ከፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ የተሰጠ የአቋም መግለጫ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ ባለፉት አመታት ወያኔ አፋኙ ጨቋኙና የብዙ አማራ ወጣቶችን የቀሰፈው አባቶችንና እናቶችን ያለ ጧሪ ያስቀረው…

ከፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ የተሰጠ የአቋም መግለጫ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ ባለፉት አመታት ወያኔ አፋኙ ጨቋኙና የብዙ አማራ ወጣቶችን የቀሰፈው አባቶችንና እናቶችን ያለ ጧሪ ያስቀረው ብሎም የሀገር በመከላከያ ሰራዊት አባላትን ባልተዘጋጁበትና ባልጠበቁት ሁኔታ በተኙበት በጅምላ እንደጨረሳቸው ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ የፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ ከሌሎች የአማራ ፋኖ ወንድምና እህቶች ጋር በጋራ በመሆን ያለማንም ቀስቃሽ ለሀገሩ፣ ለህዝቡ ብሎም ለመከላከያ ሰራዊት ጭምር ደጀን ለመሆን ጨርቄን ማቄን ሳይል እምቢኝ ለሀገሬ እምቢኝ ለወገኔ በማለት በራሱ ስንቅና ትጥቅ ሀገርን ከመፍረስ ህዝብንም ከሞት የታደገ የሀገር ዋልታና ማገር እንደሆነ አይደለም ወዳጆቻችን ጠላቶቻችን ሳይቀሩ የመሰከሩልን መሬት ላይ የሚታይ እውነታ ነው፡፡ ነገር ግን መንግስት የጭንቅ ጊዜ ደራሽ የክፉ ቀን ዋስ ጠበቃ የሆነውን ፣ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት በፍፁም ጀግንነትና ወኔ ሞራልና ብርታት በመሆን ጀግንነቱን ያስመሰከረ፣ ሴት ያልደፈረ ይልቁንም የአባቶቻችንን ታሪክ የደገመና የመሰከረ፣ መንግስትም ያልተፃረረ እንዲያውም መንግስት እንደመንግስት በዙፋኑ እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሆኖ እያለ ታዲያ ምን ይሉታል መንግስትን የሚፃረሩ ፣ ለሀገር ጠንቅ የሆኑ እንዲሁም ለዚህ ሁሉ ጥፋትና የሰው ሞት ተጠያቂ የሆኑ ወያኔን የመሰሉ ሀገር አፍራሽ፣ኦነግ ሸኔንም የመሰሉ ህዝብን ከቤት ንብረቱ የሚያፈናቅሉና ንፁሀንን በጅምላ የሚያርዱ የሀገር ነቀርሳወች እያሉ ፋኖን ማሳደዱ? ለጊዜው ጥያቄአችንን እናቆየውና በዚህ አፈናና ፋኖን በማሳደድ ስራ ላይ የተጠመደው ስርዓት ዛሬም የፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ አባላትን በማሳደድ እና በማፈን ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ የመንግስት እኩይ ተግባር ሰለባ የሆኑ የብርጌድ አባላትን ስም ዝርዝር እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን፡፡ 1 መምህር አብራራው ማዕከላዊ እርማጭሆ/ ማሰሮ ደምብ 2 አብዮት ተቀባ ማዕከላዊ እርማጭሆ/ ማሰሮ ደምብ 3 ፋኖ ጋሻው ሀይሉ ማዕከላዊ እርማጭሆ/ ማሰሮ ደምብ 4 አቶ ቸኮለ ወርቁ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ነዋሪ ሲሆኑ ሁሉም በቀን 18/09/ 2014 ዓ.ም ከመኖሪያ ቦታቸው ታፍነው የተወሰዱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች በቁጥር ከ200 በላይ የሆሚኑ የማዕከላዊ አርማጭሆ የማሰሮ ደምብ አካባቢ ወጣቶች በዚሁ መንገድ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን እያረጋገጥንላችሁ፤ ፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ ለመንግስት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ያቀርባል 1 ህግ ማስከበር በሚል ሽፋንና እንቅስቃሴ የፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ አባላትና ደጋፊዎች አፈናና እስር እንዲቆም፤ 2 በፋኖ አመራሮችና አባላት ላይ የሚቀርበው የወያኔን ዘመን የሚያስንቀው የፈጠራ ክስ በመረጃና በማስረጃ እንዲሁም ከጫና ገለልተኛ በሆነ አካል በህግ አግባብ እንዲታይ 3 የታፈኑት አባላት ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ ስለማይታወቅ አድራሻቸው በአጭር ጊዜ ለቤተሰቦቻቸው እንዲገለፅላቸው 4 ከጉዳዩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ወጣቶች አፈና እንዲቆም በማለት እንጠይቃለን፡፡ ከፋኖ አማራ ምንሊክ ብርጌድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply