ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ለማድረግ ደብዳቤ ካስገባው አስራ አምስት ቀን አልፎኛል-የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ከሚዲያ አካላት ጋር ምንም ዓይነት ውይይት አለማድረጋቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት በጠቅላላ ጉባኤ ከተነሱ ጉዳዮች አንዱ ከጋዜጠኞች ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቅረፍ ምን ተሰራ የሚል ነበረበት ይላሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ጋዜጠኛ ታምራት ሀይሉ ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፡፡

ይህንንም መሠረት ማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርጉትን ውይይት መመልከተቸውን ያነሳሉ፡፡

እንዲሁም ባለፉት ስድስት ዓመታት ከሚዲያ አካላት ጋር ምንም ዓይነት ውይይት አለነበራቸውም ሲሉ አቶ ታምራት ይናገራሉ፡፡

ይህንንም በመመለከት የኢትጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ደብዳቤ ማስገባቱ ተገልፃል፡፡

በሚዲያው አካላትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ውይይት እንዲካሄድ የሚጠይቀው ደብዳቤ ከገባ 15 ቀናት አልፎታልም ብለዋል፡፡

ደብዳቤው ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መግባቱን ማረጋገጫ ቢገኝም እስካሁን ድረስ ምንም ምላሽ አልተገኘም ሲሉ ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት ከሰማንያ በላይ የሚዲያ ተቋማት፣የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራት እና የማህበረሰብ ዓቀፍ መገናኛ ብዙሀንን በውስጡ የያዘ ነው፡፡

ዘርፉ በርካታ ችግሮች አሉት ያሉት አቶ ታምራት የጋዜጠኞች እስርን ጨምሮ መረጃ የማግኘት ችግሮችንና የተለያዩ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥያቄ ለማቅረብ በማሰብ ነው ውይይቱ የተፈለገው ብለውናል፡፡

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ የሚዲያው ነፃነት እንዲሁምአፋኝ የተባሉ የመገናኛ ብዙሀን አዋጆች ማሻሻያ ቢደረግላቸውም ተፈፃሚነታቸው ግን አናሳ ነው፡፡

ሰፍቶ የነበረው የሚዲያው ነፃትም በስድስት ዓመታት ውስጥ ቀንሷ ኢትዮጵያ አሁን ከሰሃራ በታች ካሉ ጋዜጠኞችን በማሰር ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደትቀመጥ አድርጓታል፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply