ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመራቂ ተማሪዎች ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ያቀረቡት ጥሪ ለጊዜው እንዲቆም ተደረገ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 25/2013ዓ.ም ባህርዳር ከ…

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመራቂ ተማሪዎች ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ያቀረቡት ጥሪ ለጊዜው እንዲቆም ተደረገ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 25/2013ዓ.ም ባህርዳር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 23 ፣2013 ጀምሮ ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ያቀረቡት ጥሪ ለጊዜው እንዲቆም መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በተላለፈው መልዕክት ላይ በወቅቱ በተፈጠረው አገራዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘገይ መደረጉን አስታውቋል። በዚሁ መሰረት እስካሁን በዩኒቨርሲቲዎቻቸው የደረሱ ተማሪዎች በግቢያቸው እንዲቆዩና የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያ እየተከታተሉ እንዲንቀሳቀሱ አሳስቧል። እስካሁን ከወላጆቻቸው አካባቢ ያልተነሱ ተማሪዎች ደግሞ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ባሉበት እንዲቆዩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply