ከፍተኛ ትኩረት ለፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ‼️ ታሕሳስ 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ነገ ማለትም ታህሳስ 24/2015 ዓ.ም የፍ/ቤት ቀጠሮው ነው ።ነገር ግን…

ከፍተኛ ትኩረት ለፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ‼️ ታሕሳስ 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ነገ ማለትም ታህሳስ 24/2015 ዓ.ም የፍ/ቤት ቀጠሮው ነው ።ነገር ግን<< ፍትህ ለማይገኝበት የካንካሮ ፍ/ቤት ፤የግሮሰሪ ቤት የሃሰት ውንጀላ እና የግሮሰሪ ቤት የክስ ዶሴ ፍ/ቤት አልገኝም ።>>በማለት መወሰኑን የአማራ ወጣቶች በባህርዳር (አወማ) አገኘሁት ያለው መረጃ ያመለክታል። አርበኛ ዘመነ ካሴም በዚህ ፅኑ አቋሙ የፀና መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል። በነገው ዕለት አፋኙ የመንግስት ሀይል የሚከተሉትን ሁለት አደገኛ አማራጮችን እንደ ወሰኑ መረጃዎች ደርሶናል ብሏል አወማ ፦ 1ኛ). በዛሬው ዕለት ወደ ማታ ከምሽቱ 11:00 ሰዐት አካባቢ ጀምሮ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን አስገድዶ ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ማስወጣት እና ከተማ ለጊዜው ቦታ የት እንደሆነ ባልታወቀ ስፍራ አሳድረው ፍ/ቤት ማቅረብ ።ይህ ካልተሳካ ደግሞ ፦ 2ኛ).ነገ በተመሳሳይ ወደ ሰባታሚት ማረሚያ ቤት አፋኝ የመንግሰት ሀይል በማሰማራት አስገድዶ አስወጥቶ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚሉ ናቸው ። በመሆኑም ለመላው የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ወጣቶች ፣ነዋሪዎች ከዛሬ ከሰዐት በኃላ ጀምሮ በሰባታሚት ማረሚያ ቤት እንዲሁም አካባቢው አስፈላጊውን ጥበቃ እና ክትትል እንድታደርጉ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥሪውን ያስተላልፋል ። በተጨማሪም ለመላው የአማራ ወጣት እና ህዝብ የምናስተላልፈውን ቀጣይ መልዕክት በንቃት እንዲከታተል ፤ለዚህ የሞራል ፣የስነ -ልቦና ዝግጅት እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።ከዚህ በኃላ ለሚፈጠረው ሁሉ ሃላፊነቱን የሚወሰደው አፋኙ ስርዓት እንደሆነ ለማስገንዘብ እንወዳለን ። በማሰር ፣በማፈን ፣በማዋከብ እንዲሁም በማሳደድ የተጀመረ ፤የሚቆም የአማራ ትግል የለም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል‼️ የአማራ ወጣቶች በባህርዳር “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply