYyr3nVEXOcDKRiXo7Tdz5O9Lk_mD4Satk06XecOMPoeEu4gFDL6eezj6Yma5HlVhOEYfDBw0MRA7y1PqakYbd4t7KNmHOT2BOQKH6fFMAfra6i6jjWWJ2UpWxccO0eAKcT3QAcdk4e6vCRtYLEKqKt62_8E-u_yl45HobqPbcpmMyBrbd503TH5jC0qQ_tO7K8DiaCKCqnvm4Ukmj5fWccajTExaKSrb2zUU3zCLlfaXsD2I5oPyseysWATejPeJ3k57-eJpTtaqDcXtqZgkzVObZRFSoRYVtd4AHlRbwLLGMg.jpg

ከገዛ እናቷ 50 ሽህ ዶላር ለማግኘት የራስዋን የእገታ ወንጀል ያቀነባበረችዉ ስፔናዊ ወጣት በቁጥጥር ስር ዋለች::

ከሰሞኑ አንድ ስፔናዊት ሴት ከፍቅረኛዋ ቤተሰብ ጋር በማሴር ታግቻለዉ በሚል ምክንያት ከገዛ እናቷ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ ለማስከፈል ስትንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ዉላለች፡፡

ከስፔን ብሄራዊ ህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች አንዱ የሆነዉ ጓርድያ ሲቪል፣ ዐይኗን የተጨፈነች ሴት ፊቷ ላይ ደም ያለበት ወንበር ላይ ታስራ እና ትልቅ ቢላዋ በጎሮሮዋ ላይ ያደረገች የሚመስል የሚያሳይ ምስል በቪድዮ ተለቆ ነበር፡፡

ወጣቷ እያለቀሰች እናቷ ድጋሚ በሂወት ልታያት ከፈለገች ሃምሳ ሽህ ዶላር መክፈል እንዳለባት ስትነግራት ያሳያል፣ ነገር ግን ሁሉም ምስል ከመታገቱ ዉጭ ዉሸት ነበር፡፡

በጋርዲያ ሲቪል የተለቀቀዉ ምስል ተጎጅዋ ታዳጊ ማን እንዳገታት እና ለምን እንደታገተች እንደማታዉቅ እና እናቷን ለማስለቀቂያ የሚሆን ሀምሳ ሽህ ዩሮ በጥሬ ገንዘብ እንድታመጣ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለማድረግ ብትሞክር ህይወቷ ሊያልፍ እንደሚችል ስታስጠነቅቃት ያሳያል፡፡

እናት የአጋቾቹን ጥያቄ ተቀብላለች፣ ብሩንም ከባንክ አዉጥታለች፣ ነገር ግን እንቆቅልሹ የተፈታዉ እናት በድብቅ ስለእገታዉ ለፖሊስ ስትናገር ነበር፡፡

ፖሊስ ባደረገዉ ምርመራ እዉነተኛ ተጎጅዋ ታገትኩ ያለችዉ ልጅ ሳትሆን አጀንዳ የተጠነሰሰባት እናት መሆኗ ታዉቋል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ

መስከረም 02 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply