ከ1.1 ቢሊየን ብር በላይ የፈጀው ሀይሌ ሆቴልና ሪዞርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መቀመጫ በሆነችው ወላይታ ሶዶ የተከፈተው የሀይሌ ሆቴል ከ1.1 ቢሊየን ብር በላይ መፍጀቱ ተገልጿል።

የሀይሌ ሆቴል ወላይታ ሶዶ ለ3 መቶ ሰራተኞች የስራ እድል እንደፈጠረም ታወቋል፡፡

አሁን ላይ አጠቃላይ በሀይሌ ሆቴሎች ለ1 ሺህ መቶ ሰራተኞች የስራ እድል እንደፈጠረ ተገልጿል፡፡

የድርጅቱ ባለቤት ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የውጭ ምንዛሬ ችግር ስራችዉ ላይ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮባቸው እንዳለፈ ገልፀዋል።

የሀይሌ ሆቴል ግሩፑ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ በበኩላቸው ሀይሌ ሆቴል ወላይታ በውስጡ 1መቶ 7 የማረፊያ ክፍሎች ፤ 7 የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ እንዲሁም ሶስት የምግብ አዳራሽ አሉት ብለዋል፡፡

በሚቀጥለው 6 ወር ሶስት ሆቴል በጅማ ፣በደብረ ብርሃንና በወልቂጤ ለመክፈት ዝግጅት መጠናቀቁም ተገልጿል።

ሀይሌ ሆቴል እና ሪዞርት በቅርቡ በምስራቅ አፍሪካ መዳረሻውን ለማስፋት እየሰራ እንዳለም ተገልጿል

ለአለም አሰፋ
ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply