ከፍተኛ ስርቆት በመዲናችን አዲስ አበባ ተፈጽሟል!. ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ተብሏል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎሮ ሰፈራ ልዩ ቦታው ፖስታ ቤት መቲ ጋራዥ…

ከፍተኛ ስርቆት በመዲናችን አዲስ አበባ ተፈጽሟል!

. ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ተብሏል

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎሮ ሰፈራ ልዩ ቦታው ፖስታ ቤት መቲ ጋራዥ አካባቢ በቀን 11፣ 2014 ዓ.ም የቻይና ነጋዴዎች ተከራይተው ይሰሩበት የነበረው መጋዘን ላይ ከፍተኛ ስርቆት የተፈጸመው፡፡

በዚህ ስርቆት 418 ያህል ቴሌቪዥኖች የተሰረቁ ሲሆን ቁጥራቸው የማይታወቅ ላፕቶፕ ኮምፒተሮች የመኪና ባትሪዎች እንደዚሁም 63ሺህ ጥሬ ገንዘብ አብሮ መሰረቁን ነው ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኝው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

እነዚህ ነጋዴዎች መጋዘኑን የተከራዩት ከአንድ ወር በፊት የነበረ ሲሆን ከቻይና በርካታ እቃዎችን እያስመጡ ለነጋዴዎች ያከፋፍሉበታል የነበረ መጋዘን ነው፡፡
አቶ መኮንን ድርጊቱን ያቀነባበሩት የጥበቃ ሰራተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ያላቸውን ግምት ያስቀመጡ ሲሆን አሁን ላይ እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል በለዋል፡፡

ቃላቸውን ለፖሊስ የሰጡት የጥበቃ ሰራተኞች በበኩላቸው ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ያሉት አቶ መኮነን ፣ከድርጊቱ መፈጸም በላይ የጸጥታ አካላት የሰጡት ምላሽ እንዳሳዘናቸው ነግረውናል፡፡

የቤት አከራዩ አቶ መኮንን ስርቆቱ በተፈጸመበት እለት መብራት ጠፍቶ እንደነበረ እና የአይሱዚ መኪና መጋዘን ውስጥ ገብቶ መጫኑን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ጥቆማቸውን እንዳደረሱዋቸው ነግረውናል፡፡

መጋቢት 19፣ቀን 2014
ሔኖክ ወ/ ገብርኤል

Source: Link to the Post

Leave a Reply