
በትግራይ ክልል የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በተወሰነ መልኩ መከፈቱን ተከትሎ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከክልሉ እየተሰሙ ካሉ ቅሬታዎች መካከል አንዱ በንግድ ስርዓቱ እና በፍጆታ ዕቃዎች ዋጋ ላይ ያለው ችግር ነው። ቀደም ሲል በዋጋ ጭማሪ የተማረሩ ነዋሪዎች ‘ከጥይት ቀጥሎ ሰውን እየገደለ ያለው ስግብግብ ነጋዴ ነው’ ሲሉ ቆይተዋል። ምሬቱ ግን የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም ቀጥሏል። አሁን እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ከምን የመነጩ ናቸው? ቢቢሲ ነዋሪዎችን እና ኃላፊዎችን አነጋግሯል።
Source: Link to the Post