ከ 200ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርት በዚህ ዓመት ተገበያይቷል፡፡በዚህ ዓመት ከ 200 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የምርት ግብይት መካሄዱን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታዉቋል፡፡የምርት ገበያዉ የ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/k9ybeGiGKcc3eYr-X261RWC7wayw0L1a4lP7Gi6KxxE216BNfupb0tVHxArg_bTdc86i26g5H9ejWCyCm3Tq-JF-QOal4yhRIrEm4vruA9Q-ePS6kK4ruF1GKU1CMOMfhuMG2wBrp2BRrrIXCy6Ag_v2XLRmH1EM7XmIfaRa2Qdr1ZA8oyzlMXzw-j92f2TzKWCEB8uCD5VDFNVtPLONSvGKOWjsLqXzlqzKObjiCN-UC5BwkfDIJ7O34QCURX7y4lgTs5uOztB6IK7U58UiT5vO_QNVkjRPHQA2ef-VokCrvNxxGj8c1YMhCyEfPZj2vjH-NXnyoHkc__RH_RK5jA.jpg

ከ 200ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርት በዚህ ዓመት ተገበያይቷል፡፡

በዚህ ዓመት ከ 200 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የምርት ግብይት መካሄዱን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታዉቋል፡፡

የምርት ገበያዉ የመጋዘን ኦፕሬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ በሃይሉ ንጉሴ ወደ ምርት ገበያዉ መጥተዉ የምርት ጥራት ደረጃ ሰርተፊኬት እና የክምችት አገልግሎት ያገኙትን ሳይጨምር ምርት ገበያዉ በዚህ ዓመት ከ 200ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርት ማገበያየቱን ገልጸዋል፡፡

ምርት ገበያዉ በዚህ ዓመት 22 ምርቶችን ሲያገበያይ እንደነበር የገለጹት ሃላፊዉ ፣በተጨማሪም ምርት ገበያዉ እንደ እቅድ የያዛቸዉ በርካታ አዳዲስ ምርቶች መኖራቸዉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ለቅመማ ቅመም ግብይት ዉል እንዳልነበር ያነሱት አቶ በሃይሉ አሁን ላይ ለቅመማ ቅመም ግብይት ዉል ተዘጋጅቶላቸዉ ወደ ግብይት ስርዓቱ መግባታቸዉን ነዉ የነገሩን፡፡

የምርቱን የጥራት ደረጃ ፣ ምርቱ የሚገበያይበት መስፈርቶችን እና ክፍያ እንዴት እንደሚፈጸም ዉል ተዘጋጅቶ በዚህ ዓመት ቅመማ ቅመም ማገበያየት መቻሉን ነግረዉናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እጣን የግብይት ዉል ተዘጋጅቶለት ወደ ገበያዉ መግባቱን ነዉ የገለጹት፡፡

በዚህ ዓመት ስንዴ፣ ግብጦ፣እጣን ፣ሩዝ እና ኮረሪማን ወደ ግብይት ስርዓቱ አስገብተናል ያሉት ሃላፊዉ የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ በተለይ የሲሚንቶ እና የጨዉ ግብይት ስርዓት ላይ የሚታዩትን ድክመቶች በዘመናዊ ግብይት ስርዓት ማገዝ የምንችልበትን መንገድ እያጠናን እንገኛለን ብለዋል፡፡

እስከዳር ግርማ
ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply