You are currently viewing ከጎንደር የተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው ወደ ባህር ዳር የተጓዙ በሽህ የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ወደ ስታዲዮም እንዳንገባ በመንግስት የጸጥታ አካል ክልከላ እና ወከባ እየገጠመን ነው አ…

ከጎንደር የተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው ወደ ባህር ዳር የተጓዙ በሽህ የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ወደ ስታዲዮም እንዳንገባ በመንግስት የጸጥታ አካል ክልከላ እና ወከባ እየገጠመን ነው አ…

ከጎንደር የተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው ወደ ባህር ዳር የተጓዙ በሽህ የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ወደ ስታዲዮም እንዳንገባ በመንግስት የጸጥታ አካል ክልከላ እና ወከባ እየገጠመን ነው አሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ፋኖ እያላችሁ ትጨፍራላችሁ እና አትገቡም” ተብለናል የሚሉት ወጣቶች ከጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች ተነስተው ዘንዘልማን አልፈው ቅዱስ ገብርኤል መድረሳቸውን ይናገራሉ። ባህር ዳር ሊገቡ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ እንደደረሱ የሬዲዮ መገናኛ የያዙ የልዩ ኃይል አመራሮች ከ10 እስከ 15 በሚደርሱ ተሽከርካሪዎች የመጡ ደጋፊዎችን ሁሉ በማስቆም እና በማስወረድም ጭምር ወደ ስታዲዮም መግባት አትችሉም ብለው እንደከለከሏቸው ገልጸዋል። ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገውን አምስተኛ ሳምንት ጨዋታውን ለመደገፍ እና ለመከታተል እንጅ እነሱ እንደሚሉት ለሌላ አላማ አይደለም ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ። አሁንም እየፈጸሙት ያለውን ያልተገባ እንግልት አቁመው እንድንገባ ቢያደርጉ መልካም ነው ሲሉ ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply