You are currently viewing ከጎጃም አዲስ አበባ መሥመር፤ ባለፉት 3 ወራት ብቻ መነሻቸውን ከብቸና፣ ከየጁቤ ባሶ፣ ከደብረ ማርቆስ እና ከባሕርዳር ያደረጉ ከ25 የሚበልጡ መንገደኞች እና አሽከርካሪዎች ታግተዋል። 10 የ…

ከጎጃም አዲስ አበባ መሥመር፤ ባለፉት 3 ወራት ብቻ መነሻቸውን ከብቸና፣ ከየጁቤ ባሶ፣ ከደብረ ማርቆስ እና ከባሕርዳር ያደረጉ ከ25 የሚበልጡ መንገደኞች እና አሽከርካሪዎች ታግተዋል። 10 የ…

ከጎጃም አዲስ አበባ መሥመር፤ ባለፉት 3 ወራት ብቻ መነሻቸውን ከብቸና፣ ከየጁቤ ባሶ፣ ከደብረ ማርቆስ እና ከባሕርዳር ያደረጉ ከ25 የሚበልጡ መንገደኞች እና አሽከርካሪዎች ታግተዋል። 10 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል። ከ30 የሚበልጡ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። ከአንድ ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር ከፍለው የተለቀቁ ታጋቾች አሉ። ከብቸና የመጡ፣ የታጋች ቤተሰቦች ብር ሲያሰባስቡ ባነር ይዛችሁ ለሽፍታ ገንዘብ መሰብሰብ አትችሉም ተብለው፤ ደብረ ማርቆስ ላይ ለ2 ስዓት ያህል ታስረውም ነበር። አጋቾች፤ ከጎሐ ጺዮን እስከ ፍቼ ባለው መሥመር ከመንግሥት መዋቅር ጋር አብረው የሚሠሩ ናቸው። ከ2 ቀና በፊት ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ ሲመጣ ለታገተው ታጋች፣ ቤተሰቦቹ ክፍያውን የፈጸሙት ፍቼ ሄደው፣ አባገዳዎች እና የመንግሥት ሰዎች ባሉበት መክፈላቸውን ተ…ናግረዋል። አጋቾች፤ የተደዋወሉበት ሥልክ ቁጥር ይታወቃል፤ ያሉበት ቦታም ይታወቃል፤ ገንዘብ ገቢ የሚደረግበት ሒሳብ ቁጥርም ይታወቃል። የተባሉትን ክፍያ ፈጽመውም፤ ከእንደገና ገንዘብ ጨምሩ ተብለው ያልተለቀቁ ታገቹች አሉ። ከመንገደኞች እና ከአሽከርካሪዎች በተጨማሪ የFAO ሠራተኞች፣ የአሚኮ ጋዜጠኞች እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ባለሙያዎችም የእገታው ሰለባ ሆነዋል። ትኩረት የሰጠው አካል ግን የለም። በዚኹ መስመር፤ ያላቸው አባዱላዎች በሰላም ከሚያልፉ፣ ግመል በመርፊ ቀዳዳ ብታልፍ ይቀላል የሚያስብል ከትራፊክ ፖሊስ እስከ ሕዝባዊ ፓሊስ ድረስ የተዘረጋ መዋቅር አለ። የአማራ የሆነ መኪና ከዐብይ በርሃ የግራናይት ጥሬ ዕቃ፣ አሽዋ፣ ጠጠር እና የጅፕስም ድንጋይ እንዲሁም ኦሮሚያ ክልል ካሉ ስሚንቶ ፋብሪካዎች በየኪላው የእጅ መንሻ እየከፈሉም ጭነት መሥራት ሕልም ሆኖባቸዋል። በአንጻሩ፤ ያላቸው አባዱላዎች ያለምንም ከልካይ ደጀን ድረስ መጥተው ሰው ጭነው ይሄዳሉ፤ ሲፈልጉም ያሳግታሉ። የኦሮሞ መኪኖች የፈለጉትን ነገር ጭነው ወደ አማራ ክልል ይገባል። ከልካይም ጠያቄም የላቸውም። ልታውቁት የሚገባው ነገር፤ ይኽ የእገታ ወንጀል፤ ኦነግ ሸኔ ከሚሉት አካል ጋር የማይገናኝ በጥናት እና በመረጃ እየተከናወነ ያለ አንድን ማኅበረስብ Economical Disable የማድረግ እና የሆነን ቡድን ደሞ ተጠቃሚ የማድረግ ሂደት ነው። ዳሩ ይኽን ልትረዱ ስላልፈለጋችኹ፤ ገንዘብ እየሰበሰባችሁ ታስረክባላችሁ! ፀሀፊ ቃልኪዳን

Source: Link to the Post

Leave a Reply