You are currently viewing ከጊዳ አያና ተነስተው ወደ አንገር ጉትን በቅጥቅጥ መኪና ሲጓዙ የነበሩ አማራዎች የተቀነባበረ ካሉት ጥቃት መትረፋቸውን ገለጹ፤ ይሁን እንጅ ለምርመራ ትፈለጋላችሁ በሚል በጊዳ የታሰሩ መሆናቸው…

ከጊዳ አያና ተነስተው ወደ አንገር ጉትን በቅጥቅጥ መኪና ሲጓዙ የነበሩ አማራዎች የተቀነባበረ ካሉት ጥቃት መትረፋቸውን ገለጹ፤ ይሁን እንጅ ለምርመራ ትፈለጋላችሁ በሚል በጊዳ የታሰሩ መሆናቸው…

ከጊዳ አያና ተነስተው ወደ አንገር ጉትን በቅጥቅጥ መኪና ሲጓዙ የነበሩ አማራዎች የተቀነባበረ ካሉት ጥቃት መትረፋቸውን ገለጹ፤ ይሁን እንጅ ለምርመራ ትፈለጋላችሁ በሚል በጊዳ የታሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ከጊዳ አያና ወረዳ ተነስተው ወደ አንገር ጉትን ከተማ መንገዱ ሰላም ነው በሚል በቅጥቅጥ መኪና ሲጓዙ የነበሩ አማራዎች የተቀነባበረ ካሉት ጥቃት መትረፋቸውን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ መከላከያ ደርሶ ከጥቃት የታደጋቸው ቢሆንም ለምርመራ ትፈለጋላችሁ በሚል ለጊዳ አያና ወረዳ ፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ አላግባብ የታሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከተቀነባበረው አደጋ ተርፈናል የሚለው ወጣት ጌታሰው ካሴ (በክርስትና አባቱ የሚጠራ) አቶ መልኬ የተባሉ ሰው ልጅ መሆኑን በመግለጽ ከወንድሙ ተመስገን መልኬ ጋር ሆነው አራት ራሳቸውን ሚያዝያ 22/2014 ከሀሮ አዲስ ዓለም ተነስተው ወደ ኪረሞ ወረዳ ስለማቅናታቸው በመቀጠልም ኪረሞ ካሉ ሌሎች አንዲት የምታጠባ እናትን ጨምሮ ከ5 ሰዎች ጋር ወደ ጊዳ አያና ከተማ ስለመሄዳቸው ለአሚማ ተናግረዋል። በእለቱ ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ደግሞ በጊዳ አያና ካሉ ከሌሎች በግምት 40 ከሚሆኑ ሰዎች ጋር በመሆን ሰላም ነው በመባሉ ወደ አንገር ጉትን ጉዞ ጀምረዋል። ነገር ግን ከከተማዋ በቅርብ ርቀት አስር ደቂቃ እንደተጓዙ ሾፌሩ “መኪናዬ ብልሽት አጋጥሞታል” በማለቱ ጌንዶ በተባለች አካባቢ ሁሉንም በማስረድ ለ1 ሰዓት እንደቆዩ ከአንገር ጉትን ሌላ አንድ ቅጥቅጥ መኪና ይመጣል። በመሃል ሾፌር ከሾፌር ጋር ተነጋግረው ከጊዳ አያና ተሳፍረው ሲመጡ በከፈሉት በአንድ መቶ ብር ክፍያ ከአንገር ጉትን በመጣው መኪና ገብተው እንዲሄዱ ይነገራቸዋል። ገብተው ወንበር ከያዙ በኋላ ለአንድ ሰው መቶ ሀምሳ ብር ነው በሚል ከሾፌሩ ጋር ይነጋገራሉ። በዚህም ተሳፋሪዎች በሁለት ተከፍለው ተከራክረዋል፤ ግማሾቹ እንሂድ ሲሉ ግማሾቹ ደግሞ ከጊዳ በመጣንበት በመቶ ብር እንጅ በመቶ ሀምሳ አንሄድም ሲሉ እየተነጋገሩ ሳለ ከ50 በላይ በሚሆኑ የኦሮሞ ወጣቶች(ቄሮዎች) ይከበባሉ። በመቀጠልም ወጣቶቹ አማራዎች ከተሳፈሩበት መኪና በመጠጋት ሲያፈጡባቸው እና ጥርስ ሲነክሱባቸው ከቆዩ በኋላ ዝም ሲሏቸው ወደ ስድብ ከዛም ወደ ድብደባ ገብተዋል። ይኸውም ምንጮች እንደሚሉት “እናንተ ሰው በላዎች መጣችሁ በዚህ” እያሉ ሲሳደቡ ከቆዩ በኋላ አንደኛው ቄሮ ወደ መኪናው በመግባት ጌታሰው ካሴንና ተመስገን መልኬን በጥፊ እና በቦክስ እየመታ ለማውረድ ይታገላል። እነ ወጣት ጌታሰውም አስወርደው ሊገድሏቸው መሆኑን በመረዳታቸው ” እዚሁ ግደሉን እንጅ አንወጣም” በማለት እምቢተኛ ይሆናሉ፤ በወቅቱ በመኪናው ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች ከዝምታ ውጭ ተው አለማለታቸው አሳዛኝ እንደነበር ተገልጧል። በወቅቱም ድንገት በአንድ ፒካፕ እና በአንድ አምቡላንስ የተጫኑ መከላከያዎች በመድረሳቸው በጥላቻ ተነሳስተው አማራዎችን ለመጨፍጨፍ ከበባ አድርገው የነበሩ የአካባቢው ቄሮዎች ወደ መንደራቸው ይሸሻሉ። እነ ሻምበል አየነው የሚመሩት መከላከያም ከጊዳ አያና ወደ አንገር ጉትን በሚል ይዟቸው ከመጣ በኋላ ጌንዶ ላይ በውሸት መኪና ተበላሽቶብኛል ያለውን ሾፌር መልሶ ወደ ጊዳ እንዲወስድ ያዘዋል፤ በወቅትም ያለምንም ጥገና መኪናውን አስነስቶ ወደመጡበት ይመልሳቸዋል። ጊዳ አያና ከደረሱ በኋላ ግን ከጥቃት የተረፉትን ተሳፋሪዎች ለምርመራ እንፈልጋቸዋለን በመባሉ መከላከያ ለፖሊስ አሳልፎ ስለመስጠቱና ስለመታሰራቸው ለማወቅ ተችሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከወጣት ጌታሰው ጋር ስለተፈጠረው ክስተት በእጅ ስልኩ ላይ ደውሎ እያናገረ ሳለ ሻምበል አየነው ስልኩን በመቀማት ማንነታችን ጠይቀዋል። የወጣት ጌታሰውን ስልክ በመቀማት “ምን እያልክ ነው? አንተ አማራ ሚዲያ ማዕከል ምናምን የምትለው” በማለት ካንጓጠጡ በኋላ “ከእኔ ጋር ነው ያሉ ከእኔ በላይ አንተ አታስባላቸውም” ሲሉ ተደምጠዋል። በንግግራቸውም ነገሩን ቀለል ለማድረግ እየሞከሩ በሌላ በኩል ደግሞ ደርሰው ግን እንደታደጓቸው አስታውቀዋል። በሚዲያ እንዳይወጣ በመፈለግ ለምን ደወላችሁ በማለት ወጣት ጌታሰውን ብሎም ቤተሰባቸው ላይ በመደወል እንዳስፈራሩ ደግሞ ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በመቀጠልም ተሳፋሪዎች ለምርመራ እንደሚፈለጉ፣ የሾፌሩንም መያዙ ለአሚማ የተናገሩት እኒህ የአካባቢው የመከላከያ አዛዥ ሻምበል አየነው ወደ አሚማ በመደወል ምክር አዘል በሆነ መልኩ ለማስፈራራት ሞክረዋል። ስልክ መቀማታቸውና ተሳፋሪዎች ለሚዲያ እንዳይናገሩ መከልከላቸው ልክ አለመሆናቸው ተነግሯቸው የተሰናበትን ቢሆንም በሌላ ሁለት ከአዳማ እና ከባህር ዳር ነን በሚሉ ግለሰቦች ቀጥታ በማስደወል በድጋሜ ለማስፈራራት ሞክረዋል። አሚማ አሁን ላይ ከአደጋ የተረፉ ተሳፋሪዎች “መታሰራቸው አግባብነት የለውም” የሚል የቤተሰቦች ቅሬታም እየደረሰው ይገኛል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply