ከጭቆና እና የግፍ ቀንበር ነፃ የወጡ የአማራ ግዛቶች ከአረመኔው ህዋሃታዊ አገዛዝ ነፃነት ማግስት አደረጃጀቶችን እየመሰረቱ መሆኑን የገለፀው የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር የእንኳን ደስ ያ…

ከጭቆና እና የግፍ ቀንበር ነፃ የወጡ የአማራ ግዛቶች ከአረመኔው ህዋሃታዊ አገዛዝ ነፃነት ማግስት አደረጃጀቶችን እየመሰረቱ መሆኑን የገለፀው የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር የእንኳን ደስ ያ…

ከጭቆና እና የግፍ ቀንበር ነፃ የወጡ የአማራ ግዛቶች ከአረመኔው ህዋሃታዊ አገዛዝ ነፃነት ማግስት አደረጃጀቶችን እየመሰረቱ መሆኑን የገለፀው የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ። የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር ከጭቆና እና ግፍ ነፃ የወጡ የአማራ ግዛቶች ከአረመኔው ህዋሃታዊ አገዛዝ ነፃነት ማግስት እነሆ የወጣት ማህበር አደረጃጀታቸውን እውን እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል። የአማራ ወጣቶች ማህበር በጎንደር እንኳን ለዚህ ቀን አበቃን፤ አበቃችሁ በማለት የደስታ ምኞቱን በማህበራዊ የትስስር ገጹ አጋርቷል። በዛሬው እለት ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በከሃዲው ትሕነግ ተደራራቢ ግፍና በደል ሲፈፀምበት የኖረው በወልቃይት ጠገዴ የዳንሻ ከተማ ወጣቶች አደረጃጀት ፈጥረዋል። ከአማራ ክልል ከሄዱ አመራሮች ጋር በአማራነት ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸውን ለአሚማ የገለፀው የዳንሻ ወጣት በዛሬው እለት የአማራ ወጣቶች ማህበር በዳንሻ ከተማ መመስረቱን አረጋግጧል። ወልቃይት፣ጠገዴ፣ራያ ከትሕነግ ጭቆና በተከፈለው አማራዊ መስዋዕትነት ነጻ በመውጣታቸውም የተሰማቸው ደስታ ከፍተኛ ስለመሆኑ ወጣቶቹ ገልፀዋል። ዳንሻ የትሕነግ ግድያ፣አፈና፣ እስር፣ግፍና የጭቆና ቀንበር ከበረታባቸው አካባቢዎች አንዱ ስለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ለመጥቀስ ይቻላል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply