
ከጥቅምት 2015 ጀምሮ በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ቁልቲ ሰፈር ከ570 በላይ ቤቶች በአዲስ አበባ መስተዳድር እንዲፈርሱ ተደርጓል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ቁልቲ ሰፈር ከ570 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ ተደርጓል፤ ከእነዚህም መካከል አብዛኛው የአማራዎች ቤት መሆኑ ተገልጧል። በለሚኩራ ክ/ከተማ ጥር 16/2015 የወረዳው የመስተዳድር አካል እንደሚያፈርስ ተናግሮ በሄደው መሰረት ጥር 17/2015 ከ195 በላይ ቤቶችን በወረዳ 14 ቁልቲ ሰፈር ያሉ ቤቶችን ሲያፈርስ መዋሉ ይታወሳል። ከጥቅምት 17/2015 ጀምሮ፣ ጥር 17፣ 23 እስከ 26/2015 በለሚኩራ ወረዳ 14 ያፈረሱት ቤት ከ570 በላይ መሆኑን ተጎጅዎች ተናግረዋል። ከጥር 23 ጀምሮ ነዋሪዎች በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት አማራጭ ባለመኖሩ እና የታጠቀውን የአገዛዙን ኃይል የሚከላከል በመጥፋቱ ቤታቸውን እያፈረሱ ጥለው ወጥተዋል። ፎቶ_ፋይል
Source: Link to the Post