ከፍርድ ውሳኔ ጋር በተያያዘ በዐቃቢ ሕግ ይግባኝ የተባለባቸው 4 ከሰኔ 15/2011ዱ የባለስልጣናት ግድያ ነጻ ተብለው የተፈቱ ግለሰቦች በችሎት ባልተገኙበት መዝገቡ ለመጨረሻ ውሳኔ በሚል ለግንቦት 16/2015 ተቀጥሯል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 12/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ዐቃቢ ሕግ በተሰጠው ፍርድ ቅር በመሰኘት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ይግባኝ የጠየቀባቸው በሰኔ 15/2011 የባ/ዳሩ የአመራሮች እና የጸጥታ አካላት ግድያ ወንጀል ተከሳሾች መካከል ሚያዝያ 24/2015 በነበረው ችሎት ለ28ቱ የእስር ፍ/ቤቱ የፍርድ ውሳኔ የጸደቀላቸው መሆኑ ይታወሳል። ይሁን እንጅ ከአሁን ቀደም የተፈቱት ማለትም፦ 1.ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ፣ 2.ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃባው እና ስለሽ ከበደን ጨምሮ 4 ሰዎችን ፖሊስ በግንቦት 10/2015 ቀጠሮው በችሎት ይዞ እንዲገኝ ትዕዛዝ መሰጠቱ ተገልጧል። ይሁን እንጅ ግንቦት 10/2015 በነበረው ችሎት ይግባኝ የተባለባቸው ተከሳሾች ባልተገኙበት መዝገቡ ለግንቦት 16/2015 ለመጨረሻ ውሳኔ ተቀጥሯል።
Source: Link to the Post