ከጊዜ በኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው ተባለ፡፡                 አሻራ ሚዲያ…

ከጊዜ በኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

ከጊዜ በኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-26/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር ከጊዜ ኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው ሲሉ የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንደተናገሩት እንደ ሕወሓት ያሉ ፓርቲዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታም ከዚህ እንደማያልፍ ነው የጠቀሱት፡፡ ሕወሓት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በጋብቻ፣ በንግድ፣ በሃይማኖትና በባሕል እጅግ የተሳሰረ የመሆኑን እውነታ በመካድ የማይታረቅ ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ ሲሰብክ ኖሯል ሲሉ ነው የከሰሱት፡፡ በዚህም አጥፊና ከፋፋይ የሆነውን ‹‹የእኛ እና እነሱ›› ትርክትን ፈጥሯል ብለዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ በጠላት እንደተከበበ አድርጎ በመስበክ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙኃን በኩልም ተከታታይ የጦርነት ዘጋቢ ፊልሞችን ሲያሳይ ስለመክረሙ አስታውሰዋል፡፡ ሕወሓት ራሱን የብሔር፣ ብሔረሰቦች ሰላም ብቸኛ ጠባቂ አድርጎ ሲያስፈራራ መኖሩንም ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ያነሱት፡፡ በመላ አገሪቱ ግጭቶችን በተለያዩ መንግዶች ሲደግፍ እንደነበር በመክሰስ፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሕግ ወደማስከበሩ ዘመቻ መግባቷንም አስታውሰዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply