ከ 70 በላይ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ኤኬስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡ኤክስፖዉን ያዘጋጀዉ የአርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ግርማ በሰጡት መግለጫ በተዘጋጀው አር…

ከ 70 በላይ ድርጅቶች የሚሳተፉበት ኤኬስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡

ኤክስፖዉን ያዘጋጀዉ የአርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ግርማ በሰጡት መግለጫ በተዘጋጀው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ ከ 70 በላይ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ከ የካቲት 15 እስከ የካቲት 17 ለሶስት ቀናት በሚኒሊየም አዳራሽ በሚካሄደዉ ኤክስፖ ላይ እስከ 10 ሺህ ሰው እንደሚጠበቅም ተነግሯል፡፡

በኤክስፖዉ የሚሳተፉ ድርጅቶች የህብረተሰቡን አቅም ታሳቢ በማድረግ ታላቅ ቅናሽ ያደረጉ መሆናቸዉንም አቶ ቢንያም አስታዉቀዋል፡፡

የኤክስፖዉ አላማ ሁሉንም በአንድ ቦታ በማካተት ቤት መግዛት የሚፈልገውን ሰው ድካም ለማቅለል እንደሆነም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከልም ባንኮች፤ ቤት አልሚ ድርጅቶች ፤የፈርኒቸር አምራችና ቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

“ሳያዩ ቤት እንዳይገዙ ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደዉ የዘንድሮዉ ኤክስፖም ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ከአዘጋጁ ሰምተናል፡፡

በልዑል ወልዴ

ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply