ከጉቶ ጊዳ ወረዳ ወደ ኡኬ ቀርሳ ተወስዶ ለከፍተኛ የህክምና ድጋፍ ወደ ነቀምት ሪፈር የተባለ የ10 ዓመት ህጻን ልጅ መንገድ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በመዘጋቱና ቶሎ ለመድረስ ባለመቻሉ ህይወቱ…

ከጉቶ ጊዳ ወረዳ ወደ ኡኬ ቀርሳ ተወስዶ ለከፍተኛ የህክምና ድጋፍ ወደ ነቀምት ሪፈር የተባለ የ10 ዓመት ህጻን ልጅ መንገድ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በመዘጋቱና ቶሎ ለመድረስ ባለመቻሉ ህይወቱ አለፈ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከጉቶ ጊዳ ወረዳ ወደ ኡኬ ቀርሳ ተወስዶ ለከፍተኛ የህክምና ድጋፍ ወደ ነቀምት ሪፈር የተባለ የ10 ዓመት ህጻን ልጅ መንገድ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከጥቅምት 21/2015 ጀምሮ በመዘጋቱና ቶሎ ለመድረስ ባለመቻሉ ህይወቱ ማለፉን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች አረጋግጠዋል። ከነቀምት ወደ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ለበቆሎ ጭነት ሲጓዙ የነበሩ 16 ሲኖትራክ መኪናዎች በሳሲጋ ወረዳ ሀሮ ፈይሳ ላይ ሲደርሱ ጥቅምት 21/2015 ከረፋዱ ጀምሮ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ተይዘዋል፤ ከመኪናዎቹ መካከል አንዱ ሽንኩርት የተጫነበት ነው። መኪናዎቹን በመጠቀም መንገዱን ከዘጉ በኋላ የአሽከርካሪዎችን ቁልፍ በመቀማት ወደ ጫካ መግባታቸውን የአሚማ ምንጮች ከስፍራው ተናግረዋል። በተመሳሳይ ጥቅምት 21/2015 ከአንገር ጉትን ወደ ነቀምት በአካባቢው ሚሊሾች ታጅበው ያቀኑ ተማሪዎች መንገድ በመዘጋቱ ከሳሲጋ ወረዳ ሀሮ ፈይሳ ቀበሌ ጀምሮ በእግራቸው ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ካቋረጡ በኋላ ነቀምት ገብተው ማደራቸው ታውቋል። የሽብር ቡድኑ የሰራውን ወንጀል በቢሮ ሰዎቹ በኩል ሚዲያን ተጠቅሞ በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን እየወነጀለ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ወደ አካባቢው ወርዶ በቡድኑ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply