ከ20 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ፡፡የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የክረምት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/eoYwz_O79em5_Xj_yEXSiSfjkxzpcOziJgP69rkTIGCBivAXWRdr7w4cayxMC5bmuVKTBwTD33A7jkci7GdvHZ8nSCTDCXY_WHa27ewm7ipC1h9bpkkrKurHyspKkAWcpM6xLTY9DzjwNdzFn7VNoXTzcmf6JbAVBqjLIvmAFnS1FDCmkDXpDsm7TS_CaIuOSGNsBYYnPI2c6W-jDiWQZorw-tgtUnFXlGkNpZTJu0TUmcRm9d80xXO885AgOapDkxGPz_DgwHgKRs4va5hQItdFhYhZy6cO9wcRTYmy8Dy9zr5qTX_SSM2KVpcBWD_X582VVouTFf-MmIZgNfW4Aw.jpg

ከ20 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የክረምት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከሰኔ 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚከናወን አስታውቋል፡፡

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ግዜ በሁሉም የአገሪቱ እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ይከናወናል ተብሏል፡፡

ከ50 ሚሊዮን 447ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት እንደሚከናወኑና በዚህም ከ15ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንደሚሰጥ የኢፌድሪ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አስታውቀዋል፡፡

ወጣቶቹ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ በትምህርትና ጤና አገልግሎት፣በማህበረሰብ ዓቀፍ ልማት፣በሰላምና ደህንነትና ሌሎች በርካታ ተግባራት ላይ እንደሚሰማሩም ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ህብረተሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንዲያደርጉለትም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ፎቶ-ፋይል

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply