
ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ጦርነት የቋጨው የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ተከትሎም የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መቀጠላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብት በሪፖርቱ ይፋ አደረገ።ስምምነቱ አስር ወራት ገደማ ቢያስቆጥርም ጥሰቶች መቀጠላቸውን በኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንዲያጣራ በተባበሩት መንግሥታት የተቋቋመው የሰብዓዊ መብቶች የባለሙያዎች ቡድን ትናንት መስከረም 7/2015 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
Source: Link to the Post