ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ ባለው የጊዜ ወሰን ውስጥ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ዕቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት…

ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ ባለው የጊዜ ወሰን ውስጥ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ዕቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በአተገባበር ወቅት ኮሮናን እንዴት መከላከል ይቻላል በሚል ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ውይይቱን እየመሩት ያሉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርትኳን ሚዴቅሳ ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ አካባቢ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። በእቅዳቸውም መሰረት ከታህሳስ እስከ ጥር አጋማሽ ድረስ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ስልጠና ለመስጠትና የመራጮች ምዝገባን ከጥር አጋማሽ ሳምንት እስከ የካቲት 3ተኛ ሳምንት ድረስ ለማድረግ በዕቅድ መቀመጡን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡ የእጩ ምዝገባ ከየካቲት መጀመሪያ ላይ የሚከናወን ሲሆን የምርጫ ቅስቀሳውም ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ ይካሄዳል ተብሎ መታሰቡን ተገልጧል። ቦርዱ ኮቪድ 19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶችን በተመለከተም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየመከረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዝግጅትና ዋና ዋና ተግባራት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችም አስተያየት ስለመስጠታቸው ነው በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተገለፀው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply