ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች መካከል 3.2 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸዉ ተገለጸፈተናዉን ከሰጡ ትምህርት ቤቶች መካከል 1 ሺህ 3 መቶ 28 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም ተብሏልፈተናዉ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/thtpuY13e2GlK1EXM-j2yZuqs8ZMl5NVrz76_eI9PrnOmlc65ygPGOWpfe5P8cu3tJpHJlP3lAiJ89EQiG9SVBWag1C7jajHDDbEK_LnGTL2sbJmFNYzzfIAXm8S8xa4JeElRwCWbawbRJaX1wBc0Mp9b-0XKBHPcv1Wr82AtZLy8Rj6SEHuLaynIBfn5sIjKhlOPXGkV9icUTsJogRSwch-z4t8MMb9-ZpQMVdVf7CSumWJWbOSqFprh_ciCRIVB39Ru_HCNXGEHwyw0BXu0ux7m1RUu977E53rwrF5akUJ14vOyvT3PbLmQBS0PfOFdZA3hejp8YDiBdD24swL_A.jpg

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች መካከል 3.2 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸዉ ተገለጸ

ፈተናዉን ከሰጡ ትምህርት ቤቶች መካከል 1 ሺህ 3 መቶ 28 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም ተብሏል

ፈተናዉን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 3.2 በመቶ ብቻ ማለፋቸዉን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በዚህኛዉ ዓመት የ12ኛ ክፍል የተማሪዎች ከፍተኛዉ ዉጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መመዝገቡን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የተመዘገበዉ ከፍተኛዉ ዉጤትም 649 መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ የተመዘገበዉ ከፍተኛዉ ዉጤት ደግሞ 533 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በ2014 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 3.3 በመቶ መሆናቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ 15 ተማሪዎች ከ6መቶ በላይ ያስመዘገቡ ሲሆን፤ በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 205 ተማሪዎች ከ6መቶ በላይ ማስመዝገባቸዉ ተገልጿል፡፡

ወንዶች ከሴቶች በተሻለ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ከፍኛ ዉጤት ማስመዝገባቸዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በዘንድሮዉ ዓመት ከፍተኛ ዉጤት የተመዘገበዉ ከተማ ላይ ባሉ ትምህርት ቤቶች መሆናቸዉን የገለጹት ሚኒስቴሩ አሁንም ከፍተኛ ዉጤት የሚመዘገበዉ በከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት 12ኛ ክፍል የነበሩ የትግራይ ተማሪዎች በነገዉ ዕለት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply