ከጉሙዝ ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል በሚል በጉምዞች ላይ ግድያ ፈፅማቹሀል የተባሉ ግለሰቦች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደሚገኙ ታወቀ አሻራ ሚዲያ ታህ…

ከጉሙዝ ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል በሚል በጉምዞች ላይ ግድያ ፈፅማቹሀል የተባሉ ግለሰቦች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ እንደሚገኙ ታወቀ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 05 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በ2011 ዓ.ም በመተከል ዳንጉር ወረዳ በአማራ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም ራሳቸውን ለመከላከል እርምጃ ወስዳችኋል የተባሉ 73 (ሰባ ሶስት ) የአማራ እና የአገው ተወላጆች በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ያለ ፍትህ ከ18 (አስራ ስምንት) ወር በላይ በእስር ላ እንደሚገኙ ተሰምቷል፡፡ የተከሳሾች አድራሻ ጃዊ ወረዳ ሲሆን በ2011 ዓ.ም በጉሙዞች ላይ ጥቃት ፈጽመማችኋል በሚል የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸው በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ተከሳሾቹ ምንም እልባት ሳይሰጣቸው ከቤተሰቦቻቸው ርቀው አንድ አመት ከስድስት ወር በላይ ያለ ፍትህ በእስር እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ገልጸውልናል፡፡ የተከሳሾች ብዛት ሰባ ሶስት ሲሆን ከነዚህም መካከል ፡- 1/ ኢንስፔክተር ካሳ ቢረስ የጃዊ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ 2/ ደስታው ሽመልስ የጃዊ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ 3/ የኔው መኩሪያ የጃዊ ወረዳ አስተዳደር ጸጥታ ሀላፊ 4/ በላይነህ ውዱ የጃዊ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ ይገኙበታል፡፡ አሻራ ሚዲያ የተከሳሾቹን ጉዳይ እና የችሎት ውሎ በመከታተል ዘገባዎች ያቀርባል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply